መዝሙር 10 NASV - 诗篇 10 CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 10:1-18

መዝሙር 1010፥0 ምዕ10 መዝ 9 እና 10 በመጀመሪያው የጥንት ቅጅ ላይ አንጓዎች ተከታታይ ፊደላት ባሉት የዕብራይስጥ ሆህያት የሚጀምሩ እንዲሁም ጅማሬው ወይም መጨረሻው ትርጒም ዐዘል የሆነ አንድ ወጥ ግጥም ነበር በሰብዓ ሊቃናት ውስጥ ሁለቱ አንድ መዝሙር ናቸው።

ለፍትሕ የቀረበ ልመና

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን እንዲህ ርቀህ ቆምህ?

በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ?

2ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤

በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ።

3ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤

ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል።

4ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤

በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤

5መንገዱ ዘወትር የተሳካ ነው፤

ዕቡይ፣ ከሕግህም የራቀ ነው።

በመሆኑም በጠላቶቹ ላይ ያፌዛል።

6በልቡም፣ “ከስፍራዬ የሚነቀንቀኝ የለም፤

ከትውልድ እስከ ትውልድም መከራ አያገኘኝም” ይላል።

7አፉ መርገምን፣ ቅጥፈትንና ግፍን የተሞላ ነው፤

ሽንገላና ክፋት ከምላሱ ሥር ይገኛሉ።

8በየመንደሩ ሥርቻ ያደፍጣል፤

ንጹሐንን በሰዋራ ስፍራ ይገድላል።

ዐይኖቹንም በምስኪኖች ላይ ያነጣጥራል።

9በደኑ ውስጥ እንዳለ አንበሳ በስውር ያደባል፤

ረዳት የሌለውን ለመያዝ ያሸምቃል፤

ድኻውንም አፈፍ አድርጎ በወጥመዱ ይጐትታል።

10ምስኪኑም ይደቃል፤ ዐንገቱን ይደፋል፤

ያልታደለውም በክንዱ ሥር ይወድቃል።

11በልቡም፣ “እግዚአብሔር ረስቶአል፤

ፊቱን ሸፍኖአል፤ ፈጽሞም አያይም”

ይላል።

12እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ አምላክ ሆይ፤ ክንድህን አንሣ፤

ረዳት የሌላቸውንም አትርሳ።

13ክፉ ሰው በእግዚአብሔር ላይ ለምን ክፉ ይናገራል?

በልቡስ፣ “ስለ ሥራዬ አይጠይቀኝም”

ለምን ይላል?

14አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤

በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤

ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤

ለድኻ ዐደግም ረዳቱ አንተ ነህ።

15የክፉውንና የበደለኛውን ክንድ ስበር፤

የእጁንም ስጠው፤

ምንም እስከማይገኝ ድረስ።

16እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ንጉሥ ነው፤

ሕዝቦችም ከምድሩ ይጠፋሉ።

17እግዚአብሔር ሆይ፤ የተገፉትን ምኞት ትሰማለህ፤

ልባቸውን ታበረታለህ፤ ጆሮህንም ወደ እነርሱ ጣል ታደርጋለህ፤

18ከዐፈር የተፈጠረ ሰው ከእንግዲህ

እንዳያስጨንቃቸው፣

አንተ ለድኻ ዐደጉና ለተገፋው ትሟገታለህ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 10:1-18

第 10 篇

求上帝惩治恶人

1耶和华啊,你为何远远站着?

为何在我遭难时隐藏起来?

2恶人狂妄地追逼穷苦人,

愿他们落入自己所设的圈套。

3恶人夸耀自己的贪欲,

贪婪的人憎恨、咒诅耶和华。

4他们狂傲自大,心中没有上帝,

从不寻求耶和华。

5他们凡事顺利,

对你的审判不屑一顾,

对所有的仇敌嗤之以鼻。

6他们自以为可以屹立不倒,

世世代代永不遭殃。

7他们满口咒诅、谎话和恐吓之言,

舌头沾满祸害和邪恶。

8他们埋伏在村庄,

暗中监视受害者,杀害无辜。

9他们像狮子埋伏在暗处,

猎取无助的人,

用网罗拖走他们。

10不幸的人被击垮,

倒在他们的暴力下。

11他们自言自语:“上帝忘记了,

祂掩面不理这些事!”

12耶和华啊,求你起来!

上帝啊,求你举手施罚,

不要忘记无助的人!

13恶人为何轻视上帝,

以为上帝不会追究呢?

14但你已看到世人的疾苦,

随时伸出援手。

困苦无助的人投靠你,

你是孤儿的帮助。

15求你打断恶人的臂膀,

彻底追究他们的罪恶。

16耶和华永永远远是君王,

列邦必从祂的土地上灭亡。

17耶和华啊,

你知道困苦人的愿望,

你必垂听他们的呼求,

安慰他们。

18你为孤儿和受欺压的人申冤,

使渺小的世人不能再恐吓他们。