መዝሙር 116 NASV - 诗篇 116 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 116:1-19

መዝሙር 116

ምስጋና

1የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና፣

እግዚአብሔርን ወደድሁት።

2ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና፣

በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።

3የሞት ወጥመድ ያዘኝ፤

የሲኦልም116፥3 ዕብራይስጡ ሲኦል ይላል። ጣር አገኘኝ፤

ጭንቅና ሐዘን አሸነፈኝ።

4እኔም የእግዚአብሔርን ስም ጠራሁ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ታድናት ዘንድ እለምንሃለሁ” አልሁ።

5እግዚአብሔር ቸርና ጻድቅ ነው፤

አምላካችን መሓሪ ነው።

6እግዚአብሔር ገሮችን ይጠብቃል፤

እጅግ ተቸግሬ ሳለሁ አዳነኝ።

7ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤

እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና፤

8አንተ ነፍሴን ከሞት፣

ዐይኔን ከእንባ፣

እግሮቼን ከመሰናከል አድነሃልና።

9እኔም በሕያዋን ምድር፣

በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ።

10“እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣116፥10 ወይም ያኔ እንኳን

እምነቴን ጠብቄአለሁ።

11ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣

“ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።

12ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣

ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?

13የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤

የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

14በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣

ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።

15የቅዱሳኑ ሞት፣

በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።

16እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤

እኔ የሴት ባሪያህ116፥16 ታማኝ አገልጋይህ ወይም ታማኝ ልጅህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፣

ከእስራቴም ፈታኸኝ።

17ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤

የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

18በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣

ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፤

19ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣

በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ አደርጋለሁ።

ሃሌ ሉያ።116፥19 አንዳንዶች እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 116:1-19

第 116 篇

感谢拯救之恩

1我爱耶和华,

因为祂垂听了我的呼求和祷告。

2因为祂垂听我的祈求,

我一生都要向祂祷告。

3死亡的绳索缠绕我,

阴间的恐怖笼罩我,

我被困苦和忧愁淹没。

4于是,我求告耶和华,

说:“耶和华啊,求你拯救我。”

5耶和华仁慈、公义,

我们的上帝充满怜悯。

6耶和华保护心地单纯的人,

危难之时祂救了我。

7我的心啊,再次安宁吧,

因为耶和华恩待你。

8祂救我的性命脱离死亡,

止住我眼中的泪水,

使我双脚免于滑倒。

9我要在世上事奉耶和华。

10我相信,所以才说:

“我受尽了痛苦。”

11我曾惊恐地说:

“人人都说谎。”

12我拿什么报答耶和华赐给我的一切恩惠呢?

13我要为耶和华的拯救之恩而举杯称颂祂的名。

14我要在耶和华的子民面前还我向祂许的愿。

15耶和华的眼目顾惜祂圣民的死亡。

16耶和华啊!我是你的仆人,

是你的仆人,是你婢女的儿子。

你除去了我的锁链。

17我要向你献上感恩祭,

呼求你的名。

18-19我要在耶路撒冷

在耶和华的殿中,

在耶和华的子民面前还我向祂许的愿。

你们要赞美耶和华!