马太福音 10 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

马太福音 10:1-42

差遣使徒

1耶稣叫了十二位门徒来,将权柄赐给他们,使他们能够赶出污鬼、医治各样的疾病。 2以下是这十二位使徒的名字:

首先是西门,又名彼得,还有彼得的兄弟安得烈西庇太的儿子雅各雅各的兄弟约翰3腓力巴多罗买多马、税吏马太亚勒腓的儿子雅各达太4激进党人10:4 激进党人”指当时激进的犹太民族主义者,常以行动反抗统治他们的罗马政府。西门和出卖耶稣的加略犹大

5耶稣差遣这十二个人出去,嘱咐他们:“外族人的地方不要去,撒玛利亚人的城镇也不要进, 6要到以色列人当中寻找迷失的羊。

7“你们要边走边传,‘天国临近了!’ 8要医好病人,叫死人复活,使麻风病人痊愈,赶走邪灵。你们白白地得来,也应当白白地给人。 9出门时钱袋里不要带金、银、铜币, 10不要带行李、备用的衣服、鞋子或手杖,因为做工的理应得到供应。 11你们无论到哪座城、哪个村,要在那里寻找愿意接待你们的人,然后住在他家,一直住到离开。 12你们进他家的时候,要为他们祝福。 13如果那家配得福气,你们的祝福必临到他们;如果那家不配蒙福,祝福仍归给你们。 14如果有人不接待你们,不听你们传的信息,你们离开那家或那城时,就把脚上的尘土跺掉作为对他们的警告。 15我实在告诉你们,在审判之日,他们所受的痛苦比所多玛蛾摩拉所受的还大!

将临的迫害

16“听着,我差你们出去,就好像使羊走进狼群一般。所以,你们要像蛇一样机灵,像鸽子一样驯良。

17“你们要小心谨慎,因为人们要把你们送上法庭,也要在会堂里鞭打你们。 18你们要因我的缘故被带到官长和君王面前,在他们和外族人面前为我做见证。 19当你们被押送公堂时,不用顾虑如何应对,或说什么话,那时必会赐给你们当说的话。 20因为那时候说话的不是你们自己,乃是你们父的灵借着你们说话。

21“那时,人必把自己的弟兄置于死地,父亲必把儿子置于死地,儿女必反叛父母,置他们于死地。 22你们将为我的名而被众人憎恨,但坚忍到底的必定得救。 23如果你们在一个地方遭迫害,就避到另一个地方。我实在告诉你们,没等你们走遍以色列的城镇,人子就来了。

24“学生不能高过老师,奴仆也不能大过主人。 25学生顶多和老师一样,奴仆顶多和主人一样。连一家之主都被骂成是别西卜10:25 别西卜”是鬼王的名字。,更何况祂的家人呢?

26“不要害怕那些迫害你们的人。因为掩盖的事终会暴露出来,隐藏的秘密终会被人知道。 27你们要把我私下告诉你们的当众讲出来,你们要在屋顶上把听到的悄悄话宣告出来。 28那些只能杀害身体,不能毁灭灵魂的人,不用怕他们。但要畏惧那位有权将身体和灵魂一同毁灭在地狱里的上帝。 29两只麻雀不是只卖一个铜钱吗?然而没有天父的许可,一只也不会掉在地上。 30就连你们的头发都被数过了。 31所以不要害怕,你们比许多麻雀更贵重!

32“凡公开承认我的,我在天父面前也必承认他; 33凡公开不承认我的,我在天父面前也必不承认他。

跟从主的代价

34“不要以为我来了会让天下太平,我并非带来和平,乃是带来刀剑。 35因为我来是要叫儿子与父亲作对,女儿与母亲作对,媳妇与婆婆作对, 36家人之间反目成仇。

37“爱父母过于爱我的人不配做我的门徒;爱儿女过于爱我的人不配做我的门徒; 38不肯背起他的十字架跟从我的人不配做我的门徒。 39试图保全自己生命的反而会失去生命,但为我舍弃生命的反而会得到生命。

得赏赐

40“人接待你们就是接待我,接待我就是接待差我来的那位。 41因为某人是先知而接待他的,必得到和先知一样的赏赐;因为某人是义人而接待他的,必得到和义人一样的赏赐。 42人若接待我门徒中最卑微的人,并因为他是我的门徒而给他一杯凉水喝,我实在告诉你们,那人必得到赏赐。”

New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 10:1-42

የዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት መላክ

10፥2-4 ተጓ ምብ – ማር 3፥16-19ሉቃ 6፥14-16ሐሥ 1፥13

10፥9-15 ተጓ ምብ – ማር 6፥8-11ሉቃ 9፥3-510፥4-12

10፥19-22 ተጓ ምብ – ማር 13፥11-13ሉቃ 21፥12-17

10፥26-33 ተጓ ምብ – ሉቃ 12፥2-9

10፥3435 ተጓ ምብ – ሉቃ 12፥51-53

1ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ጠርቶ ርኩሳን መናፍስትን እንዲያወጡ፣ ደዌንና ሕማምን ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣንን ሰጣቸው።

2የዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ስም የሚከተለው ነው፦ መጀመሪያ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፣ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፣ 3ፊልጶስና በርተሎሜዎስ፣ ቶማስና ቀረጥ ሰብሳቢው ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ታዴዎስ የተባለው ልብድዮስ፣ 4ቀነናዊው10፥4 ቀነናዊ የሚለው ቃል አራማይክ ሲሆን፣ ቀነናውያን የተባሉት በዚያን ጊዜ የሮምን መንግሥት የሚቃወሙ የፖለቲካ ቡድን አባላት ነበሩ። ስምዖንና በኋላ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው አስቆሮቱ ይሁዳ።

5እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን ኢየሱስ እንዲህ ከሚል ትእዛዝ ጋር ላካቸው፤ “ወደ አሕዛብ አትሂዱ፤ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ። 6ይልቁንስ የእስራኤል ቤት ወደ ሆኑት ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ። 7ሄዳችሁም፣ ‘መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች’ ብላችሁ ስበኩ። 8በሽተኞችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን10፥8 የግሪኩ ቃል የግድ ከለምጽ ጋር ብቻ የተያያዘ ሳይሆን የቈዳ በሽታዎችን ያመለክታል። አንጹ፤ አጋንንትን አስወጡ፤ በነጻ የተቀበላችሁትንም በነጻ ስጡ። 9በመቀነታችሁ ወርቅም ሆነ ብር ወይም መዳብ አትያዙ። 10ለመንገዳችሁም ከረጢት፣ ትርፍ እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ የዕለት ጕርሱ ይገባዋልና።

11“ወደ አንድ ከተማ ወይም መንደር ስትገቡ ሊቀበላችሁ ፈቃደኛ የሆነ ሰው ፈልጋችሁ በቤቱ ዕረፉ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያው ቈዩ። 12ወደ ማንኛውም ሰው ቤት ስትገቡ ሰላምታ አቅርቡ። 13ቤቱም የሚገባው ሆኖ ከተገኘ፣ ሰላማችሁ ይድረሰው፤ የማይገባው ከሆነ ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለስላችሁ። 14ማንም ሰው ሊያስተናግዳችሁ ወይም የምትናገሩትን ሊሰማ ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ከቤቱ ወይም ከከተማው ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ። 15እውነት እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን በዚያች ከተማ ከሚደርሰው ቅጣት ይልቅ በሰዶምና በገሞራ የሚደርሰው ይቀልላል።

16“እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች እንደ ርግብ የዋሃን ሁኑ።

17“ሰዎች ይዘው ለፍርድ ወደ ሸንጎ ያቀርቧችኋል፤ በምኵራቦቻቸውም ይገርፏችኋል፤ ስለዚህ ከእነርሱ ተጠንቀቁ። 18በእኔ ምክንያት ወደ ገዦችና ወደ ነገሥታት ትወሰዳላችሁ፤ በእነርሱና በአሕዛብም ፊት ምስክር ትሆናላችሁ። 19በምትያዙበትም ጊዜ ምን እንናገራለን፣ ምንስ እንመልሳለን ብላችሁ አትጨነቁ፤ በዚያን ጊዜ የምትናገሩት ይሰጣችኋል፤ 20በእናንተ የሚናገረው የሰማዩ አባታችሁ መንፈስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።

21“ወንድም ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ አባትም ልጁን፤ ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያምፃሉ፤ ያስገድሏቸዋልም። 22ስለ ስሜ ሰዎች ሁሉ ይጠሏችኋል፤ ነገር ግን እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል። 23በአንድ ስፍራ ሲያሳድዷችሁ ወደ ሌላ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁ፣ የእስራኤልን ከተሞች ሳታዳርሱ የሰው ልጅ ይመጣል።

24“ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፣ ሎሌም ከጌታው አይበልጥም፤ 25ደቀ መዝሙር መምህሩን፣ ሎሌም ጌታውን ከመሰለ ይበቃዋል። ባለቤቱን ‘ብዔልዜቡል’ ካሉት፣ ቤተ ሰዎቹንማ እንዴት አብልጠው አይሏቸውም!

26“ስለዚህ አትፍሯቸው፤ የተሸፈነ መገለጡ፣ የተደበቀ መውጣቱ አይቀርምና። 27በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን አውሩት፤ በጆሯችሁ የሰማችሁትን በአደባባይ ዐውጁት፤ 28ሥጋን መግደል እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ማጥፋት የሚቻለውን ፍሩ። 29በአንድ ሳንቲም10፥29 ግሪኩ አንድ አሳሪዮን ይላል። ከሚሸጡት ሁለት ድንቢጦች አንዲቷ እንኳ ያለ አባታችሁ ፈቃድ ምድር ላይ አትወድቅም። 30የራስ ጠጕራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር የተቈጠረ ነው። 31ስለዚህ አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች ይልቅ ዋጋችሁ የከበረ ነው።

32“በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ፣ እኔም በሰማይ ባለው አባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ 33ነገር ግን በሰው ፊት የሚክደኝን፣ እኔም በሰማይ ባለው አባቴ ፊት እክደዋለሁ።

34“እኔ የመጣሁት ሰላምን በምድር ለማስፈን አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማውረድ አልመጣሁም። 35እኔ የመጣሁት

“ ‘ልጅን ከአባት፣

ሴት ልጅን ከእናቷ

ምራትንም ከዐማቷ ለመለያየት ነው፤

36የሰው ጠላቶቹ፣ የገዛ ቤተ ሰዎቹ ይሆናሉ።’

37“ከእኔ ይልቅ እናቱን ወይም አባቱን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም። 38መስቀሉን ተሸክሞ የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባውም። 39ሕይወቱን ሊያድን የሚፈልግ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን ስለ እኔ አሳልፎ የሚሰጥ ግን ያገኛታል።

40“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። 41ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል። 42ስለዚህ እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ከእነዚህ ከታናናሾች ለአንዱ ደቀ መዝሙሬ በመሆኑ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውሃ ቢሰጠው ዋጋውን አያጣም።”