帖撒羅尼迦前書 4 – CCBT & NASV

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

帖撒羅尼迦前書 4:1-18

上帝喜悅的生活

1最後,弟兄姊妹,既然你們領受了我們的教導,知道怎樣行才能討上帝的喜悅,如你們現在所行的,我們靠著主耶穌懇求、勸勉你們要更加努力。 2你們都知道我們靠著主耶穌傳給你們的誡命。 3上帝的旨意是要你們聖潔,遠避淫亂的事, 4要你們人人都知道持守身體的聖潔和尊貴, 5不可荒淫縱慾,像那些不認識上帝的外族人一樣。 6你們在這種事上不可越軌,虧負弟兄姊妹。我們曾經對你們說過,並且鄭重地警告過你們,主必懲治犯這種罪的人。 7因為上帝呼召我們不是要我們沾染污穢,而是要我們聖潔。 8所以,人若拒絕遵行這命令,他不是拒絕人,而是拒絕賜聖靈給你們的上帝。

9關於弟兄姊妹彼此相愛的事,我就不必多寫了,因為你們自己從上帝那裡領受了要彼此相愛的教導。 10你們對馬其頓全境的弟兄姊妹已經做到了這一點。不過,我勸各位要再接再厲。 11你們要立志過安分守己的生活,親手做工,正如我們以前吩咐你們的。 12這樣,你們可以得到外人的尊敬,不必依賴任何人。

復活的盼望

13弟兄姊妹,關於安息的信徒4·13 安息的信徒」希臘文是「睡了的人」,聖經常用「睡了」作為「死了」的委婉說法,參見約翰福音十一章11—14節。,我不願意你們一無所知,免得你們像那些沒有盼望的人一樣悲傷。 14我們既然相信耶穌死了,又復活了,也要相信上帝必把那些安息的信徒和耶穌一同帶來。

15我們把主耶穌的話告訴你們:主再來的那天,我們還活著的人不會比已安息的信徒先見到主。 16因為主必在號令聲、天使長的呼喊聲和上帝的號角聲中親自從天降臨,已經離世的基督徒必先復活。 17然後,我們還活著的人要和他們一起被提到雲裡,在空中與主相會,永遠和主在一起。 18所以你們要用這些話彼此鼓勵。

New Amharic Standard Version

1 ተሰሎንቄ 4:1-18

እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አኗኗር

1በቀረውስ ወንድሞች ሆይ፤ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት እንዴት መኖር እንደሚገባችሁ አስተምረናችኋል፤ በርግጥም እንደዚያው እየኖራችሁ ነው። ስለሆነም በጌታ በኢየሱስ የምንለምናችሁና የምንመክራችሁ ከዚህ በበለጠ ሁኔታ በዚሁ እንድትገፉበት ነው። 2በጌታ በኢየሱስ ሥልጣን ምን ዐይነት ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁ።

3የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው፤ 4ደግሞም እያንዳንዱ የገዛ ሰውነቱን በቅድስናና በክብር መያዝ4፥4 ወይም ከገዛ ሚስቱ ጋር መኖርን መማር ወይም ሚስት ለማግኘት መማር እንዳለበት እንዲያውቅ ነው፤ 5ይህም እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወተ ሥጋ ምኞት አይሁን። 6በዚህም ነገር ማንም ተላልፎ ወንድሙን አያታልል፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ እንደ እነዚህ ያለውን ኀጢአት ሁሉ የሚፈጽሙትን ይበቀላል፤ 7እግዚአብሔር በቅድስና እንድንመላለስ እንጂ ለርኩሰት አልጠራንምና። 8እንግዲህ ይህን ምክር ንቆ የማይቀበል፣ የናቀው ቅዱስ መንፈሱን የሰጣችሁን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አይደለም።

9ስለ ወንድማማች መዋደድ ማንም እንዲጽፍላችሁ አያስፈልግም፤ ምክንያቱም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ እናንተ ራሳችሁ ከእግዚአብሔር ተምራችኋልና።

10በመላዪቱ መቄዶንያ የሚገኙትን ወንድሞች ሁሉ እንደምትወድዷቸው የታወቀ ነው፤ ነገር ግን ወንድሞች ሆይ፤ ከዚህ በበለጠ እንድታደርጉት እንመክራችኋለን።

11ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁ በገዛ እጃችሁ ሥሩ፤ በጸጥታ ኑሩ፤ በራሳችሁ ጕዳይ ላይ ብቻ አተኵሩ። 12ይኸውም፣ በዕለት ተለት ኑሯችሁ በውጭ ባሉት ዘንድ እንዲያስከብራችሁና በማንም ሰው ላይ ሸክም እንዳትሆኑ ነው።

የጌታ ዳግም ምጽአት

13ወንድሞች ሆይ፤ አንቀላፍተው ስላሉ ሰዎች ሳታውቁ እንድትቀሩ አንፈልግም፤ ደግሞም ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሰዎች እንድታዝኑ አንሻም። 14ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፣ በኢየሱስ ሆነው ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደዚሁ ያመጣቸዋል። 15በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህን ነው፤ እኛ በሕይወት ያለንና ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም፤ 16ጌታ ራሱ በታላቅ ትእዛዝ፣ በመላእክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር የመለከት ድምፅ ከሰማይ ይወርዳልና። በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሣሉ። 17ከዚያም በኋላ እኛ የቀረነው፣ በሕይወትም የምንኖረው ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ በዚህም መሠረት ለዘላለም ከጌታ ጋር እንሆናለን። 18ስለዚህ በዚህ ቃል እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ።