創世記 46 – CCBT & NASV

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 46:1-34

以色列全家下埃及

1以色列帶著他所有的一切來到別示巴,向他父親以撒的上帝獻祭。 2晚上,上帝在異象中對他說:「雅各雅各!」他說:「我在這裡。」 3上帝說:「我是上帝,是你父親的上帝,不要害怕下到埃及,因為我要使你在那裡成為大族。 4我必跟你一起下到埃及,也必帶領你回來,約瑟必為你送終。」

5於是,雅各別示巴啟程。以色列的兒子們帶著父親和妻兒,乘坐法老送來的車, 6帶著在迦南獲得的牲畜和財物前往埃及。這樣,雅各帶著他所有的子孫, 7就是他的兒子、孫子、女兒和孫女一起去了埃及

8以下是去埃及以色列人,即雅各和他後代的名字。

雅各的長子是呂便9呂便的兒子是哈諾法路希斯倫迦米10西緬的兒子是耶姆利雅憫阿轄雅斤瑣轄迦南女子生的掃羅11利未的兒子是革順哥轄米拉利12猶大的兒子是俄南示拉法勒斯謝拉俄南死在了迦南法勒斯的兒子是希斯倫哈姆勒13以薩迦的兒子是陀拉普瓦約伯伸崙14西布倫的兒子是西烈以倫雅利15這些都是利亞巴旦·亞蘭雅各生的兒孫,加上女兒底娜共有三十三人。

16迦得的兒子是洗非芸哈基書尼以斯本以利亞羅底亞列利17亞設的兒子是音拿亦施瓦亦施韋比利亞和他們的妹妹西拉比利亞的兒子是希別瑪結18這些是悉帕雅各生的兒孫,共有十六人,悉帕拉班給女兒利亞的婢女。

19雅各的妻子拉結生的兒子是約瑟便雅憫20約瑟埃及生的兒子是瑪拿西以法蓮,他們的母親是城祭司波提非拉的女兒亞西納21便雅憫的兒子是比拉比結亞實別基拉乃幔以希羅實姆平戶平亞勒22這些是拉結雅各生的兒孫,共有十四人。

23的兒子是戶伸24拿弗他利的兒子是雅薛沽尼耶色示冷25這些是辟拉雅各生的兒孫,共有七人,辟拉拉班給女兒拉結的婢女。

26雅各一同到埃及去的兒孫共有六十六人,他的兒媳婦除外。 27加上約瑟埃及生的兩個兒子,雅各一家來到埃及的共有七十人。

28雅各猶大先去見約瑟,請他派人引路到歌珊去。他們來到歌珊29約瑟備好車前去迎接父親以色列。父子重逢,約瑟抱住父親哭了很久。 30以色列約瑟說:「我現在看到你還活著,就是死也安心了。」

31約瑟對他的弟兄們和其他家人說:「我要去告訴法老,你們已經從迦南來到我這裡。 32你們是牧人,以畜牧為業,已經把羊群、牛群和所有的一切都帶來了。 33等法老召見你們,問你們以什麼為業, 34你們要說,『僕人們跟我們的祖先一樣,從小以畜牧為業。』這樣,你們就可以住在歌珊,因為埃及人厭惡牧羊的。」

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 46:1-34

ያዕቆብ ወደ ግብፅ ሄደ

1እስራኤልም ጓዙን ሁሉ ጠቅልሎ ተነሣ፤ ቤርሳቤህም ሲደርስ፣ ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ (ኤሎሂም) መሥዋዕት ሠዋ።

2እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ። 3እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ነኝ፤ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ በዚያ ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና፤ 4አብሬህ ወደ ግብፅ እወርዳለሁ፤ ከዚያም መልሼ አወጣሃለሁ፤ የዮሴፍ የራሱ እጆችም ዐይኖችህን ይገጥሟቸዋል።”

5ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሣ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን፣ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን ለያዕቆብ በላካቸው ሠረገላዎች ላይ አወጧቸው። 6ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብፅ ወረዱ። 7ወደ ግብፅም የወረደው፣ ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹንና ሴቶች የልጅ ልጆቹን፣ ማለትም ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ነው።

