New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 4:1-26

ቃየንና አቤል

1አዳም ሚስቱን ሔዋንን ተገናኛት፤ እርሷም ፀንሳ ቃየንን4፥1 ቃየን የሚለው ስም ማምጣት ወይም ማግኘት የሚል ትርጒም ካላቸው የዕብራይስጥ ቃላት ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው ወለደች፤ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ርዳታ ወንድ ልጅ አገኘሁ” አለች። 2ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች።

አቤል የበግ እረኛ፣ ቃየንም ዐራሽ ነበር። 3በአንድ ወቅት፣ ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሥዋዕት አቀረበ። 4አቤልም መጀመሪያ ከተወለዱት በጎች መካከል ስባቸውን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤ 5በቃየንና በመሥዋዕቱ ግን አልተደሰተም፤ ስለዚህ ቃየን ክፉኛ ተናደደ፤ ፊቱም ጠቈረ።

6እግዚአብሔር አምላክም (ያህዌ ኤሎሂም) ቃየንን እንዲህ አለው፤ “ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቈረ? 7መልካም ብታደርግ ተቀባይነትን አታገኝምን? መልካም ባታደርግ ግን፣ ኀጢአት በደጅህ እያደባች ናት፤ ልታሸንፍህ ትፈልጋለች፤ አንተ ግን ተቈጣጠራት።”

8ቃየንም ወንድሙን አቤልን፣ “እስቲ ና፤ ወደ መስኩ እንውጣ”4፥8 እስቲ ና፣ ወደ መስኩ እንውጣ የሚለው ሐረግ በኦሪተ ሳምራውያን፣ በሰብዓ ሊቃናት፣ በቩልጌትና፣ በሱርስት የሚገኝ ሲሆን በማሶሬቲክ ጽሑፍ ውስጥ ግን የለም አለው፤ በመስኩም ሳሉ፣ ቃየን ወንድሙን አቤልን አጠቃው፤ ገደለውም።

9ከዚያም፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ቃየንን፣ “ወንድምህ አቤል የት ነው?” አለው።

ቃየንም፣ “አላውቅም፤ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” ሲል መለሰ።

10እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “ምንድ ነው ያደረግኸው? ስማ! የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። 11እንግዲህ የተረገምህ ነህ፤ የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፏን ከከፈተችው መሬት ትሰደዳለህ። 12ብታርሳትም ፍሬዋን አትለግስህም፤ በምድር ላይ ኰብላይና ተንከራታች ትሆናለህ።” 13ቃየንም እግዚአብሔርን (ያህዌ) እንዲህ አለው፤ “ቅጣቴ ልሸከመው ከምችለው በላይ ነው። 14እነሆ፤ ዛሬ ከምድሪቱ አባረርኸኝ፤ ከፊትህም እሸሸጋለሁ፤ በምድር ላይ ኰብላይና ተንከራታች እሆናለሁ፤ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል።”

15እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን፣ “የለም! እንደርሱ አይሆንም፤4፥15 ዕብራይሰጡ ከሰብዓ ሊቃናት፣ ከቩልጌትና ከሱርስቱ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን መልካም! ይለዋል ማንም ቃየንን ቢገድል፣ ሰባት ዕጥፍ የበቀል ቅጣት ይቀበላል” አለው፤ ስለዚህ፣ ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው እግዚአብሔር (ያህዌ) በቃየን ላይ ምልክት አደረገለት። 16ቃየንም ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወጥቶ ሄዶ፣ ከዔድን በስተ ምሥራቅ በምትገኝ ኖድ4፥16 ኖድ ማለት መቅበዝበዝ ማለት ለው (ቍ 12 እና 14 ይመ) በተባለች ምድር ተቀመጠ።

17ቃየን ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ፀንሳ ሄኖክን ወለደች። ቃየን የቈረቈረውን ከተማ በልጁ ስም ሄኖክ ብሎ ጠራው። 18ሄኖክ ኢራድን ወለደ፤ ኢራድም መሑያኤልን፣ መሑያኤልም ማቱሣኤልን፣ ማቱሣኤልም ላሜሕን ወለደ።

19ላሜሕ ሁለት ሚስቶች አገባ፤ የአንደኛዋ ስም ዓዳ፣ የሁለተኛዋም ጺላ ነበር። 20ዓዳ ያባልን ወለደች፤ እርሱም በድንኳን ለሚኖሩ ከብት አርቢዎች አባት ነበረ። 21ወንድሙም ዩባል ይባላል፤ እርሱም የበገና ደርዳሪዎችና የዋሽንት ነፊዎች አባት ነበረ። 22ሴላም ደግሞ ቱባልቃይን የተባለ ወንድ ልጅ ነበራት፤ እርሱም ከብረትና ከናስ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እየቀረጸ የሚሠራ4፥22 ወይም ለሚሠሩት ሁሉ መመሪያ የሚሠጥ ነበር። የቱባልቃይን እኅት ናዕማ ትባል ነበር።

23ላሜሕ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤

“ዓዳና ጺላ ሆይ ስሙኝ፤

የላሜሕ ሚስቶች ሆይ አድምጡኝ፤

አንድ ሰው ቢያቈስለኝ፣

ጒልማሳው ቢጐዳኝ፣ ገደልሁት፤4፥23 ወይም እገድላለሁ

24ቃየንን የሚገድል ሰባት ጊዜ ቅጣት ካገኘው፣

የላሜሕ ገዳይማ ሰባ ሰባት ጊዜ ቅጣት ያገኘዋል።”

25አዳም እንደ ገና ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር (ያህዌ) ምትክ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ሴት4፥25 ሴት ማለት ሰጠ ሳይሆን አይቀርም ብላ ጠራችው። 26ለሴትም ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት፤ ስሙንም ሄኖስ አለው።

በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም መጥራት4፥26 ወይም ማወጅ ጀመሩ።

Thai New Contemporary Bible

ปฐมกาล 4:1-26

คาอินกับอาแบล

1อาดัม4:1 หรือชายผู้นั้นได้ร่วมหลับนอนกับเอวา นางก็ตั้งครรภ์และคลอดบุตรชายชื่อคาอิน4:1 คำว่าคาอินมีเสียงคล้ายคำภาษาฮีบรูที่มีความหมายว่าได้มาหรือได้รับ นางกล่าวว่า “ฉันได้ลูกชายคนนี้มาโดยความช่วยเหลือขององค์พระผู้เป็นเจ้า2ภายหลังนางให้กำเนิดน้องชายของเขาคือ อาแบล

อาแบลเลี้ยงสัตว์ ส่วนคาอินทำไร่ไถนา 3เมื่อถึงฤดูเก็บเกี่ยว คาอินนำพืชผลจากไร่นามาถวายองค์พระผู้เป็นเจ้า 4ส่วนอาแบลนำไขมันของลูกสัตว์หัวปีที่ดีที่สุดในฝูงสัตว์ของเขามาถวายแด่องค์พระผู้เป็นเจ้าองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงโปรดปรานอาแบลและเครื่องถวายของเขา 5แต่ไม่ได้ทรงโปรดปรานคาอินและเครื่องถวายของเขา คาอินจึงโกรธนักและชักสีหน้า

6แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับคาอินว่า “เจ้าโกรธทำไม? เจ้าชักสีหน้าทำไม? 7หากเจ้าทำสิ่งที่ถูกที่ควร เจ้าก็จะเป็นที่ยอมรับไม่ใช่หรือ? แต่หากเจ้าไม่ทำสิ่งที่ถูกต้อง บาปก็หมอบอยู่ที่ประตูคอยเล่นงานเจ้า แต่เจ้าจะต้องชนะบาปให้ได้”

8ฝ่ายคาอินชวนอาแบลน้องชายของเขาว่า “เราไปที่ทุ่งนากันเถอะ”4:8 ฉบับ MT. ไม่มีประโยคที่ว่า“เราไปที่ทุ่งนากันเถอะ” ขณะอยู่ด้วยกันที่นั่น คาอินก็ทำร้ายและฆ่าอาแบลน้องชายของเขา

9องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสถามคาอินว่า “อาแบลน้องชายของเจ้าอยู่ที่ไหน?”

เขาตอบว่า “ข้าพระองค์ไม่ทราบ ข้าพระองค์เป็นผู้ดูแลน้องชายหรือ?”

10องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า “เจ้าทำอะไรลงไป! ฟังให้ดี โลหิตของน้องชายเจ้าร้องขึ้นจากแผ่นดินมาถึงเรา 11บัดนี้เจ้าถูกสาปแช่งและขับออกจากแผ่นดินซึ่งรองรับโลหิตของน้องชายของเจ้าเพราะน้ำมือของเจ้า 12เมื่อเจ้าไถพรวนดิน มันจะไม่ให้ผลผลิตแก่เจ้าอีกต่อไป เจ้าจะเป็นคนร่อนเร่พเนจรไปในโลก”

13คาอินทูลองค์พระผู้เป็นเจ้าว่า “โทษทัณฑ์นี้ใหญ่หลวงเกินกว่าข้าพระองค์จะรับได้ 14ในวันนี้พระองค์ทรงขับไล่ข้าพระองค์ไปจากแผ่นดินนี้ และทรงปิดกั้นข้าพระองค์จากพระพักตร์ของพระองค์ ข้าพระองค์จะเป็นคนร่อนเร่พเนจรไปในโลก ใครพบเห็นก็จะฆ่าข้าพระองค์”

15แต่องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับเขาว่า “ไม่ใช่เช่นนั้น ถ้าผู้ใดฆ่าคาอิน จะถูกเอาคืนเจ็ดเท่า” แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงทำเครื่องหมายไว้ที่ตัวคาอินเพื่อไม่ให้ผู้ที่พบเข้าฆ่าเขา 16ดังนั้นคาอินจึงออกไปจากเบื้องหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้าและตั้งถิ่นฐานอยู่ในดินแดนโนด4:16 แปลว่าร่อนเร่พเนจร(ดูข้อ 12 และ 14)ทางทิศตะวันออกของเอเดน

17คาอินร่วมหลับนอนกับภรรยา นางก็ตั้งครรภ์และให้กำเนิดเอโนค ขณะนั้นคาอินกำลังสร้างเมือง เขาจึงตั้งชื่อเมืองนั้นว่าเอโนคตามชื่อบุตรชายของตน 18เอโนคมีบุตรชายชื่ออิราด และอิราดเป็นบิดาของเมหุยาเอล เมหุยาเอลเป็นบิดาของเมธูชาเอล และเมธูชาเอลเป็นบิดาของลาเมค

19ลาเมคมีภรรยาสองคน คนหนึ่งชื่ออาดาห์ อีกคนหนึ่งชื่อศิลลาห์ 20อาดาห์มีบุตรชายชื่อยาบาล ซึ่งเป็นบิดาของคนเลี้ยงสัตว์และอาศัยในเต็นท์ 21ยาบาลมีน้องชายชื่อยูบาล ซึ่งเป็นบิดาของคนเล่นพิณและขลุ่ย 22ส่วนศิลลาห์ก็มีบุตรชายคนหนึ่งด้วย ชื่อทูบัลคาอิน เขาทำเครื่องมือเครื่องใช้จาก4:22 หรือเขาสอนทุกคนที่ทำเครื่องทองสัมฤทธิ์และเหล็ก ทูบัลคาอินมีน้องสาวชื่อนาอามาห์

23ลาเมคพูดกับภรรยาทั้งสองของเขาว่า

“อาดาห์และศิลลาห์ จงฟังเรา

ภรรยาของลาเมคเอ๋ย จงฟังคำของเรา

เราได้ฆ่าชายคนหนึ่งที่ทำร้ายเรา

ฆ่าเด็กหนุ่มคนหนึ่งที่ทำให้เราบาดเจ็บ

24หากใครทำร้ายคาอินจะถูกเอาคืนเจ็ดเท่า

ส่วนคนที่ทำร้ายลาเมคจะถูกเอาคืนเจ็ดสิบเจ็ดเท่า”

25อาดัมร่วมหลับนอนกับภรรยาของเขาอีก และนางให้กำเนิดบุตรชายอีกคนหนึ่ง จึงตั้งชื่อเขาว่าเสท4:25 คงจะมีความหมายว่าให้ นางกล่าวว่า “พระเจ้าประทานลูกชายอีกคนหนึ่งแทนอาแบลเพราะคาอินได้ฆ่าเขา” 26เสทก็มีบุตรชายคนหนึ่งชื่อว่าเอโนช

ในเวลานั้นมนุษย์เริ่มนมัสการโดยออก4:26 หรือประกาศพระนามพระยาห์เวห์