መዝሙር 110 NASV - 诗篇 110 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 110:1-7

መዝሙር 110

መሲሑ ንጉሥና ካህን

የዳዊት መዝሙር

1እግዚአብሔር ጌታዬን፣

“ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ፣

እስከማደርግልህ ድረስ፣

በቀኜ ተቀመጥ” አለው።

2እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰዳል፤

አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ።

3ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣

ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤

ከንጋት ማሕፀን፣

በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣

የጐልማሳነትህን ልምላሜ110፥3 ወይም ጐልማሶችህ እንደ ንጋት ወዳንተ ይመጣሉ ማለት ነው። እንደ ጠል ትቀበላለህ።

4“እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት፤

አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣

እግዚአብሔር ምሎአል፤

እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም።

5ጌታ በቀኝህ ነው፤

በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቃቸዋል።

6በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤

በየአገሩ ያሉትንም ራሶች ከስክሶ ሬሳ በሬሳ ያደርጋቸዋል።

7መንገድ110፥7 ወይም ሥልጣን ለመስጠት ኀይል ያለው ሥልጣን ላይ ያስቀምጠዋል ዳር ካለች ፈሳሽ ውሃ ይጠጣል፤

ስለዚህ ራሱን ቀና ያደርጋል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 110:1-7

第 110 篇

上帝和祂拣选的王

大卫的诗歌。

1耶和华对我主说:

“你坐在我的右边,

等我使你的仇敌成为你的脚凳。”

2耶和华必从锡安扩展你的王权,

你必统管你的仇敌。

3你跟仇敌作战的时候,

你的百姓必甘心跟从,

他们衣着圣洁,

如清晨的甘露。

4耶和华起了誓,永不反悔,

祂说:“你照麦基洗德的模式永远做祭司。”

5主在你身旁保护你,

祂发怒的时候,必毁灭列王。

6祂要审判列国,

使列国尸横遍野。

祂要毁灭世上的首领。

7祂要喝路旁的溪水,

祂必精神抖擞。