約伯記 42 – CCBT & NASV

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

約伯記 42:1-17

1約伯回答耶和華說:

2「我知道你無所不能,

你的旨意無不成就。

3你問,『誰用無知的話使我的旨意晦暗不明?』

誠然,我對自己所談論的事一無所知,

這些事太奇妙,我無法明白。

4你說,『你且聽著,我要發言。

我來提問,你來回答。』

5我從前風聞有你,

現在親眼看見你。

6因此我厭惡自己,

在塵土和爐灰中懺悔。」

結語

7耶和華對約伯說完這些話後,就對提幔以利法說:「你和你的兩個朋友令我憤怒,因為你們對我的議論不如我僕人約伯說的有理。 8現在你們要取七頭公牛和七隻公羊,到我僕人約伯那裡,為自己獻上燔祭,因為你們對我的議論不如我僕人約伯說的有理。我僕人約伯會為你們禱告,我會悅納他的禱告,不按你們的愚妄懲罰你們。」 9於是,提幔以利法書亞比勒達拿瑪瑣法遵命而行,耶和華悅納了約伯的禱告。

10約伯為朋友們禱告後,耶和華恢復了他以前的昌盛,並且耶和華賜給他的比以前多一倍。 11約伯的兄弟姊妹和從前的朋友都來探望他,在他家裡一同吃飯,為他遭受耶和華所降的種種災難而安撫、慰問他。他們每人送他一塊銀子和一個金環。

12耶和華賜給約伯晚年的福分比起初更多:他有一萬四千隻羊、六千隻駱駝、一千對牛和一千頭母驢。 13他還有七個兒子和三個女兒。 14他給長女取名叫耶米瑪、次女叫基洗亞、三女叫基連·哈樸15那地方找不到像約伯三個女兒那樣美麗的女子。約伯讓她們與弟兄一同承受產業。 16此後,約伯又活了一百四十年,得見四代子孫。 17約伯年紀老邁,壽終正寢。

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 42:1-17

ኢዮብ

1ኢዮብም እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር መለሰ፤

2“አንተ ሁሉን ማድረግ እንደምትችል፣

ዕቅድህም ከቶ እንደማይሰናከል ዐወቅሁ።

3አንተ፣ ‘ያለ ዕውቀት ዕቅዴን የሚያደበዝዝ ይህ ማን ነው?’ አልኸኝ፤

በርግጥ ያልገባኝን ነገር፣

የማላውቀውንና ላስተውለው የማልችለውን ጕዳይ ተናገርሁ።

4“ ‘ስማኝ፣ ልናገር እኔ እጠይቃለሁ፤

አንተ ትመልስልኛለህ’ አልኸኝ።

5ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤

አሁን ግን ዐይኔ አየችህ።

6ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤

በትቢያና በዐመድ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።”

መደምደሚያ

7እግዚአብሔር ይህን ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ፣ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፤ “እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር ስላልተናገራችሁ፣ ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዷል። 8አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ስለ ራሳችሁ አቅርቡ። እንደ አሳፋሪ ተግባራችሁ እንዳላደርግባችሁ አገልጋዬ ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፤ እኔም ጸሎቱን እቀበላለሁ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር አልተናገራችሁምና።” 9ቴማናዊው ኤልፋዝ፣ ሹሐዊው በልዳዶስና ናዕማታዊው ሶፋር እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም የኢዮብን ጸሎት ተቀበለ።

10ኢዮብ ለወዳጆቹ ከጸለየ በኋላ፣ እግዚአብሔር እንደ ገና አበለጸገው፤ ቀድሞ በነበረው ፈንታ ዕጥፍ አድርጎ ሰጠው። 11ወንድሞቹና እኅቶቹ፣ ቀድሞም ያውቁት የነበሩ ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፤ በቤቱም ከእርሱ ጋር ምግብ በሉ። እነርሱም ሐዘናቸውን ገለጡለት፤ እግዚአብሔርም ካመጣበት መከራ ሁሉ አጽናኑት፤ እያንዳንዳቸውም ጥሬ ብርና42፥11 ዕብራይስጡ፣ ኬሊታ ይላል፤ ኬሊታ የገንዘብ ዐይነት ነው፤ ክብደቱና መጠኑ ግን በትክክል አይታወቅም። የወርቅ ቀለበት ሰጡት።

12እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን የኢዮብን ሕይወት ባረከ። እርሱም ዐሥራ አራት ሺሕ በጎች፣ ስድስት ሺሕ ግመሎች፣ አንድ ሺሕ ጥማድ በሬዎች፣ አንድ ሺሕ እንስት አህዮችም ነበሩት። 13ደግሞም ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ 14የመጀመሪያዋን ይሚማ፣ ሁለተኛዋን ቃሥያ፣ ሦስተኛዋንም አማልቶያስ ቂራስ ብሎ ሰየማቸው። 15እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች የተዋቡ ሴቶች በምድሪቱ ሁሉ አልተገኙም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት ሰጣቸው።

16ከዚህ በኋላ ኢዮብ አንድ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ። 17በዚህ ሁኔታ አርጅቶ፣ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ።