New Amharic Standard Version

ሉቃስ 2:1-52

የኢየሱስ መወለድ

1በዚያን ዘመን፣ የዓለሙ ሁሉ ሕዝብ እንዲቈጠርና እንዲመዘገብ ከአውግስጦስ ቄሳር ትእዛዝ ወጣ። 2ይህም ቄሬኔዎስ የሶርያ ገዢ በነበረበት ጊዜ የተደረገ የመጀመሪያው የሕዝብ ቈጠራ ነበር። 3ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለመመዝገብ ወደየራሱ ከተማ ሄደ።

4ዮሴፍም ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ፣ በገሊላ አውራጃ ከምትገኘው ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ የዳዊት ከተማ ወደሆነችው፣ ቤተ ልሔም ወደምትባል ከተማ ወደ ይሁዳ ወጣ። 5ወደዚያም ለመመዝገብ የተጓዘው፣ የመውለጃ ጊዜዋ ከተቃረበው ከእጮኛው ከማርያም ጋር ነበር። 6በዚያም እንዳሉ የምትወልድበት ጊዜ ደረሰ፤ 7የበኵር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ በጨርቅም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማረፊያ ቦታ ስላላገኙ በግርግም አስተኛችው።

እረኞችና መላእክት

8በዚያው አገር በሌሊት መንጋቸውን ሲጠብቁ በሜዳ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ። 9የጌታም መልአክ ድንገት መጥቶ በአጠገባቸው ቆመ፤ የጌታም ክብር በዙሪያቸው አበራ፤ ታላቅም ፍርሀት ያዛቸው። 10መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች አምጥቼላችኋለሁና። 11ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀን ተወልዶላችኋልና፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ2፥11 ወይም መሲሕ፤ ክርስቶስ (በግሪክ) መሲሕ (በዕብራይስጥ) ማለት ሲሆን የሁለቱም ትርጒም የተቀባ ማለት ነው፤ እንዲሁም ቍ 26 ይመ ነው። 12ይህ ምልክት ይሁናችሁ፤ ሕፃን ልጅ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም ተኝቶ ታገኛላችሁ።”

13ድንገትም ብዙ የሰማይ ሰራዊት ከመልአኩ ጋር ታዩ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፣ እንዲህ አሉ፤

14“ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም፣ ሰላምም እርሱ

ለሚወዳቸው ሰዎች በምድር ይሁን!”

15መላእክቱ ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ ከወጡ በኋላ እረኞቹ፣ “ጌታ የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንድናይ ወደ ቤተ ልሔም እንሂድ” ተባባሉ።

16እነርሱም ፈጥነው ሄዱ፤ ማርያምንና ዮሴፍን፣ ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ። 17ካዩም በኋላ፣ ስለ ሕፃኑ የተነገራቸውን ገልጠው አወሩ። 18ይህንንም የሰሙ ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር ተደነቁ፤ 19ማርያም ግን ይህንን ሁሉ በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር። 20እረኞቹም ሁሉም ነገር እንደ ተነገራቸው ሆኖ በማግኘታቸው፣ ስለ ሰሙትና ስላዩት ሁሉ እግዚአብሔርን እያከበሩና እያመሰገኑ ተመለሱ።

ሕፃኑን ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት

21ስምንት ቀን ሆኖት የመገረዣ ጊዜው ሲደርስ፣ ከመፀነሱ በፊት መልአኩ ባወጣለት ስም ኢየሱስ ተባለ።

22በሙሴ ሕግ መሠረት፣ የመንጻታቸው ወቅት በተፈፀመ ጊዜ፣ ዮሴፍና ማርያም ሕፃኑን ለጌታ ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት ወጡ፤ 23ይኸውም በጌታ ሕግ፣ “ተባዕት የሆነ በኵር ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይሆናል” ተብሎ እንደ ተጻፈ ለመፈጸምና 24ደግሞም በጌታ ሕግ፣ “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ፣” መሥዋዕት ለማቅረብ ነበር።

25በዚያን ጊዜ ጻድቅና ትጒሕ የሆነ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ እርሱም የእስራኤልን መጽናናት የሚጠባበቅና መንፈስ ቅዱስ በላዩ ያደረሰው ነበር። 26ደግሞም የጌታን መሲሕ ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር፤ 27እርሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ የልጁም ወላጆች በሕጉ ልማድ መሠረት ተገቢውን ሊፈጽሙለት ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘው በገቡ ጊዜ፣ 28ስምዖን ተቀብሎ ዐቀፈው፤ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እንዲህ አለ፤

