መዝሙር 102 NASV - 诗篇 102 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 102:1-28

መዝሙር 102

በክፉ ጊዜ የቀረበ ጸሎት

ባዘነና ልመናውን በእግዚአብሔር ፊት ባፈሰሰ ጊዜ፣ የተጨነቀ ሰው ጸሎት

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤

ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ።

2በመከራዬ ቀን፣ ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤

ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤

በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ።

3ዘመኔ እንደ ጢስ ተኖ አልቆአልና፤

ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል።

4ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቆአል፤

እህል መብላትም ዘንግቻለሁ።

5ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ፣

ዐጥንቴ ከቈዳዬ ጋር ተጣበቀ።

6የምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤

በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጒጒት ሆንሁ።

7ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤

በቤቴ ጒልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።

8ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይዘልፉኛል፤

የሚያክፋፉኝም ስሜን እንደ ርግማን ቈጥረውታል።

9ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤

መጠጤንም ከእንባ ጋር ቀላቅያለሁ።

10ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣

ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ።

11ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤

እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።

12እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤

ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

13ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤

ለእርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤

የተወሰነውም ጊዜ ደርሶአል።

14አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤

ለዐፈሯም ይሳሳሉ።

15ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣

የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።

16እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤

በክብሩም ይገለጣል።

17እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤

ልመናቸውንም አይንቅም።

18ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣

ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤

19እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቶአልና፤

ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቶአል፤

20ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣

ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”

21ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣

ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤

22ይህም፣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣

እግዚአብሔርን ለማምለክ በአንድነት ሲሰበሰቡ ይሆናል።

23ብርታቴን መንገድ ላይ ቀጨው፤102፥23 ወይም በኀይሉ ብርታቴን ቀጨው

ዕድሜዬንም ባጭሩ አስቀረው።

24እኔም እንዲህ አልሁ፤

“አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤

ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ።

25አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤

ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።

26እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤

ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤

እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤

እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ።

27አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤

ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።

28የአገልጋዮችህ ልጆች ተደላድለው ይኖራሉ፤

ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 102:1-28

第 102 篇

患难中的祈祷

受苦之人的祷告,在疲惫不堪时向耶和华的倾诉。

1耶和华啊,求你听我的祷告,

垂听我的呼求!

2我在危难的时候,

求你不要掩面不理我。

求你垂听我的呼求,

赶快应允我。

3我的年日如烟消散,

我全身如火焚烧。

4我的心被摧残,如草枯萎,

以致我不思饮食。

5我因哀叹而瘦骨嶙峋。

6我就像旷野中的鸮鸟,

又像废墟中的猫头鹰。

7我无法入睡,

我就像屋顶上一只孤伶伶的麻雀。

8我的仇敌终日辱骂我,

嘲笑我的用我的名字咒诅人。

9我以炉灰为食物,

眼泪拌着水喝,

10因为你向我大发烈怒,

把我抓起来丢在一边。

11我的生命就像黄昏的影子,

又如枯干的草芥。

12耶和华啊!唯有你永远做王,

你的大名万代长存。

13你必怜悯锡安

因为现在是你恩待她的时候了,时候到了。

14你的仆人们喜爱城中的石头,

怜惜城中的尘土。

15列国敬畏耶和华的名,

世上的君王都因祂的荣耀而战抖。

16因为耶和华必重建锡安

带着荣耀显现。

17祂必垂听穷人的祷告,

不藐视他们的祈求。

18要为后代记下这一切,

好让将来的人赞美耶和华。

19耶和华从至高的圣所俯视人间,

从天上察看大地,

20要垂听被囚之人的哀叹,

释放被判死刑的人。

21-22这样,万族万国聚集、敬拜

耶和华时,

人们必在锡安传扬祂的名,

耶路撒冷赞美祂。

23祂使我未老先衰,

缩短了我的岁月。

24我说:“我的上帝啊,

你世代长存,

求你不要叫我中年早逝。

25太初你奠立大地的根基,

亲手创造诸天。

26天地都要消亡,

但你永远长存。

天地都会像外衣渐渐破旧,

你必更换天地,如同更换衣服,

天地都要消逝。

27但你永远不变,

你的年日永无穷尽。

28你仆人的后代必生生不息,

在你面前安然居住。”