New Amharic Standard Version

ሉቃስ 11:1-54

ኢየሱስ ያስተማረው ጸሎት

11፥2-4 ተጓ ምብ – ማቴ 6፥9-13

11፥9-13 ተጓ ምብ – ማቴ 7፥7-11

1አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም እንደ ጨረሰ፣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ “ጌታ ሆይ፤ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው አንተም መጸለይን አስተምረን” አለው።

2እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፤

“ ‘አባታችን11፥2 አንዳንድ ቅጆች በሰማይ የምትኖር አባታችን ይላሉ ሆይ፤

ስምህ ይቀደስ፤

መንግሥትህ ትምጣ፤11፥2 አንዳንድ ቅጆች ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን ይላሉ

3የዕለት እንጀራችንን በየዕለቱ ስጠን፤

4በደላችንን ይቅር በለን፤

እኛም የበደሉንን11፥4 አንዳንድ ቅጆች በእኛ ላይ ኀጢአት የሠሩትን ይላሉ። ሁሉ ይቅር ብለናልና።

ወደ ፈተናም አታግባን፤ ከክፉው አድነን እንጂ።”11፥4 አንዳንድ ቅጆች ከክፉው አድነን እንጂ የሚለው የላቸውም።

5ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ከእናንተ አንዱ ወዳጅ ቢኖረውና በእኩለ ሌሊት ወደ እርሱ ሄዶ፣ ‘ወዳጄ ሆይ፤ ሦስት እንጀራ አበድረኝ፤ 6አንድ ባልንጀራዬ ከመንገድ መጥቶብኝ የማቀርብለት ምንም ነገር የለኝምና’ ብሎ ለመነው እንበል።

7“በቤት ውስጥ ያለውም፣ ‘አታስቸግረኝ፤ በሩ ተቈልፎአል፤ ልጆቼም አብረውኝ ተኝተዋል፤ ከእንግዲህ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም’ ይለዋልን? 8እላችኋለሁ፤ ወዳጁ በመሆኑ ተነሥቶ ባይሰጠው እንኳ፣ ስለ ንዝነዛው11፥8 ወይም ስለ ብዙ ልመናው ብቻ የሚፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል።

9“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ 10ምክንያቱም የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ በር ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።

11“ከእናንተ መካከል አባት ሆኖ ሳለ ልጁ11፥11 አንዳንድ ቅጆች ዳቦ ቢለምነው ድንጋይ የሚሰጠው አለን? የሚል አላቸው። ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጠው ይኖራልን? 12ወይስ ዕንቊላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? 13እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳላችሁ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁበት፣ የሰማዩ አባታችሁ ታዲያ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጥ!”

ጌታ ኢየሱስና ብዔልዜቡል

11፥14-15፡17-22፡24-26 ተጓ ምብ – ማቴ 12፥22፡24-29፡43-45

11፥17-22 ተጓ ምብ – ማር 3፥23-27

14አንድ ቀን ኢየሱስ ድዳ ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣለት በኋላ ድዳው ሰው ተናገረ፤ ሕዝቡም ተገረመ። 15አንዳንዶቹ ግን፣ “በአጋንንት አለቃ፣ በብዔልዜቡል11፥15 ግሪኩ ብዔዜቡል ወይም ብዔል ዜብል ይላል፤ እንዲሁም ቍ 18፡19 ይመ፣ አጋንንትን ያወጣል” አሉ፤ 16አንዳንዶቹ ደግሞ ሊፈታተኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ከእርሱ ይፈልጉ ነበር።

17ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ የሚለያይ ቤትም ይወድቃል። 18ሰይጣንም እርስ በርሱ ከተከፋፈለ፣ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? አጋንንትን በብዔልዜቡል እንደማወጣ ትናገራላችሁና። 19እንግዲህ እኔ አጋንንትን የማወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ልጆቻችሁ በማን ያወጧቸው ይሆን? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። 20እኔ ግን አጋንንትን የማወጣው በእግዚአብሔር ጣት ከሆነ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ መጣች ዕወቁ።

21“ብርቱ ሰው በሚገባ ታጥቆ ቤቱን ከጠበቀ፣ ንብረቱ በሰላም ይቀመጣል። 22ነገር ግን ይበልጥ ብርቱ የሆነ ሰው መጥቶ ካጠቃውና ካሸነፈው ታምኖበት የነበረውን ትጥቁን ያስፈታዋል፤ ምርኮውንም ወስዶ ለሌሎች ያካፍላል።

