創世記 14 – CCBT & NASV

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 14:1-24

亞伯蘭救回羅得

1-2那時,示拿暗拉非以拉撒亞略以攔基大老瑪戈印提達聯合攻打以下五王:所多瑪比拉蛾摩拉比沙押瑪示納洗扁善以別比拉王,即瑣珥王。 3五王會師西訂谷,即鹽海。 4他們受基大老瑪王統治十二年,在第十三年叛變了。 5第十四年,基大老瑪聯合其他王在亞特律·加寧打敗利乏音人,在哈麥打敗蘇西人,在沙微·基列亭打敗以米人, 6西珥山打敗住在那裡的何利人,直殺到靠近曠野的伊勒·巴蘭7然後,他們返回安·密巴,即加低斯,征服了亞瑪力全境以及住在哈洗遜·他瑪亞摩利人。 8那時,所多瑪王、蛾摩拉王、押瑪王、洗扁王和比拉王,即瑣珥王,在西訂谷擺開陣勢, 9抵抗以攔基大老瑪戈印提達示拿暗拉非以拉撒亞略:四王跟五王交戰。 10西訂谷有許多柏油坑,所多瑪王和蛾摩拉王敗走的時候,有些人掉進坑裡,其他人都往山上逃命。 11四王把所多瑪蛾摩拉所有的財物和糧食洗劫一空, 12並劫走亞伯蘭的侄兒羅得和他的財物,那時羅得正住在所多瑪

13有一個逃出來的人把這件事情告訴了希伯來亞伯蘭。那時,亞伯蘭住在亞摩利幔利的橡樹那裡。幔利以實各亞乃的兄弟,三人都是亞伯蘭的盟友。 14亞伯蘭聽見侄兒被擄的消息,便率領家中三百一十八名訓練有素的壯丁去追趕他們,一直追到但。 15夜裡,亞伯蘭和他的隨從分頭出擊,大敗敵人,一直追殺到大馬士革北面的何巴, 16奪回所有被劫的財物,並救出他侄兒羅得和他的財物、婦女及其他人。

麥基洗德祝福亞伯蘭

17亞伯蘭大敗基大老瑪及其盟軍後凱旋歸來,所多瑪王到沙微谷來迎接他們。沙微谷即王谷。 18撒冷麥基洗德也帶著餅和酒出來相迎,他是至高上帝的祭司。 19他祝福亞伯蘭說:

「願創造天地的主、至高的上帝賜福給亞伯蘭

20將敵人交在你手中的至高上帝當受稱頌!」

於是,亞伯蘭把所得的十分之一給麥基洗德21所多瑪王對亞伯蘭說:「請把我的人民交還給我,你可以把財物拿去。」 22亞伯蘭對他說:「我向創造天地的主、至高的上帝耶和華起誓, 23凡是你的東西,就是一根線、一條鞋帶,我都不會拿,免得你說,『我使亞伯蘭發了財!』 24除了我的隨從已經吃用的以外,我什麼也不要。至於我的盟友亞乃以實各幔利所應得的戰利品,請分給他們。」

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 14:1-24

አብራም ሎጥን መታደጉ

1አምራፌል የሰናዖር14፥1 በ9 ላይ ያለውንም ጨምሮ ባቢሎንን ያመላክታል። ንጉሥ፣ አርዮክ የእላሳር ንጉሥ፣ ኮሎዶጎምር የኤላም ንጉሥ፣ ቲድዓል የጎይም ንጉሥ በነበሩበት ዘመን፣ 2ከሰዶም ንጉሥ ከበላ፣ ከገሞራ ንጉሥ ከብርሳ፣ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፣ ከሰቦይ ንጉሥ ከሰሜበር፣ እንዲሁም ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ወጡ። 3እነዚህ የኋለኞቹ አምስቱ ነገሥታት በሲዲም ሸለቆ፣ በጨው ባሕር14፥3 የሙት ባሕር ማለት ነው። ተሰበሰቡ። 4እነርሱም ዐሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ከተገዙ በኋላ በዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ዐመፁ።

