הבשורה על-פי מרקוס 7 – HHH & NASV

Habrit Hakhadasha/Haderekh

הבשורה על-פי מרקוס 7:1-37

1יום אחד באו אחדים מהפרושים והסופרים אל ישוע כדי לחקור את מעשיו. 2הם הבחינו בכך שכמה מתלמידיו של ישוע אינם נוטלים ידיים לפני הארוחה, כפי שנהוג במסורת היהודית. 3(במסורת היהודית של אז, במיוחד אצל הפרושים, נהגו ליטול ידיים עד למרפק לפני כל ארוחה. 4גם בשובם מן השוק עליהם ליטול ידיים לפני שהם נוגעים באוכל. זוהי רק דוגמה אחת ממנהגים רבים שהם מקיימים מאות שנים. דוגמה נוספת היא הכשרת סירים, מחבתות וכלים.)

5הם שאלו את ישוע: ”מדוע התלמידים שלך אינם שומרים את מסורת אבותינו הדורשת נטילת ידיים לפני הארוחה?“

6‏-7”צבועים שכמוכם!“ ענה להם ישוע. ”הנביא ישעיהו תיאר אתכם נכונה כשאמר:7‏.6‏-7 ז 5 ישעיהו כט 13

’ניגש העם הזה בפיו,

ובשפתיו כבדוני, ולבו רחק ממני,

ותהי יראתם אותי מצות אנשים מלומדה‘.

8”אתם מתעלמים ממצוותיו של אלוהים, ובמקומם אתם ממציאים מצוות ומנהגים למיניהם. 9ביטלתם את מצוות אלוהים כדי שתוכלו לקיים את המסורת שהמצאתם בעצמכם! 10קחו למשל את המצווה ’כבד את אביך ואת אמך‘. משה אמר שכל מקלל אביו ואמו מות יומת! 11ואילו אתם אומרים שמותר לאדם להתעלם מצרכי הוריו העניים, אם הוא מבטיח לתרום לעבודת אלוהים את אשר הוא חייב לתת להוריו. 12‏-13כך אתם מפרים את מצוות אלוהים כדי לקיים את המסורת שהמצאתם אתם. זוהי רק דוגמה אחת מתוך רבות.“

14ישוע אסף סביבו שנית את כל הקהל ואמר: ”הקשיבו אלי כולכם והשתדלו להבין: 15‏-16לא מה שנכנס אל גופכם מטמא אתכם, אלא מה שיוצא מתוכו. כל מי שיש לו אוזניים שישמע!“ 17לאחר שעזבו את הקהל והגיעו הביתה, שאלו התלמידים את ישוע למה התכוון במשל שסיפר.

18”מה, גם אתם אינכם מבינים?“ שאל ישוע בתימהון. ”האם אינכם מבינים כי האוכל שאתם אוכלים אינו מטמא אתכם? 19הרי האוכל אינו בא במגע עם הלב; האוכל עובר דרך מערכת העיכול.“ 20ישוע הוסיף ואמר: ”המחשבות הן המטמאות את האדם. 21כי מקרב לב האדם יוצאות מחשבות רעות של ניאוף, גניבה, רצח, 22בגידה, רדיפת בצע, רשעות, רמאות, פריצות, קנאה, הוצאת־דיבה, גאווה, ניבול־פה וכדומה. 23כל הדברים הנתעבים האלה יוצאים מתוך לב האדם, והם המטמאים והמרחיקים אותנו מאלוהים.“

24ישוע עזב את הגליל והלך לאזור צור וצידון. הוא ניסה להסתיר את דבר בואו, אך לא עלה בידו. כמו תמיד נפוצו השמועות על בואו במהירות.

25לאישה אחת הייתה בת אחוזת שד. כאשר שמעה האישה על בואו של ישוע באה אליו, נפלה לרגליו 26והתחננה לפניו שיגרש את השד מבתה (היא הייתה אישה יוונית שנולדה בפניקיה הסורית).

27”תחילה עלי לעזור לבני עמי – היהודים“, ענה לה ישוע. ”אין זה צודק לקחת את לחמם של הילדים ולהשליכו לכלבים.“

28”נכון, אדוני“, ענתה האישה. ”אולם גם גורי הכלבים מקבלים תחת השולחן את השאריות והפירורים מצלחות הילדים.“

29ישוע אמר לה: ”בגלל תשובתך בתך נרפאה; לכי לביתך ותראי שהשד יצא ממנה.“

30האישה הלכה לביתה ומצאה את בתה הקטנה שוכבת רגועה על מיטתה לאחר שיצא ממנה השד.