8ወደ ግብፅ የወረዱት የእስራኤል ልጆች፣ ያዕቆብና ዘሮቹ እነዚህ ናቸው፦

የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል።

9የሮቤል ልጆች፦

ሄኖኅ፣ ፈሉሶ፣ አስሮን እና ከርሚ ናቸው።

10የስምዖን ልጆች፦

ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደው ሳኡል ናቸው።

11የሌዊ ልጆች፦

ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው።

12የይሁዳ ልጆች፦

ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ።

13የይሳኮር ልጆች፦

ቶላ፣ ፉዋ፣46፥13 ከኦሪተ ሳምራውያንና ከሱርስቱ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን (1ዜና 7፥1 ይመ) የማሶሬቲክ ጽሑፍ ግን ፋቫ ይለዋል። ዮብና ሺምሮን ናቸው፤

14የዛብሎን ልጆች፦

ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤

15እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቍጥር ሠላሳ ሦስት ነው።

16የጋድ ልጆች፦

ጽፎን፣46፥16 ከኦሪተ ሳምራውያንና ከሰብዓ ሊቃናት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን (ዘኍ 26፥15 ይመ) የማሶሬቲክ ጽሑፍ ግን ጸሬን ይለዋል። ሐጊ፣ ሹኒ፣ ኤስቦን፣ ዔሪ፣ አሮዲና አርኤሊ ናቸው፤

17የአሴር ልጆች፦

ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊና በሪዓ ናቸው፤ እኅታቸውም ሤራሕ ናት፤

የበሪዓ ልጆች፦

ሐቤርና መልኪኤል ናቸው፤

18እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ፣ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።

19የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች፦

ዮሴፍና ብንያም ናቸው፤ 20በግብፅም የሄልዮቱ46፥20 ሆሲዮፖሊስን ያመለክታል። ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት።

21የብንያም ልጆች፦

ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ናዕማን፣ አኪ፣ ሮስ፣ ማንፌን ሑፊምና አርድ ናቸው።

22እነዚህ ዐሥራ አራቱ፣ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው።

23የዳን ልጅ፦

ሑሺም ነው፤

24የንፍታሌም ልጆች፦

ያሕጽኤል፣ ጉኒ፣ ዬጽርና ሺሌም ናቸው፤

25እነዚህ ሰባቱ ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።

26ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የሄዱት የገዛ ዘሮቹ ብዛት ስድሳ ስድስት ሲሆን ይህ ቍጥር ግን የልጆቹን ሚስቶች አይጨምርም። 27ዮሴፍ በግብፅ የወለዳቸውን ሁለት ልጆች46፥27 ከዕብራይስጡ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ሰብዓ ሊቃናት ግን ዘጠኙ ልጆች ይለዋል። ጨምሮ፣ ወደ ግብፅ የወረደው የያዕቆብ ቤተ ሰብ ቍጥር ሰባ46፥27 ከዕብራይስጡ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን (ዘፀ 1፥5 እና ማብ ይመ)፣ ሰብዓ ሊቃናት ግን (ሐሥ 7፥14 ይመ) ሰባ አምስት ይለዋል። ነበር።

28ያዕቆብም ወደ ጌሤም ለመሄድ መመሪያን ይቀበል ዘንድ ይሁዳን አስቀድሞ ወደ ዮሴፍ ላከው። እነርሱም ጌሤም ሲደርሱ፣ 29ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጅቶ፤ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጌሤም አመራ።

ዮሴፍ አባቱ ዘንድ እንደ ደረሰ፣ ዐንገቱ ላይ46፥29 ዕብራይስጡ በላዩ ላይ ይለዋል። ተጠምጥሞ ለረጅም ጊዜ አለቀሰ።

30እስራኤልም ዮሴፍን፣ “በሕይወት መኖርህን ስላየሁ፣ ከእንግዲህ ብሞትም አይቈጨኝ” አለው።

31ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ አናግረዋለሁ፤ እንዲህም እለዋለሁ፣ ‘በከነዓን ምድር የሚኖሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል። 32ሰዎቹ ከብት የሚጠብቁ ስለ ሆኑ እረኞች ናቸው፤ ሲመጡም በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውንና ከብቶቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል።’ 33ፈርዖን አስጠርቷችሁ፣ ‘ሥራችሁ ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ፣ 34እናንተ፣ ‘እኛ ባሮችህ ሥራችን ከልጅነታችን ጀምሮ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት ማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። ከዚያም ግብፃውያን ከብት አርቢዎችን እንደ ጸያፍ ስለሚቈጥሩ፣ በጌሤም ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”