23“ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብም ይበትናል።

24“ርኵስ11፥24 ወይም ክፉ መንፈስ ከሰው ሲወጣ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ ሳያገኝም ሲቀር፣ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፤ 25ሲመለስም ቤቱ ተጠራር ጐና ተስተካክሎ ያገኘዋል። 26ከዚያም በኋላ ሄዶ ሌሎች ከእርሱ የከፉ ሰባት አጋንንት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውበትም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያ ሰው ከመጀመሪያው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታ የከፋ ይሆንበታል።

27ኢየሱስ ይህን እየተናገረ እያለ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፣ “የተሸከመችህ ማሕፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው” አለችው።

28እርሱ ግን፣ “ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚታዘዙት ናቸው” አለ።

የዮናስ ምልክትነት

11፥29-32 ተጓ ምብ – ማቴ 12፥39-42

29ብዙ ሕዝብ እየተሰበሰበ በሄደ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ይህ ትውልድ ክፉ ነው፤ ታምራዊ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከዮናስ ምልክት በስተቀር ሌላ አይሰጠውም። 30ምክንያቱም ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደሆናቸው የሰው ልጅም ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል። 31የደቡቧ ንግሥት በፍርድ ጊዜ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድባቸዋለች፤ እርሷ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆ፤ ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ። 32የነነዌ ሰዎችም በፍርድ ጊዜ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ እነርሱ የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆ፣ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።

የሰውነት መብራት

11፥34፡35 ተጓ ምብ – ማቴ 6፥22፡23

33“መብራት አብርቶ በስውር ቦታ ወይም ከእንቅብ በታች የሚያስቀምጥ ማንም የለም፤ ይልቁን የሚገቡ ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል። 34የሰውነትህ ብርሃን ዐይንህ ናት፤ ዐይንህ ጤናማ ስትሆን መላ ሰውነትህ ብሩህ ይሆናል፤ ዐይንህ ታማሚ ከሆነች ግን መላ ሰውነትህ የጨለመ ይሆናል። 35ስለዚህ በውስጥህ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። 36እንግዲህ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ከሆነና የጨለመ የሰውነት ክፍል ከሌለበት፣ የሰውነትህ ሁለንተና መብራት በወገግታው ያበራልህ ያህል ይደምቃል።”

ስድስት ዐይነት ወዮታ

37ኢየሱስ ንግግሩን እንደ ጨረሰ፣ አንድ ፈሪሳዊ ከእርሱ ጋር ምግብ እንዲበላ ጋበዘው፤ እርሱም አብሮት ገብቶ በማእድ ተቀመጠ። 38ፈሪሳዊውም ኢየሱስ ከምግብ በፊት እጁን እንዳልታጠበ ባየ ጊዜ ተደነቀ።

39ጌታም እንዲህ አለው፤ “አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጫዊ ክፍል ታጸዳላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን በስስትና በክፋት የተሞላ ነው። 40እናንት ሞኞች፤ የውጪውን የፈጠረ የውስጡንም አልፈጠረምን? 41ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት11፥41 ወይም ያላችሁን አድርጋችሁ ስጡ፤ በዚህ ጊዜ ሁሉም ንጹሕ ይሆንላችኋል።

42“እናንት ፈሪሳውያን ግን ወዮላችሁ፤ ከአዝሙድና ከጤና አዳም እንዲሁም ከአትክልት ሁሉ ዐሥራት ታወጣላችሁ፤ ሆኖም ፍትሕንና እግዚአብሔርን መውደድ ቸል ትላላችሁ፤ ነገር ግን ያንን ሳትተዉ ይኸኛውን ማድረግ በተገባችሁ ነበር።

43“እናንት ፈሪሳውያን ወዮላችሁ፤ በምኵራብ የክብር መቀመጫ፣ በገበያ መካከልም እጅ መነሣትን ትወዳላችሁና።

44“ሰዎች ሳያውቁ በላዩ የሚሄዱበትን የተሰወረ መቃብር ስለምትመስሉ፣ ወዮላችሁ።”

