創世記 38 – CCBT & NASV

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 38:1-30

猶大與她瑪

1那時,猶大離開了他的兄弟們,到亞杜蘭希拉的家裡住。 2他在那裡遇見了迦南書亞的女兒,就娶她為妻,與她同房。 3她懷孕生了一個兒子,猶大給他取名叫4她又懷孕生了一個兒子,給他取名叫俄南5她再次懷孕生了一個兒子,給他取名叫示拉示拉是在基悉出生的。

6猶大給長子娶了她瑪為妻。 7耶和華見行為邪惡,就取走了他的性命。 8猶大俄南說:「你要與哥哥的妻子她瑪同房,向她盡你做弟弟的本分,好替你哥哥傳宗接代。」 9俄南知道生了兒子也不歸自己,所以每次與她瑪同房都把精液遺在地上,免得給他哥哥留後。 10耶和華見俄南行為邪惡,就取走了他的性命。 11猶大恐怕示拉會像他的兩個哥哥一樣死去,就對兒媳她瑪說:「示拉還沒有長大,你先回娘家守寡吧。」

12多年後,猶大的妻子,即書亞的女兒死了,等到守喪的日子滿了,猶大就和他的朋友亞杜蘭希拉亭拿,到替他剪羊毛的人那裡。 13有人告訴她瑪說:「你公公到亭拿去剪羊毛了。」 14她瑪示拉已經長大,卻仍然沒有娶她,就脫下寡婦的衣服,蒙上臉,換了裝束,坐在去亭拿路上的伊拿印城門口。 15猶大看見她蒙著臉,以為她是妓女, 16就走過去對她說:「你陪我睡覺吧。」猶大不知道她是自己的兒媳婦。她瑪問道:「你要我陪你睡覺,你給我什麼呢?」 17猶大回答說:「我會從羊群中取一隻山羊羔送給你。」她瑪問道:「羊還沒有送來以前,你給我什麼作抵押呢?」 18猶大問:「你要什麼作抵押呢?」她瑪說:「我要你的印、印帶和你的手杖。」猶大給了她,然後跟她睡覺。她瑪就這樣懷了孕。 19事後,她起來走了。她拿掉蒙臉的布,仍舊穿上寡婦的裝束。

20猶大託他的朋友亞杜蘭人送去一隻山羊羔,要從那女人手中換回抵押物,卻找不到她。 21他的朋友就問當地的人:「伊拿印路旁的廟妓在哪裡?」他們回答說:「這裡沒有廟妓。」 22他的朋友只好回去對猶大說:「我找不著她,當地人說那裡沒有廟妓。」 23猶大說:「讓她留著我的東西吧,免得我們成為笑柄。反正我把羊送過去了,只是你找不到她。」

24大約過了三個月,有人告訴猶大說:「你的兒媳婦她瑪不守婦道,並且懷孕了。」猶大說:「把她拉出來燒死!」 25他們正要把她拉出來,她請人帶口信給他公公,說:「這些東西的主人使我懷了孕,請你看這印、印帶和杖是誰的?」 26猶大認出是自己的東西,就說:「她比我更有理,因為我沒有讓示拉娶她。」猶大沒有再與她睡覺。

27她瑪臨產的時候,才知道腹中是一對雙胞胎。 28生產的時候,一個嬰兒先伸出手來,接生婆就把一條紅線繫在他的手上,說:「他是先出生的。」 29可是那嬰兒隨後卻把手縮回去,另一個嬰兒先出生了,接生婆說:「你怎麼搶先出來了?」因此,他的名字叫法勒斯38·29 法勒斯」意思是「搶先出來」。30後來,那個手上繫有紅線的孩子也出生了,給他取名叫謝拉38·30 謝拉」意思是「紅色」或「光明」。

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 38:1-30

ይሁዳና ትዕማር

1በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ፣ ኤራስ ወደ ተባለ ዓዶሎማዊ ሰው ወረደ፤ እርሱም ዘንድ ለመኖር ቤቱ ገባ። 2እዚያም ሳለ፣ ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ አየ፤ እርሷንም አግብቶ አብሯት ተኛ፤ 3እርሷም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙም ዔር ተባለ። 4እንደ ገናም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙን አውናን አለችው። 5አሁንም ደግማ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ አወጣችለት፤ እርሱንም የወለደችው ክዚብ በተባለ ቦታ ነበር።