31מצור הלך ישוע לצידון, ומשם חזר לים הכינרת דרך אזור עשר הערים. 32ההמון הביא אליו איש חרש ואילם, וכולם התחננו לפניו שישים את ידיו על האיש וירפא אותו.

33ישוע הרחיק את החרש־אילם מההמון, הכניס את אצבעותיו לאוזני האיש, לאחר מכן ירק על אצבעותיו ונגע בלשונו של האילם. 34ישוע נשא את עיניו לשמים, נאנח וקרא: ”אפתח“ (”היפתח!“). 35מיד נפתחו אוזני האיש והוא שמע. גם לשונו הותרה והוא היה מסוגל לדבר ולשמוע היטב.

36‏-37ישוע ביקש מהנוכחים שלא להפיץ את הדבר. אולם ככל שהרבה להזהירם, כך הם הרבו לספר לאחרים, כי מעשיו הדהימו אותם כל כך. שוב ושוב קראו האנשים בהתרגשות: ”ראו איזה מעשים נפלאים ונהדרים; הוא אפילו מסוגל לרפא חרשים־אילמים!“

New Amharic Standard Version

ማርቆስ 7:1-37

ኢየሱስ የአይሁድን ውጫዊ ሥርዐት ተቃወመ

7፥1-23 ተጓ ምብ – ማቴ 15፥1-20

1ከዚህ በኋላ ፈሪሳውያንና ከኢየሩሳሌም የመጡ አንዳንድ ጸሐፍት በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ 2ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ ባልነጻ ማለት ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ፤ 3ፈሪሳውያንና አይሁድ ሁሉ የአባቶችን ወግ ለመጠበቅ ሲሉ፣ በሥርዐቱ መሠረት እጃቸውን በጥንቃቄ ሳይታጠቡ አይበሉም ነበርና። 4ከገበያ ሲመለሱም ታጥበው ራሳቸውን ካላነጹ በስተቀር አይበሉም ነበር። እንዲሁም ዋንጫን፣ ማሰሮን፣ ሳሕንና ዐልጋን7፥4 አንዳንድ የጥንት ቅጆች የማእድ ዐልጋ ይላሉ። እንደ ማጠብ ያሉትን ሌሎችን ወጎች ይጠብቁ ነበር።

5ፈሪሳውያንና ጸሐፍትም፣ “ደቀ መዛሙርትህ እንደ አባቶች ወግ በመኖር ፈንታ ባልታጠበ እጃቸው ለምን እንጀራ ይበላሉ?” ብለው ጠየቁት።

6እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ኢሳይያስ ስለ እናንተ፣ ስለ ግብዞች በትክክል ተንብዮአል፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤

“ ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤

ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤

7በከንቱ ያመልከኛል፤

ትምህርታቸውም ሰው ሠራሽ ሥርዐት ብቻ ነው።’

8የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ የሰዎችን ወግና ሥርዐት ታጠብቃላችሁ።”

9ደግሞም፣ እንዲህ አላቸው፤ “የራሳችሁን ወግ ለመጠበቅ7፥9 አንዳንድ ቅጆች ለማቆም ይላሉ። ስትሉ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የምትተዉበት ዘዴ አላችሁ። 10ሙሴ፣ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ፈጽሞ ይሙት’ ብሎ ነበርና፤ 11እናንተ ግን አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን፣ ከእኔ ማግኘት የሚገባችሁን ርዳታ ሁሉ ቍርባን፣ ይኸውም መባ አድርጌአለሁ ቢላቸው፣ 12እናንተም ይህ ሰው ለአባቱም ሆነ ለእናቱ ከዚህ በኋላ ምንም ነገር እንዲያደርግ አትፈቅዱለትም። 13ስለዚህ ለትውልድ በምታስተላልፉት ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ ይህን የመሰለም ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።”

14ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ስሙኝ፤ ሁላችሁም አስተውሉ፤ 15ከውጭ ወደ ውስጥ ገብቶ ሰውን የሚያረክሰው አንዳች ነገር የለም፤ ይልቁን ሰውን የሚያረክሰው ከራሱ ወደ ውጭ የሚወጣው ነገር ነው፤ 16ሰሚ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ7፥16 አንዳንድ የጥንት ቅጆች ይህ ቍጥር የላቸውም።።”

17ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ስለ ምሳሌው ጠየቁት። 18እርሱም፣ “እናንተም ነገሩ አይገባችሁምን? ከውጭ ወደ ሰው ገብቶ ሊያረክሰው የሚችል አንዳች ነገር የለም፤ 19ወደ ልቡ ሳይሆን ወደ ሆዱ ይገባል፤ ከዚያም ከሰውነቱ ይወጣልና።” ኢየሱስ ይህን በማለቱ ምግብ ሁሉ ንጹሕ መሆኑን ገለጠ።

20ቀጥሎም፣ እንዲህ አለ፤ “ከሰው የሚወጣ ያ ሰውን ያረክሰዋል፤ 21ከውስጥ፣ ከሰው ልብ የሚወጡት ክፉ ሐሳብ፣ ምንዝር፣ ስርቆት፤ ሰው መግደል፣ ዝሙት፣ 22መስገብገብ፣ ክፋት፣ ማታለል፣ መዳራት፣ ምቀኝነት፣ ስም ማጥፋት፣ ትዕቢት፣ ስንፍና ናቸው። 23እነዚህ ክፉ ነገሮች ሁሉ ከሰው ይወጣሉ፤ ሰውንም ያረክሱታል።”

ሲሮፊኒቃዊቷ ሴት

7፥24-30 ተጓ ምብ – ማቴ 15፥21-28

24ከዚያ ተነሥቶ ወደ ጢሮስ7፥24 አያሌ የጥንት ቅጆች ጢሮስና ሲዶና የሚለው አላቸው። አገር ሄደ፤ ወደ አንድ ቤት ገብቶ እዚያ መኖሩን ማንም እንዳያውቅበት ፈለገ፤ ሆኖም እዚያ መኖሩ ሊሸሸግ አልቻለም። 25ወዲያው ግን ትንሺቱ ልጇ በርኩስ7፥25 ወይም ክፉ መንፈስ የተያዘችባት አንዲት ሴት ስለ እርሱ ሰምታ መጣችና በእግሩ ላይ ወደቀች። 26ሴትዮዋም ግሪካዊት፣ በትውልዷም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች። እርሷም ኢየሱስ ጋኔኑን ከልጇ እንዲያስወጣላት ለመነችው።

27እርሱ ግን፣ “የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለውሾች መጣል ተገቢ ስላልሆነ፣ መጀመሪያ ልጆቹ ጠግበው ይብሉ” አላት።

28እርሷም መልሳ፣ “አዎን፣ ጌታ ሆይ፤ ውሾችም ከገበታ በታች ሆነው የልጆችን ትራፊ ይበላሉ” አለችው።

29እርሱም፣ “ስለዚህ ይህን ስላልሽ ሂጂ፤ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቷል” አላት።

30እርሷም ወደ ቤቷ ስትመለስ ልጇ ዐልጋ ላይ ተኝታ፣ ጋኔኑም ለቅቋት አገኘቻት።

የደንቈሮውና የድዳው መፈወስ

7፥31-37 ተጓ ምብ – ማቴ 15፥29-31

31ከዚያም ኢየሱስ ከጢሮስ አገር ተነሥቶ፣ በሲዶና በኩል አድርጎ ዐሥር ከተማ7፥31 የግሪኩ ዴካፖሊስ ይለዋል። በተባለው አገር በማለፍ ወደ ገሊላ ባሕር መጣ። 32በዚያም ሰዎች ደንቈሮና ዲዳ የሆነ አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፤ እጁንም እንዲጭንበት ለመኑት።

33ኢየሱስም ሰውየውን ከሕዝቡ ለይቶ ከወሰደው በኋላ፣ ጣቶቹን በጆሮው አስገባ፤ ከዚያም እንትፍ ብሎ የሰውየውን ምላስ ዳሰሰ። 34ወደ ሰማይም ተመልክቶ ቃተተና፣ “ኤፍታህ!” አለው፤ ይኸውም፣ “ተከፈት” ማለት ነው። 35ወዲያውም ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤ ምላሱም ተፈትቶ አጥርቶ መናገር ጀመረ።

36ኢየሱስ ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፤ ሆኖም እርሱ እንዳይናገሩ ባዘዛቸው መጠን፣ ነገሩን አስፍተው አወሩት። 37ሕዝቡም ከመጠን በላይ በመደነቅ፣ “ያደረገው ሁሉ ጥሩ ነው፤ ደንቈሮዎች እንዲሰሙ፣ ድዳዎች እንዲናገሩ እንኳ አድርጓል” አሉ።