መዝሙር 104 NASV - 诗篇 104 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 104:1-35

መዝሙር 104

የፍጥረት መብት

1ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤

ክብርንና ግርማን ለብሰሃል።

2ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል፤

ሰማያትንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፤

3የእልፍኝህን አግዳሚ በውሆች ላይ አኖርህ፤

ደመናትን ሠረገላህ አደረግህ፤

በነፋስ ክንፍ ትሄዳለህ።

4መላእክትህን104፥4 መልእክተኞቹን ወይም አገልጋዮቹን መንፈስ፣

አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ።

5ለዘላለም እንዳትናወጥ፣

ምድርን በመሠረቷ ላይ አጸናሃት።

6በጥልቁ እንደ ልብስ ሸፈንሃት፤

ውሆችም ከተራሮች በላይ ቆሙ።

7በገሠጽሃቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ፤

የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ።

8በተራሮች ላይ ፈሰሱ፤

ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ፣

ወደ ሸለቆዎች ወረዱ።

9ተመልሰው ምድርን እንዳይሸፍኑ፣

አልፈውም እንዳይመጡ ድንበር አበጀህላቸው።

10ምንጮችን በሸለቆ ውስጥ እንዲሄዱ አደረግህ፤

በተራሮችም መካከል ይፈሳሉ፤

11የዱር እንስሳትም ከዚያ ይጠጣሉ፤

የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ይቈርጣሉ።

12የሰማይ ወፎች ጎጇቸውን በወንዞቹ ዳር ይሠራሉ፤

በቅርንጫፎችም መካከል ይዘምራሉ።

13ከላይ ከእልፍኝህ ተራሮችህን ታጠጣለህ፤

ምድርም በሥራህ ፍሬ ትረካለች።

14ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣

ለእንስሳት ሣርን፣

ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤

15የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣

ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣

ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል።

16ደግሞም የእግዚአብሔር ዛፎች፣

እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች ጠጥተው ይረካሉ፤

17ወፎች ጎጆአቸውን በዚያ ይሠራሉ፤

ሽመላ በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ታገኛለች።

18ረጃጅሙ ተራራ የዋልያ መኖሪያ፣

የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው።

19ጨረቃን የወቅቶች መለያ አደረግሃት፤

ፀሓይም የምትጠልቅበትን ጊዜ ታውቃለች።

20ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤

የዱር አራዊትም ሁሉ በዚህ ጊዜ ወጥተው ይራወጣሉ።

21የአንበሳ ግልገሎች ምግብ ፍለጋ ይጮኻሉ፤

የሚበሉትንም ከእግዚአብሔር ይሻሉ።

22ፀሓይ በወጣች ጊዜም ይመለሳሉ፤

በየጐሬአቸውም ገብተው ይተኛሉ።

23ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል፤

እስኪመሽም በተግባሩ ላይ ይሰማራል።

24እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው!

ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤

ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች።

25ይህች ባሕር ሰፊና የተንጣለለች ናት፤

ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣

ስፍር ቍጥር የሌላቸውም ነፍሳት በውስጧ አሉ።

26መርከቦች በላይዋ ይመላለሳሉ፤

አንተ የፈጠርኸውም ሌዋታን በውስጧ ይፈነጫል።

27ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸው ዘንድ፣

እነዚህ ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ።

28በሰጠሃቸውም ጊዜ፣

አንድ ላይ ያከማቻሉ፤

እጅህንም ስትዘረጋ፣

በመልካም ነገር ይጠግባሉ።

29ፊትህን ስትሰውር፣

በድንጋጤ ይሞላሉ፤

እስትንፋሳቸውንም ስትወስድባቸው ይሞታሉ፤

ወደ ዐፈራቸውም ይመለሳሉ።

30መንፈስህን ስትልክ፣

እነርሱ ይፈጠራሉ፤

የምድርንም ገጽ ታድሳለህ።

31የእግዚአብሔር ክብር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤

እግዚአብሔር በሥራው ደስ ይበለው፤

32እርሱ ምድርን ሲመለከት፣ ትንቀጠቀጣለች፤

ተራሮችም እርሱ ሲዳስሳቸው ይጤሳሉ።

33በሕይወት ሳለሁ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤

ቆሜ እስከ ሄድሁ ድረስም አምላኬን እወድሳለሁ።

34እኔ በእግዚአብሔር ደስ እንደሚለኝ፣

የልቤ ሐሳብ እርሱን ደስ ያሰኘው።

35ኀጥአን ከምድር ገጽ ይጥፉ፤

ዐመፀኞች ከእንግዲህ አይገኙ።

ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤

ሃሌ ሉያ።104፥35 እግዚአብሔር ይመስገን የሚሉ ትርጒሞች አሉ፤ በሰብዓ ሊቃናት ትርጒም ይህ መሥመር በመዝ 105 መጀመሪያ ላይ ይገኛል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 104:1-35

第 104 篇

称颂创造主——上帝

1我的心啊,要称颂耶和华。

我的上帝耶和华啊,

你是多么伟大!

你以尊贵和威严为衣,

2你身披光华如披外袍,

你铺展穹苍如铺幔子。

3你在水中设立自己楼阁的栋梁。

你以云彩为车驾,乘风飞驰。

4风是你的使者,

火焰是你的仆役。

5你奠立大地的根基,

使它永不动摇。

6你以深水为衣覆盖大地,

淹没群山。

7你一声怒叱,众水便奔逃;

你一声雷鸣,众水就奔流,

8漫过山峦,流进山谷,

归到你指定的地方。

9你为众水划定不可逾越的界线,

以免大地再遭淹没。

10耶和华使泉水涌流在谷地,

奔腾在山间,

11让野地的动物有水喝,

野驴可以解渴。

12飞鸟也在溪旁栖息,

在树梢上歌唱。

13祂从天上的楼阁降雨在山间,

大地因祂的作为而丰美富饶。

14祂使绿草如茵,滋养牲畜,

让人种植作物,

享受大地的出产,

15有沁人心怀的醇酒、

滋润容颜的膏油、

增强活力的五谷。

16耶和华种植了黎巴嫩的香柏树,

使它们得到充沛的水源,

17鸟儿在树上筑巢,

鹳鸟在松树上栖息。

18高山是野山羊的住处,

峭壁是石獾的藏身之所。

19你命月亮定节令,

使太阳自知西沉。

20你造黑暗,定为夜晚,

作林中百兽出没的时间。

21壮狮吼叫着觅食,

寻找上帝所赐的食物。

22太阳升起,

百兽便退回自己的洞窟中休息,

23人们外出工作,直到黄昏。

24耶和华啊,你的创造多么繁多!

你用智慧造了这一切,

大地充满了你创造的万物。

25汪洋浩瀚,

充满了无数的大小水族,

26船只往来于海上,

你造的鲸鱼也在水中嬉戏。

27它们都倚靠你按时供应食物。

28它们从你那里得到供应,

你伸手赐下美食,

使它们饱足。

29你若对它们弃而不顾,

它们会惊慌失措。

你一收回它们的气息,

它们便死亡,归于尘土。

30你一吹气便创造了它们,

你使大地更新。

31愿耶和华的荣耀存到永远!

愿耶和华因自己的创造而欢欣!

32祂一看大地,大地就震动;

祂一摸群山,群山就冒烟。

33我要一生一世向耶和华歌唱,

我一息尚存就要赞美上帝。

34愿祂喜悦我的默想,

祂是我喜乐的泉源。

35愿罪人从地上消逝,

愿恶人荡然无存。

我的心啊,要称颂耶和华!

你们要赞美耶和华!