45ከሕግ ዐዋቂዎች አንዱ መልሶ “መምህር ሆይ፤ እንዲህ ስትናገር እኮ እኛንም መስደብህ ነው” ሲል መለሰለት።

46ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “እናንት ሕግ ዐዋቂዎችም ደግሞ ወዮላችሁ፤ ሰዎች ሊሸከሙ የማይችሉትን ከባድ ሸክም ታሸክማላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ ግን በጣታችሁ እንኳ አትነኵትም።

47“አባቶቻችሁ የገደሏቸውን የነቢያትን መቃብር ስለምታበጃጁ፣ ወዮላችሁ፤ 48እንግዲህ የአባቶቻችሁን ሥራ የምታጸኑ ምስክሮች ናችሁ፤ እነርሱ ነቢያትን ገደሉ፣ እናንተም መቃብራቸውን ታበጃጃላችሁ። 49ስለዚህም የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፤ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን እልክላቸዋለሁ፤ እነርሱ አንዳንዶቹን ይገድላሉ፤ ሌሎችንም ያሳድዳሉ።’ 50ስለዚህ ይህ ትውልድ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ስለ ፈሰሰው፣ ስለ ነቢያት ሁሉ ደም ተጠያቂ ነው፤ 51ከአቤል ደም ጀምሮ፣ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ መካከል እስከ ፈሰሰው እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ ይፈለግበታል፤ አዎን፣ እላችኋለሁ፤ ይህ ትውልድ ለዚህ ተጠያቂ ነው።

52“እናንት ሕግ ዐዋቂዎች ወዮላችሁ፤ የዕውቀትን መክፈቻ ነጥቃችሁ ወስዳችኋልና፤ እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁበትም፤ የሚገቡትንም ከልክላችኋል።”

53ኢየሱስ ከዚያ ከወጣ በኋላ፣ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ክፉኛ ይቃወሙትና በጥያቄም ያዋክቡት ጀመር፤ 54ከአፉ በሚወጣውም ቃል ሊያጠምዱት ያደቡ ነበር።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

路加福音 11:1-54

教導門徒禱告

1有一天,耶穌在某地禱告完畢,有個門徒對祂說:「主啊,請教導我們禱告,像約翰教他的門徒一樣。」

2耶穌對他們說:「你們應該這樣禱告,

『天父,願人都尊崇你的聖名,

願你的國度降臨,

願你的旨意在地上成就,

就像在天上成就一樣11·2 有古卷無「願你的旨意在地上成就,就像在天上成就一樣」。

3願你天天賜給我們日用的飲食。

4求你饒恕我們的罪,

因為我們也饒恕那些虧欠我們的人。

不要讓我們遇見誘惑,

拯救我們脫離那惡者11·4 有古卷無「拯救我們脫離那惡者」。。』」

5耶穌又對他們說:「假設你在半夜跑去朋友家請求說,『朋友,請借給我三個餅吧, 6因為有一位朋友遠道而來,我家沒有什麼可以招待他。』 7那個人在屋裡應聲說,『請別打攪我,門已經鎖上了,我和孩子們也已經上床了,我不能起來給你拿餅。』

8「我告訴你們,那人雖不念朋友之情,但是倘若你不肯甘休,繼續請求,他最終會起來滿足你的願望。

9「我告訴你們,祈求,就會給你們;尋找,就會尋見;叩門,就會給你們開門。 10因為凡祈求的,就得到;尋找的,就尋見;叩門的,就給他開門。

11「你們中間做父親的,如果孩子要餅,你會給他石頭嗎?11·11 有古卷無「如果孩子要餅,你會給他石頭嗎?」要魚,你會給他蛇嗎? 12要雞蛋,你會給他蠍子嗎? 13你們雖然邪惡,尚且知道把好東西給兒女,天父豈不更要賜聖靈給那些求祂的人嗎?」

耶穌和別西卜

14有一次,耶穌趕出一個使人啞巴的鬼。鬼一出去,啞巴就能說話了,大家都很驚奇。 15有人卻說:「祂是靠鬼王別西卜趕鬼。」 16還有些人想試探耶穌,要求祂行個神蹟證明自己是上帝派來的。

17耶穌知道他們的心思,就說:「一個國內部自相紛爭,必然滅亡;一個家內部自相紛爭,必然崩潰。 18同樣,若撒旦內部自相紛爭,牠的國怎能維持呢?你們說我是靠別西卜趕鬼, 19若我是靠別西卜趕鬼,你們的子弟又是靠誰趕鬼呢?因此,他們要審判你們。 20但若我是靠上帝的能力趕鬼,就是上帝的國已降臨在你們中間了。

