New Amharic Standard Version

መክብብ 3:1-22

ለሁሉም ጊዜ አለው

1ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤

ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤

2ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤

ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤

3ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤

ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤

4ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤

ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤

5ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤

ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤

6ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤

ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤

7ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤

ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤

8ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤

ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።

9ሠራተኛ ከጥረቱ የሚያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? 10ሰዎች ይደክሙበት ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ከባድ የሥራ ጫና አየሁ። 11ሁሉንም ነገር በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ በሰዎችም ልብ ዘላለማዊነትን አኖረ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገውን ማወቅ አይችሉም። 12ለሰዎች፣ በሕይወት እያሉ ደስ ከመሰኘትና መልካምን ነገር ከማድረግ የተሻለ ነገር እንደሌለ ዐወቅሁ። 13ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፣ በሚደክምበትም ሁሉ ርካታን ያገኝ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ችሮታ ነው። 14እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘላለም እንደሚኖር ዐውቃለሁ፤ በእርሱ ላይ ምንም አይጨመርም፤ ከእርሱም ምንም አይቀነስም፤ ሰዎች ያከብሩት ዘንድ ይህን አደረገ።

15አሁን ያለው ከዚህ በፊት የነበረው ነው፤

ወደ ፊት የሚሆነውም ቀድሞ የነበረ ነው፤

እግዚአብሔርም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል3፥15 ወይም እግዚአብሔር ያለፈውን መልሶ ይጠራዋል

16ከፀሓይ በታችም ሌላ ነገር አየሁ፤

በፍርድ ቦታ ዐመፅ ነበር፤

በፍትሕ ቦታ ግፍ ነበር።

17እኔም በልቤ

“ለማንኛውም ድርጊት፣

ለማንኛውም ተግባር ጊዜ ስላለው፣

እግዚአብሔር ጻድቁንና ኀጢአተኛውን ወደ ፍርድ ያመጣቸዋል”

ብዬ አሰብሁ።

18እንዲህም ብዬ አሰብሁ፤ “ሰዎች፣ እንደ እንስሳት መሆናቸውን ያዩ ዘንድ እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል። 19የሰው ዕድል ፈንታ እንደ እንስሳት ነው፤ ሁለቱም ዕጣ ፈንታቸው አንድ ነው፤ አንዱ እንደሚሞት፣ ሌላውም እንዲሁ ይሞታል። ሁሉ አንድ ዐይነት እስትንፋስ3፥19 ወይም መንፈስ አላቸው፤ ሰውም ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነው። 20ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ፤ ሁሉም ከዐፈር እንደሆኑ፣ ተመልሰው ወደ ዐፈር ይሄዳሉ። 21የሰው መንፈስ ወደ ላይ መውጣቱን፣ የእንስሳ እስትንፋስ3፥21 ወይም የሰው መንፈስ ወደ ላይ እንደሚሄድ ወይም የእንስሳት መንፈስ ደግሞ ወደ ታች ወደ ምድር መውረዱን ማን ያውቃል?”

22ስለዚህ ለሰው ዕጣ ፈንታው ስለ ሆነ፣ በሥራው ከመደሰት የተሻለ ነገር እንደሌለው አየሁ፤ ከእርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ተመልሶ እንዲያይ የሚያደርገው ማን ነው?

Korean Living Bible

전도서 3:1-22

모든 것의 때

1세상의 모든 일은 다 정한 때와 기한이 있다:

2날 때와 죽을 때,

심을 때와 거둘 때,

3죽일 때와 치료할 때,

헐 때와 세울 때,

4울 때와 웃을 때,

슬퍼할 때와 춤출 때,

5돌을 던질 때와 돌을 모을 때,

포옹할 때와 포옹하지 않을 때,

6찾을 때와 잃을 때,

간직할 때와 던져 버릴 때,

7찢을 때와 꿰맬 때,

침묵을 지킬 때와 말할 때,

8사랑할 때와 미워할 때,

전쟁할 때와 평화로울 때가 있다.

9사람이 수고하여 실제로 얻는 것이 무엇인가?

10나는 하나님이 인간에게 지워 주신 무거운 짐을 보았다.

11하나님은 모든 것을 때를 따라 아름답게 만드시고 3:11 암시됨.사람에게 영원을 사모하는 마음을 주셨다. 그러나 사람은 하나님이 하시는 일을 처음부터 끝까지 이해할 수가 없다.

12그래서 나는 사람이 사는 동안 기뻐하고 선을 행하는 것보다 나은 것이 아무것도 없으며

13사람이 먹고 마시며 자기가 수고하는 모든 일에 만족을 느끼는 이것이 하나님의 선물임을 알게 되었다.

14하나님이 행하시는 모든 일은 영원히 남을 것이다. 거기에는 아무것도 더하거나 제할 수가 없다. 하나님이 이렇게 하시는 목적은 사람이 그를 두려운 마음으로 섬기도록 하기 위해서이다.

15지금 있는 일도 오래 전에 있었던 일이며 앞으로 일어날 일도 전에 다 있었던 일이다. 이와 같이 하나님은 지나간 일들이 반복해서 일어나게 하신다.

세상의 부정을 개탄함

16내가 보니 이 세상에는 잘못된 것이 많이 있다. 법정에도 악이 있고 반드시 정의가 실현되어야 하는 곳에도 악이 있다.

17나는 혼자 이런 생각을 하였다. “하나님은 의로운 자와 악인을 다 같이 심판하실 것이다. 이것은 모든 일과 사건이 일어날 때가 있기 때문이다.”

18나는 또 사람이 짐승과 다를 것이 없다는 것을 깨닫게 하려고 하나님이 인간을 시험하시는 사실도 알게 되었다.

19결국 사람이나 짐승에게는 같은 운명이 기다리고 있다. 이것이 죽으면 저것도 죽는다. 사람과 짐승은 다 같이 호흡하는 동물일 뿐 사람이 짐승보다 나은 것이 없으니 모든 것이 헛될 뿐이다.

20사람과 짐승은 다 같은 곳으로 가게 되는데 모두 흙에서 났으므로 흙으로 돌아간다.

21사람의 영은 위로 올라가고 짐승의 영은 땅 속으로 내려간다고 누가 입증할 수 있겠는가?

22그러므로 내가 보기에는 사람이 자기 일에 즐거움을 느끼는 것보다 더 좋은 것은 없으니 이것이 사람의 운명이기 때문이다. 죽은 후의 사건을 볼 수 있도록 사람을 다시 살릴 자가 누구인가?