መዝሙር 111 NASV - 诗篇 111 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 111:1-10

መዝሙር 111111፥0 የግጥሙ መሥመሮች እያንዳንዳቸው ከላይ እስከ ታች በተከታታይ በዕብራይስጥ ፊደሎች ቅደም ተከተል የተቀመጡ ናቸው።

ለመለኮቱ ባሕርያት የቀረበ ጸሎት

1ሃሌ ሉያ።

በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣

ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።

2የእግዚአሔር ሥራ ታላቅ ናት፤

ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል።

3ሥራው ባለ ክብርና ባለ ግርማ ነው፤

ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

4ድንቅ ሥራው ሲታወስ እንዲኖር አደረገ፤

እግዚአብሔር ቸር፣ ርኅሩኅም ነው።

5ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤

ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።

6ለሕዝቡ የአሕዛብን ርስት በመስጠት፣

የአሠራሩን ብርታት አሳይቶአል።

7የእጁ ሥራ እውነተኛና ቅን ነው፤

ሥርዐቱም ሁሉ የታመነ ነው፤

8ከዘላለም እስከ ለዘላለም የጸና ነው፤

በእውነትና በቅንነትም የተሠራ ነው።

9ለሕዝቡ መዳንን ሰደደ፤

ኪዳኑንም ለዘላለም አዘዘ፤

ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው።

10እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤

ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፤

ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 111:1-10

第 111 篇

赞美上帝

1你们要赞美耶和华!

在正直人的大会中,

我要全心全意地称谢耶和华。

2耶和华的作为伟大,

所有喜欢的人都必思想。

3祂的作为荣耀威严,

祂的公义永远长存。

4祂的奇妙作为令人无法忘怀。

耶和华充满怜悯和恩惠。

5祂赐下粮食给那些敬畏祂的人,

祂永不忘记自己的约。

6祂向自己的子民彰显大能,

把列国的土地赐给他们。

7祂凭信实和公正行事,

祂的法则可靠,

8是凭信实和正直赐下的,

存到永永远远。

9祂救赎了自己的子民,

立了永远的约,

祂的名神圣可畏。

10智慧始于敬畏耶和华,

遵行祂命令者皆明睿。

祂永远当受赞美。