21「壯漢全副武裝地看守自己的住宅,他的財物會很安全。 22但是,來了一個比他更強壯的人,把他制伏後,奪去他所依靠的武裝,並把他搶來的東西分給了人。 23誰不與我為友,就是與我為敵;誰不和我一起收聚,就是故意拆散。

24「有個污鬼離開了牠以前所附的人,在乾旱無水之地四處遊蕩,尋找安歇之處,卻沒有找到。於是牠說,『我要回到老地方。』 25牠回去後,看見裡面打掃得又乾淨又整齊, 26就去帶來了七個比自己更邪惡的鬼一起住在那裡。那人的下場比從前更慘了。」

誰更有福

27耶穌說話的時候,人群中有個婦人高喊:「生你養你的人真有福啊!」

28耶穌回答說:「但那聽了上帝的話又去遵行的人更有福。」

可悲的邪惡世代

29這時聚集的人越來越多,耶穌說:「這是一個邪惡的世代,人們只想看神蹟,但除了約拿的神蹟以外,再沒有神蹟給他們看。 30正如約拿成了尼尼微人的神蹟,人子也要成為這世代的神蹟。

31「在審判的日子,南方的女王和這世代的人都要起來11·31 起來」或作「復活」,下同32節。,她要定這個世代的罪,因為她曾不遠千里來聽所羅門王的智言慧語。看啊!這裡有一位比所羅門王更偉大。

32「在審判的日子,尼尼微人和這世代的人都要起來,尼尼微人要定這個世代的罪,因為他們聽到約拿的宣告,就悔改了。看啊!這裡有一位比約拿更偉大。

燈的比喻

33「沒有人點了燈卻將它放在地窖裡或斗底下,人總是把燈放在燈臺上,讓進來的人可以看見光。 34你的眼睛就是身體的燈,你的眼睛明亮,全身就光明;你的眼睛昏花,全身就黑暗。 35因此要小心,不要讓你心裡的光變為黑暗。 36如果你全身光明、毫無黑暗,你整個人就熠熠生輝,好像有燈光照在你身上。」

譴責法利賽人

37耶穌說完這番話後,有一個法利賽人來請祂吃飯,祂便應邀入席。 38這位法利賽人看見耶穌飯前沒有行猶太人洗手的禮儀,十分詫異。 39主對他說:「你們法利賽人洗淨杯盤的外面,你們裡面卻充滿了貪婪和邪惡。 40愚蠢的人啊,人裡外不都是上帝所創造的嗎? 41只要你們發自內心地去施捨,一切對你們都是潔淨的。

42「法利賽人啊,你們有禍了!你們將薄荷、茴香、各樣蔬菜獻上十分之一,卻忽略了上帝的公義和仁愛。後者是你們本該做的,前者也不可忽略。

43「法利賽人啊,你們有禍了!你們喜歡在會堂裡坐首位,又喜歡在街市上聽到別人的問候。 44你們有禍了!因為你們就像沒有墓碑的墳墓,人們從上面走過也不知道。」

譴責律法教師

45一位律法教師對耶穌說:「老師,你這話把我們也侮辱了!」

46耶穌回答說:「你們這些律法教師也有禍了!你們把沉重難負的擔子放在別人肩上,自己卻連一根指頭也不肯動。

47「你們有禍了,你們為先知修造墳墓,而他們正是被你們祖先殺害的! 48所以你們是見證人,你們讚同祖先的行為,因為他們殺了先知,你們為先知造墳墓。 49因此,充滿智慧的上帝說,『我要差遣先知和使徒到他們那裡,有些要被殺害,有些要遭迫害』, 50-51使創世以來,自亞伯一直到在祭壇和聖所之間被殺的撒迦利亞等眾先知的血債,都由這個世代承擔。我實在告訴你們,這些罪責都要由這個世代承擔。

52「律法教師啊,你們有禍了!你們拿走了知識的鑰匙,自己不進去,還阻擋那些正要進去的人。」

53耶穌離開那裡後,法利賽人和律法教師開始激烈地反對祂,用各種問題刁難祂, 54伺機找把柄陷害祂。