29“ጌታ ሆይ፤ ቃል በገባኸው መሠረት፣

አሁን ባሪያህን በሰላም አሰናብተው፤

30ዐይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን፣

31ማዳንህን አይተዋልና።

32ይህም ለአሕዛብ መገለጥን የሚሰጥ ብርሃን፣

ለሕዝብህ ለእስራኤልም ክብር ነው።”

33አባቱና እናቱም ስለ እርሱ በተነገረው ነገር ተገረሙ። 34ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “ይህ ሕፃን በእስራኤል ለብዙዎች መነሣትና መውደቅ ምክንያት እንዲሆን፣ ደግሞም ክፉ ለሚያስወሩበት ምልክት እንዲሆን ተወስኖአል፤ 35የብዙዎችም የልብ ሐሳብ የተገለጠ እንዲሆን፣ የአንቺም ነፍስ ደግሞ በሰይፍ ይወጋል።”

36ደግሞም ከአሴር ወገን የሆነች የፋኑኤል ልጅ፣ ሐና የምትባል ነቢይት በዚያ ነበረች፤ እርሷም በጣም አርጅታ ነበር፤ በድንግልናዋ ካገባችው ባሏም ጋር ሰባት ዓመት የኖረች ነበረች፤ 37ዕድሜዋም ሰማንያ አራት ዓመት2፥37 ወይም ለሰማንያ አራት ዓመት መበለት የነበረች እስኪሆናት ድረስ ቀንና ሌሊት ከቤተ መቅደስ ሳትለይ፣ በጾምና በጸሎት የምታገለግል መበለት ሆና ቈየች። 38በዚያኑም ጊዜ ቀርባ እግዚአብሔርን አመሰገነች፤ የኢየሩሳሌምንም መቤዠት ለሚጠባበቁ ሁሉ ስለ ሕፃኑ ተናገረች።

39ዮሴፍና ማርያም በጌታ ሕግ የታዘዘውን ሁሉ ከፈጸሙ በኋላ፣ በገሊላ አውራጃ ወዳለችው ከተማቸው ወደ ናዝሬት ተመለሱ። 40ሕፃኑም እያደገና እየጠነከረ ሄደ፤ በጥበብ ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።

ኢየሱስ በዐሥራ ሁለት ዓመቱ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ

41ወላጆቹም በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር። 42ልጁም ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ፣ እንደተለመደው ወደ በዓሉ ወጡ። 43በዓሉን ከፈጸሙ በኋላ፣ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፣ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀረ፤ ወላጆቹ ግን መቅረቱን አላወቁም ነበር። 44አብሮአቸው ያለ መስሎአቸው፣ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፤ በኋላ ግን ከዘመዶቻቸውና ከወዳጆቻቸው ዘንድ ይፈልጉት ጀመር፤ 45ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

46ከሦስት ቀንም በኋላ፣ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲያዳምጣቸውና ጥያቄ ሲያቀርብላቸው በቤተ መቅደስ ውስጥ አገኙት፤ 47የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይደነቁ ነበር። 48ወላጆቹም ባዩት ጊዜ ተገረሙ፤ እናቱም፣ “ልጄ ሆይ፤ ለምን እንዲህ አደረግኸን? አባትህና እኔኮ ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር” አለችው።

49እርሱም፣ “ለምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት መገኘት እንደሚገባኝ አላወቃችሁምን?” አላቸው። 50እነርሱ ግን የተናገራቸው ነገር አልገባቸውም።

51ከዚያም አብሮአቸው ወደ ናዝሬት ወረደ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ሁሉ ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር። 52ኢየሱስም በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት አደገ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

路加福音 2:1-52

耶穌降生伯利恆

1那時,凱撒奧古斯都頒下諭旨,命羅馬帝國的人民都辦理戶口登記。 2這是第一次戶口登記,正值居里紐敘利亞總督。 3大家都回到本鄉辦理戶口登記。 4約瑟因為是大衛家族的人,就從加利利拿撒勒鎮趕到猶太地區大衛的故鄉伯利恆5要和已許配給他、懷著身孕的瑪麗亞一起登記。 6他們抵達目的地時,瑪麗亞產期到了, 7便生下第一胎,是個兒子。她用布把孩子裹好,安放在馬槽裡,因為旅店沒有房間了。

牧羊人和天使

8當晚,伯利恆郊外有一群牧羊人正在看守羊群。 9忽然,主的天使向他們顯現,主的榮光四面照著他們,他們非常害怕。 10天使對他們說:「不要怕!我告訴你們一個有關萬民的大喜訊, 11今天在大衛的城裡有一位救主為你們降生了,祂就是主基督! 12你們將看見一個嬰孩包著布躺在馬槽裡,這就是給你們的記號。」

13忽然,有一大隊天軍出現,與那天使一同讚美上帝說:

14「在至高之處,

願榮耀歸於上帝!

