雅各书 5 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

雅各书 5:1-20

警告为富不仁者

1你们这些富有的人啊!为那将要临到你们身上的灾难痛哭哀号吧! 2你们的财物朽坏了,衣服也被虫蛀了。 3你们的金银生了锈,那锈必要指控你们,像火一样吞噬你们的身体。在末世的日子里,你们只知道积攒财宝。 4工人替你们收割庄稼,你们却克扣他们的工钱。那工钱发出不平的呼喊,工人的冤声已经传到万军之主的耳中了。 5你们在世上奢侈享乐,在被宰杀的日子里,把自己养得肥肥胖胖。 6你们冤枉好人、残害无辜,他们也没有反抗。

要忍耐到底

7弟兄姊妹,你们要一直忍耐到主来。你们看农夫怎样耐心等候地里宝贵的出产,等候秋雨和春雨的降临。 8同样,你们也要忍耐,心志坚定,因为主快来了。 9弟兄姊妹,不要互相埋怨,免得受审判。你们看,审判的主已经站在门外了。 10弟兄姊妹,你们要效法从前奉主的名说话的先知,以他们的受苦和忍耐为榜样。 11我们认为那些忍耐到底的人是有福的。你们都知道约伯的忍耐,也知道主最终怎样待他,因为主充满怜悯和慈悲。

12我的弟兄姊妹,最重要的是不可起誓,不可指着天起誓,也不可指着地起誓,不可指着任何东西起誓。你们说话,是就说是,不是就说不是,免得你们受审判。

祷告的力量

13你们中间正在受苦的人应该祷告,喜乐的人应该唱歌赞美, 14生病的人应该请教会的长老来,奉主的名用油抹他的身体并为他祷告。 15出于信心的祷告必能使病人痊愈,主必使他康复。倘若他犯了罪,也必得到赦免。 16所以你们要彼此认罪,互相代祷,好得到医治。义人的祷告有极大的力量和功效。 17以利亚先知和我们一样同是血肉之躯,他恳切地祈求不要下雨,结果三年半没有下雨。 18后来他再祷告求雨,天就降雨,地也长出了庄稼。

19我的弟兄姊妹,如果有人领一个偏离真道的人归回正路, 20他该知道:使一个迷途中的罪人归回正路就是救一个灵魂脱离死亡,并且会遮盖许多罪。

New Amharic Standard Version

ያዕቆብ 5:1-20

ለጨካኝ ሀብታሞች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

1እንግዲህ እናንተ ሀብታሞች ስሙ፤ ስለሚደርስባችሁ መከራ አልቅሱ፤ ዋይ ዋይም በሉ። 2ሀብታችሁ ሻግቷል፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል። 3ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጓል፤ ዝገቱም በእናንተ ላይ ይመሰክራል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል፤ ለመጨረሻው ዘመን ሀብትን አከማችታችኋል። 4ልብ በሉ፤ ዕርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የዐጫጆቹም ጩኸት ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው ጌታ ጆሮ ደርሷል። 5በምድርም ላይ በምቾትና በመቀማጠል ኖራችኋል፤ ለዕርድ5፥5 ወይም ለድግስ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል። 6እናንተን ያልተቃወሙትን ንጹሓን ሰዎች ኰንናችኋል፤ ገድላችኋልም።

በመከራ ውስጥ መታገሥ

7እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ታገሡ። ገበሬ መሬቱ መልካምን ፍሬ እስከሚሰጥ ድረስ እንዴት እንደሚታገሥ፣ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እንዴት እንደሚጠባበቅ አስተውሉ። 8እናንተም እንዲሁ ታገሡ፤ ልባችሁንም አጽኑ፤ ምክንያቱም የጌታ መምጫ ተቃርቧል። 9ወንድሞች ሆይ፤ እርስ በርሳችሁ አታጕረምርሙ፤ አለዚያ ይፈረድባችኋል፤ እነሆ፤ ፈራጁ በበር ላይ ቆሟል።

10ወንድሞች ሆይ፤ በጌታ ስም የተናገሩትን ነቢያት የመከራና የትዕግሥት ምሳሌ አድርጋችሁ ተመልከቱ። 11በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው።

12ከሁሉም በላይ ወንድሞቼ ሆይ፤ በሰማይ ወይም በምድር ወይም በማናቸውም ነገር ቢሆን አትማሉ፤ “አዎ” ቢሆን አዎ ይሁን፤ “አይደለም” ቢሆን አይደለም ይሁን፤ አለዚያ ይፈረድባችኋል።

ከእምነት የሆነ ጸሎት

13ከእናንተ መካከል በመከራ ውስጥ ያለ አለ? እርሱ ይጸልይ፤ የተደሰተ አለ? የምስጋና መዝሙር ይዘምር። 14ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። 15በእምነት የቀረበ ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሰዋል፤ ጌታም ያስነሣዋል፤ ኀጢአትም ሠርቶ ከሆነ፣ ይቅር ይባላል። 16ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።

17ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ፤ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ተኩል ዝናብ አልዘነበም። 18እንደ ገናም ጸለየ፤ ዝናብም ከሰማይ ዘነበ፤ ምድርም ፍሬዋን ሰጠች።

19ወንድሞቼ ሆይ፤ ከእናንተ አንዱ ከእውነት ቢስትና ሌላው ቢመልሰው፣ 20ይህን አስተውሉ፤ ኀጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልስ ሰው ነፍሱን ከሞት ያድነዋል፤ ብዙ ኀጢአትንም ይሸፍናል።