መዝሙር 127 NASV - 诗篇 127 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 127:1-5

መዝሙር 127

በእግዚአብሔር መታመን

የሰሎሞን መዝሙረ መዓርግ

1እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣

ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤

እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣

ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።

2የዕለት ጒርስ ለማግኘት በመጣር፣

ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣

አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤

እርሱ ለሚወዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።127፥2 ወይም ተኝተው ሳሉ ምግብ ያዘጋጅላቸዋል።

3እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤

የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።

4በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣

በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው።

5ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ፣

የተባረከ ሰው ነው፤

ከጠላቶቻቸው ጋር በአደባባይ በሚሟ

ገቱበት ጊዜ፣ አይዋረዱም።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 127:1-5

第 127 篇

颂赞上帝的美善

所罗门上圣殿朝圣之诗。

1若不是耶和华建造房屋,

建造者的工作都是徒劳。

若不是耶和华保护城池,

守城者保持警觉也是徒然。

2你早起晚睡,

为生活操劳也是徒然,

唯有耶和华所爱的人才能安眠。

3儿女是耶和华所赐的礼物,

孩子是祂所给的赏赐。

4人年轻时生的儿女犹如战士手中的箭。

5袋中装满了箭的人有福了!

他们在城门与仇敌争论时,

必不致蒙羞。