马太福音 22 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

马太福音 22:1-46

王宴客的比喻

1耶稣又用比喻对他们说: 2“天国就像一个王为儿子筹备婚宴。 3他派奴仆去请受邀的客人,可是客人都不肯赴宴。 4王再派其他奴仆去,说,‘去告诉被邀请的人,我的宴席已经备好,公牛和肥畜都宰了,一切都预备妥当,来赴婚宴吧!’ 5那些人却毫不理会地走了,一个去种田,一个去做买卖, 6其余的竟然抓住王的奴仆,把他们羞辱一番后杀了。 7王大怒,派军队去剿灭凶手,烧毁他们的城。

8“然后,他对奴仆说,‘婚宴已预备好了,只是被邀请的人不配。 9所以你们到街头巷尾,把所有见到的人都请来。’ 10奴仆到街上把遇到的人都请了来,好人坏人都有,大厅里满了客人。

11“王出来会见在座的客人,发现有一个人没有穿礼服, 12就问他,‘朋友,你来这里怎么不穿婚宴的礼服呢?’那人无言以对。 13王便吩咐侍从,‘把他手脚绑起来丢到外面的黑暗里,让他在那里哀哭切齿。’”

14耶稣又说:“被邀请的人多,选上的人少。”

以纳税问题刁难耶稣

15那时,法利赛人出去策划怎样从耶稣的话里找把柄陷害祂。 16他们派了自己的门徒跟希律党人一同去问耶稣:“老师,我们知道你诚实无伪,按真理传上帝的道,你不徇情面,不以貌取人。 17那么请告诉我们,纳税给凯撒对不对呢?”

18耶稣看出了他们的恶意,就说:“你们这些伪君子,为什么试探我呢? 19拿一个纳税用的钱币来给我看。”他们就拿给祂一个银币。

20耶稣问他们:“上面刻的是谁的像和名号?”

21他们说:“凯撒的。”

耶稣说:“那么,属于凯撒的东西应该给凯撒,属于上帝的东西应该给上帝。” 22他们听了很惊奇,只好离开祂走了。

论复活

23同一天,不相信死人会复活的撒都该人也来问耶稣, 24说:“老师,摩西说,‘如果一个人死了,没有儿女,只留下妻子,他的兄弟就当娶嫂嫂,替哥哥传宗接代。’ 25从前,我们这里有弟兄七人,老大结了婚,没有孩子就死了,把妻子留给了弟弟。 26二弟、三弟一直到七弟都相继娶了嫂嫂,都没留下孩子。 27最后,那女人也死了。 28那么,到复活的时候,她将是谁的妻子呢?因为他们都娶过她。”

29耶稣说:“你们弄错了。你们不明白圣经,也不知道上帝的能力。 30因为到复活的时候,人们将不娶也不嫁,就像天上的天使一样。

31“关于死人复活的事,难道你们没有读过上帝对你们说过的话吗? 32祂说,‘我是亚伯拉罕的上帝,以撒的上帝,雅各的上帝。’上帝不是死人的上帝,而是活人的上帝。” 33众人听到祂的教导都很惊奇。

最大的诫命

34法利赛人听见耶稣使撒都该人无言以对,就聚集在一起。 35其中有位律法专家试探耶稣说: 36“老师,请问律法中哪一条诫命最重要呢?”

37耶稣回答说:“‘你要全心、全情、全意爱主——你的上帝’, 38这是第一条也是最重要的诫命。 39第二条也相似,就是‘要爱邻如己’。 40律法和先知的全部教导都以这两条诫命为基础。”

基督的身份

41耶稣趁着法利赛人聚在那里,就问他们: 42“你们对基督有何看法?祂是谁的后裔?”他们答道:“大卫的后裔。”

43耶稣说:“那么,为什么大卫受圣灵感动,称祂为主呢?大卫曾说,

44“‘主对我主说,

你坐在我的右边,

等我使你的仇敌伏在你脚下。’

45既然大卫称基督为主,基督又怎么会是大卫的后裔呢?” 46没人能回答耶稣的问题。从此再没有人敢用问题来刁难耶稣了。

New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 22:1-46

በሰርግ ድግስ ላይ የተጠሩ ሰዎች ምሳሌ

22፥2-14 ተጓ ምብ – ሉቃ 14፥16-24

1ኢየሱስም እንደ ገና እንዲህ የሚል ምሳሌ ነገራቸው፤ 2“መንግሥተ ሰማይ ለልጁ ሰርግ የደገሰን ንጉሥ ትመስላለች፤ 3ንጉሡም የተጋበዙትን ሰዎች እንዲጠሩ አገልጋዮቹን ላከ፤ እነርሱ ግን አንመጣም አሉ።

4“እንደ ገናም ሌሎች አገልጋዮች ልኮ፣ ‘የተጋበዙትን፣ እነሆ፣ በሬዎችንና የሠቡ ከብቶቼን ዐርጄ ድግሱን አዘጋጅቻለሁ፤ ሁሉም ነገር ዝግጁ ስለሆነ፣ ወደ ሰርጉ ኑ በሏቸው’ አለ።

5“ተጋባዦቹ ግን ጥሪውን ችላ ብለው፣ አንዱ ወደ ዕርሻው ሌላው ወደ ንግዱ ሄደ፤ 6የቀሩትም አገልጋዮቹን በመያዝ አጕላልተው ገደሏቸው። 7ንጉሡም በመቈጣት ሰራዊቱን ልኮ ገዳዮቻቸውን አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።

8“ከዚያም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘የሰርጉ ድግስ ዝግጁ ነው፤ ነገር ግን የተጋበዙት የሚገባቸው ሆነው ስላልተገኙ፣ 9ወደ መንገድ መተላለፊያ ወጥታችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ድግስ ጥሩ።’ 10አገልጋዮቹም ወደ መንገድ ወጥተው ያገኙትን መልካሙንም ክፉውንም ሁሉ ሰብስበው የሰርጉን አዳራሽ በእንግዶች ሞሉት።

11“ንጉሡም የተጋበዙትን እንግዶች ለማየት ሲገባ፣ አንድ የሰርግ ልብስ ያልለበሰ ሰው አየ፤ 12እንዲህም አለው፤ ‘ወዳጄ ሆይ፤ የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት እዚህ ልትገባ ቻልህ?’ ሰውየው ግን የሚመልሰው ቃል አልነበረውም።

13“ንጉሡም አገልጋዮቹን፣ ‘እጅና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል’ አላቸው፤ 14የተጠሩት ብዙዎች፣ የተመረጡት ግን ጥቂቶች ናቸውና።”

ግብር ስለ መክፈል

22፥15-22 ተጓ ምብ – ማር 12፥13-17ሉቃ 20፥20-26

15ከዚህ በኋላ ፈሪሳውያን ወጥተው በመሄድ በአፍ ዕላፊ እንዴት እንደሚያጠምዱት ተማከሩ። 16ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ወገኖች ጋር ወደ እርሱ ልከው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ እውነተኛና የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት የምታስተምር እንደ ሆንህ፣ ለማንም ሳታዳላ ሁሉን በእኩልነት እንደምትመለከት እናውቃለን፤ 17ንገረን፤ ምን ይመስልሃል? ለመሆኑ ለቄሣር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?”

18ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን በመረዳት እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ግብዞች ለምን በነገር ልታጠምዱኝ ትሻላችሁ? 19ለግብር የሚከፈለውን ገንዘብ እስቲ አሳዩኝ።” እነርሱም አንድ ዲናር አመጡለት። 20እርሱም፣ “በዚህ ገንዘብ ላይ የሚታየው መልክ የማን ነው? ጽሕፈቱስ የማን ነው?” አላቸው።

21እነርሱም፣ “የቄሣር ነው” አሉት።

እርሱም መልሶ፣ “እንግዲያውስ የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ” አላቸው።

22ይህን ሲሰሙ ተደነቁ፤ ትተውትም ሄዱ።

ስለ ሙታን ትንሣኤ

22፥23-33 ተጓ ምብ – ማር 12፥18-27ሉቃ 20፥27-40

23የሙታን ትንሣኤ የለም ብለው የሚያምኑ ሰዱቃውያን በዚያኑ ቀን ወደ ኢየሱስ ቀርበው እንዲህ ብለው ጠየቁት፤ 24“መምህር ሆይ፤ ሙሴ፣ ‘አንድ ሰው ከሚስቱ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ የሟቹን ሚስት አግብቶ ለእርሱ ዘር ይተካለት’ ብሏል። 25በእኛ ዘንድ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፤ የመጀመሪያው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ በመሞቱ፣ ሚስቱን ወንድሙ አገባት፤ 26እንደዚሁ ደግሞ ሁለተኛውም፣ ሦስተኛውም እስከ ሰባተኛው ድረስ በዚህ ሁኔታ ሞቱ። 27በመጨረሻ ሴትየዋ ራሷ ሞተች። 28ስለዚህ ሁሉም ስላገቧት በትንሣኤ ቀን ከሰባቱ ለየትኛው ሚስት ትሆናለች?”

29ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ቅዱሳት መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታውቁ ትስታላችሁ፤ 30ከትንሣኤ በኋላ ሰዎች እንደ ሰማይ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፤ አይጋቡም። 31ስለ ሙታን ትንሣኤ ግን እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ የተናገራችሁን አላነበባችሁምን? 32‘እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ።’ እግዚአብሔር የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም።”

33ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ በትምህርቱ ተደነቁ።

ታላቁ ትእዛዝ

22፥34-40 ተጓ ምብ – ማር 12፥28-31

34ኢየሱስ ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው ሰምተው፣ ፈሪሳውያን በአንድነት ተሰበሰቡ፤ 35ከእነርሱም አንድ የኦሪት ሕግ ዐዋቂ፣ ሊፈትነው ፈልጎ እንዲህ አለው፤ 36“መምህር ሆይ፤ ከሕግ ሁሉ የሚበልጠው የትኛው ትእዛዝ ነው?”

37እርሱም እንዲህ አለው፤ “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤’ 38ይህ የመጀመሪያውና ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ ነው፤ 39ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል፤ ይህም፣ ‘ጎረቤትህን እንደ ራስህ ውደድ’ የሚለው ነው፤ 40ሕግና ነቢያት በሙሉ በእነዚህ ሁለት ትእዛዞች ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው።”

ክርስቶስ የማን ልጅ ነው?

22፥41-46 ተጓ ምብ – ማር 12፥35-37ሉቃ 20፥41-44

41ፈሪሳውያን ተሰብስበው ሳሉ ኢየሱስ፣ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፤ 42“ስለ ክርስቶስ22፥42 ወይም መሲሑ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው?”

እነርሱም፣ “የዳዊት ልጅ ነው” አሉት።

43እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ታዲያ፣ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ለምን ‘ጌታዬ’ ይለዋል? ለምንስ፣ እንዲህ ይለዋል?

44“ ‘እግዚአብሔር ጌታዬን፤

“ጠላቶችህን ከእግርህ በታች

እስካንበረከክልህ ድረስ፣

በቀኜ ተቀመጥ።” ’

45ስለዚህ ዳዊት፣ ‘ጌታዬ’ ብሎ ከጠራው፣ እንዴት ልጁ ሊሆን ይችላል?” 46አንድ ቃል ሊመልስለት የቻለ ወይም ከዚያን ቀን ጀምሮ ሊጠይቀው የደፈረ ማንም አልነበረም።