6ይሁዳ የበኵር ልጁን ዔርን፣ ትዕማር የምትባል ሚስት አጋባው። 7የይሁዳ የበኵር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ፊት ክፉ ነበር፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ቀሠፈው።

8በዚህ ጊዜ ይሁዳ አውናንን፣ “ዋርሳዋ እንደ መሆንህ ከወንድምህ ሚስት ጋር ሩካቤ ሥጋ በመፈጸም የወንድምህን ስም የሚያስጠራለት ዘር ተካለት” አለው። 9አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የእርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፣ ከወንድሙ ሚስት ጋር ሩካቤ ሥጋ በፈጸመ ቍጥር የወንድሙንም ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወልድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስስ ነበር። 10ይህም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ክፉ አድራጎት ሆኖ ስለ ተገኘ፣ እርሱንም እግዚአብሔር (ያህዌ) በሞት ቀሠፈው።

11ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፣ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት። ይህን ያለውም፣ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።

12ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፣ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጕር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።

13ሰዎቹም ለትዕማር፣ “ዐማትሽ የበጎቹን ጠጕር ወደሚሸልቱ ሰዎች ዘንድ ወደ ተምና እየሄደ ነው” አሏት። ይህን እንደ ሰማች 14የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፣ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፣ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፣ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።

15ፊቷ በሻሽ ተሸፋፍኖ ሲያያት፣ ይሁዳ ዝሙት ዐዳሪ መሰለችው። 16ምራቱ መሆኗን ባለማወቁ፣ እርሷ ወዳለችበት ወደ መንደሩ ዳር ጠጋ ብሎ፣ “እባክሽ አብሬሽ ልተኛ” አላት። እርሷም፣ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው።

17“ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርሷም መልሳ፣ “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ ምን መያዣ ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው።

18“ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርሷም፣ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፣ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና አብሯት ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች። 19ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፣ ሻሽዋን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች።

20ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶሎማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፣ መልእክተኛው ግን ሴትየዋን ሊያገኛት አልቻለም። 21“በኤናይም ከተማ መግቢያ ከመንገዱ ዳር የነበረች ያቺ ዝሙት ዐዳሪ የት ደረሰች?” ሲል ጠየቃቸው። ሰዎቹም፣ “በዚህ አካባቢ ኧረ ምንም ዝሙት ዐዳሪ ታይታ አትታወቅም” አሉት።

22መልእክተኛውም ወደ ይሁዳ ተመልሶ፣ “ሴቲቱን ላገኛት አልቻልሁም፤ ነዋሪዎቹም ‘በዚህ አካባቢ እንደዚህች ያለች ዝሙት ዐዳሪ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው።

23ይሁዳም፣ “እንግዲህ መያዣውን እንደ ያዘች ትቅር፣ አለዚያ መሣቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፤ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ።

24ከሦስት ወር ያህል በኋላ፣ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው።

ይሁዳም፣ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።

25እርሷም ተይዛ በምትወሰድበት ጊዜ ለዐማቷ፣ “እኔ ያረገዝሁት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” ስትል ላከችበት፤ ደግሞም፣ “የማኅተሙ ቀለበት ከነማንጠልጠያውና በትሩ የማን እንደ ሆነ እስቲ ተመልከት” አለችው።

26ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም።

27የመውለጃዋ ጊዜ እንደ ደረሰም ፅንሷ መንታ መሆኑ ታወቀ። 28በምትወልድበትም ጊዜ አንደኛው እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም፣ “ይህኛው መጀመሪያ ወጣ” ስትል በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት፤ 29ነገር ግን፣ እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ከዚያም ስሙ ፋሬስ38፥29 ፋሬስ ማለት ጥሶ መውጣት ማለት ነው። ተባለ። 30ከዚያ በኋላ እጁ ላይ ቀይ ክር የታሰረለት ወንድሙ ተወለደ፤ ስሙም ዛራ38፥30 ዛራ የሚለው ደማቅ ቀይ ወይም ብሩህ እንደ ማለት ነው። ተባለ።