መዝሙር 112 NASV - 诗篇 112 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 112:1-10

መዝሙር 112

የጻድቅ ሰው ባሕርይ

1ሃሌ ሉያ።112፥1 እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ነው።

እግዚአብሔርን የሚፈራ፣

በትእዛዙም እጅግ ደስ የሚሰኝ የተባረከ ነው።

2ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤

የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።

3ሀብትና ብልጽግና በቤቱ ይሞላል፤

ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።

4ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣

ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።

5ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣

ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል፤

6ለዘላለም ከስፍራው አይናወጥምና፤

ጻድቅ ሰው112፥6 ወይም እግዚአብሔር ቸር ርኅሩኅና ጻድቅ ስለ ሆነ ሲታወስ ይኖራል።

7ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤

ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።

8ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤

በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።

9በልግስና ለድኾች ሰጠ፤

ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፤

ቀንዱም112፥9 በዚህ ስፍራ ክብርን ያመለክታል። በክብር ከፍ ከፍ ይላል።

10ክፉ ሰው ይህን በማየት ይበሳጫል፤

ጥርሱን ያፋጫል፤ እየመነመነም ይጠፋል፤

የክፉዎችም ምኞት ትጠፋለች።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 112:1-10

第 112 篇

敬畏上帝者必蒙福

1你们要赞美耶和华!

敬畏耶和华、乐于遵行祂命令的人有福了!

2他的子孙在世上必兴盛,

正直人的后代必蒙福。

3他的家财丰厚,

他的公义永存。

4黑暗中必有光照亮正直人,

照亮有恩慈、好怜悯、行公义的人。

5慷慨借贷,

行事公正的人必亨通。

6他必永不动摇,

义人必永远蒙眷顾。

7他不怕恶讯,

他坚定地信靠耶和华。

8他心里镇定自若,毫不害怕,

他终必战胜仇敌。

9他慷慨施舍,周济穷人;

他的仁义永远长存;

他必充满力量,得享尊荣。

10恶人见状,必然恼怒,

咬牙切齿,气绝身亡。

恶人的盼望必破灭。