以斯拉記 10 – CCBT & NASV

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

以斯拉記 10:1-44

終止雜婚

1以斯拉禱告、認罪、哭泣、俯伏在上帝的殿前時,一大群以色列人,包括男女和孩子,都聚集到他那裡,與他一起痛哭。 2以攔宗族耶歇的兒子示迦尼以斯拉說:「我們對我們的上帝不忠,娶這地方的外族女子為妻,但以色列還有希望。 3現在,我們來與我們的上帝立約,聽從你和那些敬畏我們上帝誡命之人的指示,遵照律法而行,送走這些妻子和她們的兒女。 4起來吧!這事由你處理,我們支持你,放膽去做吧!」

5於是,以斯拉起來,要祭司長、利未人和所有以色列人起誓照這話去做,他們就都起了誓。 6以斯拉從上帝的殿前起來,進了以利亞實的兒子約哈難的房間。他在那裡不吃不喝,為流亡歸來者的不忠而憂傷。

7他們在猶大耶路撒冷發出通告,要求所有流亡歸來的人在耶路撒冷集合。 8按照眾首領和長老的決定,三天之內未到者,其財產會被沒收,他本人也要被逐出流亡歸來者的會。

9三天內,所有的猶大人和便雅憫人都聚集在耶路撒冷。九月二十日,大家都坐在上帝的殿前面的廣場上。因為這事,加上當時下大雨,眾人都戰戰兢兢。

10以斯拉祭司站起來對他們說:「你們對上帝不忠,娶外族的女子為妻,加重了以色列的罪惡。 11現在,你們要向你們祖先的上帝耶和華認罪,遵行祂的旨意,與這地方的人和你們的外族妻子斷絕關係。」

12會眾都高聲回答說:「你說的對,我們必照你的話做。 13可是,人這麼多,又逢大雨季節,我們不能總站在外面,並且這事一兩天也解決不了,因為我們在這事上犯了大罪。 14不如讓我們的首領為全體會眾處理這事,讓那些娶了外族女子為妻的人在指定的時間與本城的長老和審判官一起來找首領解決,直到我們的上帝因這事而發的烈怒離開我們。」

15只有撒黑的兒子約拿單特瓦的兒子雅哈謝反對這事,支持他們的還有米書蘭利未沙比太

16流亡歸來的人都遵照建議而行。以斯拉祭司按家族選出各族長,都是點名指定的。他們從十月一日開始著手查辦這事, 17到次年一月一日才查清娶外族女子為妻的人。

18祭司中娶外族女子為妻的有耶書亞的子孫約薩達的兒子及其弟兄瑪西雅以利以謝雅立基大利19他們答應休掉自己的妻子,並從羊群中獻上一隻公綿羊為自己贖罪。 20音麥的子孫中有哈拿尼西巴第雅21哈琳的子孫中有瑪西雅以利雅示瑪雅耶歇烏西雅22巴施戶珥的子孫中有以利約乃瑪西雅以實瑪利拿坦業約撒拔以利亞撒

23利未人中有約撒拔示每基拉雅——又名基利他毗他希雅猶大以利以謝24歌樂手中有以利亞實。殿門守衛中有沙龍提聯烏利

25其他以色列人中有巴錄的子孫拉米耶西雅瑪基雅米雅民以利亞撒瑪基雅比拿雅26以攔的子孫中有瑪他尼撒迦利亞耶歇押底耶利末以利雅27薩土的子孫中有以利約乃以利亞實瑪他尼耶利末撒拔亞西撒28比拜的子孫中有約哈難哈拿尼雅薩拜亞勒29巴尼的子孫中有米書蘭瑪鹿亞大雅雅述示押耶利末30巴哈·摩押的子孫中有阿底拿基拉比拿雅瑪西雅瑪他尼比撒列賓內瑪拿西31哈琳的子孫中有以利以謝伊示雅瑪基雅示瑪雅西緬32便雅憫瑪鹿示瑪利雅33哈順的子孫中有瑪特乃瑪達他撒拔以利法列耶利買瑪拿西示每34巴尼的子孫中有瑪玳暗蘭烏益35比拿雅比底雅基祿36瓦尼雅米利末以利亞實37瑪他尼瑪特乃雅掃38賓內的子孫中有示每39示利米雅拿單亞大雅40瑪拿底拜沙賽沙賴41亞薩利示利米雅示瑪利雅42沙龍亞瑪利雅約瑟43尼波的子孫中有耶利瑪他提雅撒拔西比拿雅玳約珥比拿雅