在地上,

願平安臨到祂所喜悅的人!」

15眾天使離開他們升回天上之後,牧羊人便商議說:「我們現在去伯利恆,察看一下主剛才告訴我們的那件事吧!」 16他們就連忙進城,找到了瑪麗亞約瑟以及躺在馬槽裡的嬰孩。 17他們看過之後,就把天使告訴他們有關這嬰孩的事傳開了。 18聽見的人都對牧羊人的話感到驚訝。

19瑪麗亞把這些事牢記在心裡,反覆思想。 20牧羊人在歸途中不斷地將榮耀歸於上帝,讚美祂,因為他們的所見所聞跟天使告訴他們的一樣。

奉獻聖嬰

21在第八天,嬰孩接受了割禮,祂的名字叫耶穌,是瑪麗亞懷孕前天使取的。

22摩西律法規定的潔淨期滿後,約瑟瑪麗亞把嬰孩帶到耶路撒冷去獻給主, 23因為主的律法規定:必須把長子分別出來獻給主。 24他們又按照主的律法獻上祭物,即一對斑鳩或兩隻雛鴿。 25耶路撒冷有一位公義敬虔、有聖靈同在的人名叫希緬,他一直期待著以色列的安慰者到來。 26聖靈曾啟示他:他去世前必能親眼看見主所立的基督。

27一天,他受聖靈感動進入聖殿,看見約瑟瑪麗亞抱著嬰孩耶穌進來,要依照律法的規定為祂行奉獻禮, 28就把祂抱過來,稱頌上帝說:

29「主啊,現在你的話已經成就,

可以讓你的奴僕安然離世了,

30因為我已親眼看到你的救恩,

31就是你為萬民所預備的救恩。

32這救恩是啟示外族人的光,

也是你以色列子民的榮耀。」

33約瑟瑪麗亞聽見這番話,感到驚奇。 34希緬給他們祝福後,就對孩子的母親瑪麗亞說:「看啊,這孩子必使以色列許多人跌倒、許多人興起。祂將成為眾人攻擊的對象, 35好叫許多人的心思意念暴露出來,你自己則會心如刀割。」

36-37亞設支派中有一位八十四歲高齡的女先知名叫亞拿,是法內利的女兒,婚後七年便開始守寡,之後一直住在聖殿裡,禁食禱告,日夜事奉上帝。 38正在那時,她也前來感謝上帝,並把耶穌的事報告給所有盼望耶路撒冷蒙救贖的人。

39約瑟瑪麗亞辦完了主的律法規定的一切事之後,就回到他們的家鄉——加利利拿撒勒40耶穌漸漸長大,身心強健,充滿智慧,上帝的恩典與祂同在。

少年耶穌聖殿論道

41約瑟瑪麗亞每年都上耶路撒冷去過逾越節。 42耶穌十二歲那年,跟父母照例上去過節。 43節期完了,約瑟瑪麗亞便啟程回家,他們並不知道少年耶穌仍然留在耶路撒冷44還以為祂跟在同行的人中間。他們走了一天的路後,才開始在親戚朋友中找祂, 45結果沒有找到,只好回到耶路撒冷46三天後,他們才在聖殿裡找到耶穌,祂正和教師們坐在一起,一邊聽一邊問問題。 47祂的知識和對答令聽見的人感到驚奇。 48約瑟瑪麗亞看見耶穌在那裡,大為驚奇。

瑪麗亞對祂說:「兒子,你為什麼這樣對我們呢?你父親和我急得到處找你!」

49耶穌對他們說:「你們為什麼找我呢?難道你們不知道我應該在我父的家嗎?」 50但他們不明白祂在講什麼。

51於是,耶穌隨父母回到拿撒勒,並順從他們。瑪麗亞把這一切事牢記在心。 52耶穌漸漸長大,智慧與日俱增,越來越受上帝和人們的喜愛。