5በዐሥራ አራተኛው ዓመት ኮሎዶጎምርና ከርሱ ጋር የተባበሩት ነገሥታት ወጡ፤ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፣ ዙዚምን በሃም፣ ኑሚምን በሴዊ ቂርያታይም፣ 6የሖር ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይር በረሓማ አጠገብ እስካለው እስከ ኤልፋራን ድረስ ድል አደረጓቸው። 7ከዚያም ተመልሰው ዐይን ሚስፖጥ ወደተባለው ወደ ቃዴስ መጡ፤ የአማሌቃውያንና በሐሴስ ታማር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያንን ግዛት በሙሉ ድል አድርገው ያዙ።

8ከዚያም የሰዶም፣ የገሞራ፣ የአዳማ፣ የሰቦይ እንዲሁም ዞዓር የተባለችው የቤላ ነገሥታት በሲዲም ሸለቆ ሰራዊታቸውን አስተባበሩ። 9እነዚህ አምስቱ፣ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉሥ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፣ በእነዚህ በአራቱ ላይ ዘመቱባቸው። 10በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጕድጓዶች ስለ ነበሩ የሰዶምና የገሞራ ነገሥታት ሲሸሹ ከሰዎቻቸው አንዳንዶቹ በእነዚህ ጕድጓዶች ውስጥ ወደቁ፤ የቀሩትም ወደ ተራሮች ሸሹ። 11አራቱ ነገሥታትም በሰዶምና በገሞራ ያገኙትን ሀብትና ምግብ ሁሉ ዘርፈው ሄዱ። 12የአብራም ወንድም ልጅ ሎጥ፣ ሰዶም ይኖር ስለ ነበር እርሱንም ማርከው ንብረቱንም ዘርፈው ሄዱ።

13ከዚህም ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ይህን ነገረ፤ አብራም በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው በአሞራዊው መምሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ ነበር። መምሬ፣ ወንድሞቹ14፥13 ወይም ዘመድ፤ ወይም ጓድ አስኮና አውናን የአብራም የኪዳን አጋሮቹ ነበሩ። 14አብራም የወንድሙን ልጅ መማረክ እንደ ሰማ በቤቱ ተወልደው አድገው የሠለጠኑ 318 ጦረኞች አሰልፎ እስከ ዳን ድረስ ገሠገሠ። 15አብራም ጠላቶቹን ለማጥቃት ሰራዊቱን ሌሊቱን በቡድን በቡድን ከፋፍሎ ከደማስቆ በስተ ሰሜን እስከሚገኘው እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው። 16አብራም ጠላት የማረከውን በሙሉ አስጣለ፤ የወንድሙን ልጅ ሎጥን፣ ንብረቱን እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎቹን ምርኮኞች አስመለሰ።

17አብራም ኮሎዶጎምርንና አብረውት የተሰለፉትን ነገሥታት ድል አድርጎ ሲመለስ፣ የሰዶም ንጉሥ፣ “የንጉሥ ሸለቆ” ተብሎ በሚጠራው በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ።

18የልዑል እግዚአብሔር (ኤል-ኤልዮን) ካህን የነበረው የሳሌም14፥18 ኢየሩሳሌም ናት ንጉሥ መልከጼዴቅም እንጀራና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤ 19አብራምንም እንዲህ ሲል ባረከው፤

“ሰማይንና ምድርን የፈጠረ14፥19 ወይም በ22 ላይ ያለውንም ጨምሮ ባለቤት ሊሆን ይችላል። ልዑል

እግዚአብሔር (ኤል-ኤልዮን) አብራምን ይባርክ፤

20ጠላቶችህን አሳልፎ በእጅህ የሰጠህ፣

ልዑል እግዚአብሔር (ኤል-ኤልዮን) ይባረክ።”

አብራምም ካመጣው ሁሉ ዐሥራትን ሰጠው።

21የሰዶም ንጉሥም አብራምን፣ “ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው።

22አብራም ግን ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ሰማይንና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ)፣ ወደ ልዑል አምላክ (ኤል-ኤልዮን) እጆቼን አንሥቻለሁ፤ 23‘አብራምን አበለጸግሁት’ እንዳትል፣ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ከአንተ አንዳች አልፈልግም። 24ሰዎቼ ከበሉትና ከእኔ ጋር ከሄዱት ሰዎች ድርሻ በስተቀር ለራሴ አንዳች ነገር አልቀበልም፤ አውናን፣ ኤስኮልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።”