44以上這些人都娶了外族女子為妻,其中有些還生了子女。

New Amharic Standard Version

ዕዝራ 10:1-44

ሕዝቡ ኀጢአቱን ተናዘዘ

1ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ወድቆ በሚጸልይበት፣ በሚናዘዝበትና በሚያለቅስበት ጊዜ ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች የሚገኙበት እጅግ ብዙ የእስራኤል ማኅበር በዙሪያው ተሰበሰበ፤ እነርሱም እንደዚሁ አምርረው አለቀሱ። 2ከዚያም ከኤላም ዘሮች አንዱ የሆነው የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፤ “በዙሪያችን ካሉት አሕዛብ፣ ባዕዳን ሴቶችን በማግባታችን ለአምላካችን ታማኞች ሆነን አልተገኘንም፤ ይህም ሆኖ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ። 3አሁንም እንደ ጌታዬ ምክርና የአምላካችንን ትእዛዝ እንደሚፈሩ ሰዎች እነዚህን ሴቶችና ልጆቻቸውን ለመስደድ በአምላካችን ፊት ቃል ኪዳን እንግባ፤ በሕጉም መሠረት ይፈጸም። 4ዕዝራ፣ ነገሩ በእጅህ ነው፤ ተነሥ! እኛም እንደግፍሃለን፤ በርትተህም አድርገው።”

5ዕዝራም ተነሥቶ ዋና ዋናዎቹ ካህናት፣ ሌዋውያንና እስራኤል ሁሉ የቀረበውን ሐሳብ እንዲፈጽሙ አስማላቸው፤ እነርሱም ማሉ። 6ከዚያም ዕዝራ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ክፍል ገባ፤ ምርኮኞቹ ታማኞች ሆነው ባለ መገኘታቸው ያለቅስ ነበር፤ በዚያም ምግብ አልቀመሰም፤ ውሃም አልጠጣም።

7ከዚያም ምርኮኞቹ ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ዐዋጅ ተነገረ፤ 8ዐዋጁም በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ማንም ሰው በሹማምቱና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሠረት ንብረቱ ሁሉ እንዲወረስ፣ ራሱም ከምርኮኞቹ ጉባኤ እንዲወገድ የሚያዝ ነበር።

9ስለዚህ በሦስት ቀን ውስጥ የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ በዘጠነኛው ወር በሃያኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ስለ ወቅቱ ጕዳይና ስለ ከባዱ ዝናብ በመጨነቅ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀምጠው ነበር። 10ከዚያም ካህኑ ዕዝራ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ታማኞች አልነበራችሁም፤ በእስራኤል በደል ላይ በደል በመጨመር ባዕዳን ሴቶችን አገባችሁ። 11አሁንም ለአባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር ተናዘዙ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ በዙሪያችሁ ካሉት አሕዛብና ከባዕዳን ሚስቶቻችሁ ተለዩ።”

12ጉባኤውም ሁሉ እንዲህ ሲሉ በታላቅ ድምፅ መለሱ፤ “እውነት ብለሃል፤ ያልኸውን መፈጸም ይገባናል። 13ይሁን እንጂ በዚህ የተሰበሰበው ሕዝብ ብዙ ነው፤ ወቅቱም ክረምት ነው፤ ስለዚህ ውጭ መቆም አንችልም፤ ከዚህም በላይ በዚህ ነገር ብዙ ኀጢአት ስለ ሠራን፣ ይህ ጕዳይ በአንድና በሁለት ቀን የሚያልቅ አይደለም። 14ስለዚህ ሹሞቻችን በማኅበሩ ሁሉ ምትክ መደረግ ያለበትን ያድርጉ። ከዚያም፣ በዚህ የተነሣ የመጣው የአምላካችን ብርቱ ቍጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ፣ በየከተሞቻችን ያሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ሁሉ በየከተማው ካሉት ሽማግሌዎችና ዳኞች ጋር በተወሰነው ቀን ይምጡ።” 15ይህንም ነገር የተቃወሙት ከሜሱላምና ከሌዋዊው ከሳባታይ ድጋፍ ያገኙት የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ብቻ ናቸው።

16ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጕዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤ 17በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡትን ወንዶች ሁሉ አጣርተው ጨረሱ።

ከባዕዳን ሴቶች ጋር የተጋቡት ሰዎች

18ከካህናት ዘሮች መካከል ባዕዳን ሴቶችን ያገቡት ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፤

ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ዘሮችና ከወንድሞቹ መካከል፤

መዕሤያ፣ አልዓዛር፣ ያሪብና ጎዶልያስ። 19እነዚህ ሁሉ ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ቃል በመግባት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም እያንዳንዳቸው ከመንጋው አንዳንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።

20ከኢሜር ዘሮች፤

አናኒና ዝባድያ።

21ከካሪም ዘሮች፤

መዕሤያ፣ ኤልያስ፣ ሸማያ፣ ይሒኤልና ዖዝያ።

22ከፋስኩር ዘሮች፤

ኤልዮዔናይ፣ መዕሤያ፣ ይስማኤል፣ ናትናኤል፣ ዮዛባትና ኤልዓሣ።

23ከሌዋውያኑም መካከል፤

ዮዛባት፣ ሰሜኢ፣ ቆሊጣስ የሚባል ቆልያ፣ ፈታያ፣ ይሁዳ፣ አልዓዛር።

24ከመዘምራኑም መካከል፤

ኤልያሴብ።

ከበር ጠባቂቹም፣

ሰሎም፣ ጤሌም፣ ኡሪ።

25ከሌሎቹ እስራኤላውያን መካከል፤

ከፋሮስ ዘሮች፤

ራምያ፣ ይዝያ፣ መልክያ፣ ሚያሚን፣ አልዓዛር፣ መልክያና በናያስ።

26ከኤላም ዘሮች፤

መታንያ፣ ዘካርያስ፣ ይሒኤል፣ አብዲ፣ ይሬሞትና ኤልያ።

27ከዛቱዕ ዘሮች፤

ዒሊዮዔናይ፣ ኢልያሴብ፣ መታንያ፣ ይሬሞት፣ ዛባድና ዓዚዛ።

28ከቤባይ ዘሮች፤

ይሆሐናን፣ ሐናንያ፣ ዛባይና አጥላይ።

29ከባኒ ዘሮች፤

ሜሱላም፣ መሉክ፣ ዓዳያ፣ ያሱብ፣ ሸዓልና ራሞት።

30ከፈሐት ሞዓብ ዘሮች፤

ዓድና፣ ክላል፣ በናያስ፣ መዕሤያ፣ መታንያ፣ ባስልኤል፣ ቢንዊና ምናሴ።

31ከካሪም ዘሮች፤

አልዓዛር፣ ይሺያ፣ መልክያ፣ ሸማያ፣ ስምዖን፣ 32ብንያም፣ መሉክና ሰማራያ።

33ከሐሱም ዘሮች፤

መትናይ፣ መተታ፣ ዛባድ፣ ኤሊፋላት፣ ይሬማይ፣ ምናሴና ሰሜኢ።

34ከባኒ ዘሮች፤

መዕዳይ፣ ዓምራም፣ ኡኤል፣ 35በናያስ፣ ቤድያ፣ ኬልቅያ፣ 36ወንያ፣ ሜሪሞት፣ ኤልያሴብ፣ 37መታንያ፣ መትናይና የዕሡ።

38ከቢንዊ ዘሮች፤

ሰሜኢ10፥37-38 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም (እንዲሁም መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል 9፥34) ይመ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ የዕሡ፣ ባኒና ቤኑዊ ይላል።39ሰሌምያ፣ ናታን፣ ዓዳያ፣

40መክነድባይ፣ ሴሴይ፣ ሸራይ፣ 41ኤዝርኤል፣

ሰሌምያ፣ ሰማራያ፣ 42ሰሎም፣ አማርያና ዮሴፍ።

43ከናባው ዘሮች፤

ይዒኤል፣ መቲትያ፣ ዛባድ፣ ዘቢና፣ ያዳይ፣ ኢዮኤልና በናያስ።

44እነዚህ ሁሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ናቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ ከእነዚህ ሴቶች ልጆችን ወልደው ነበር።10፥44 ወይም ከልጆቻቸው ጋር ላኳቸው