诗篇 118 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 118:1-29

第 118 篇

为胜利而感恩

1你们要称谢耶和华,

因为祂是美善的,

祂的慈爱永远长存。

2以色列人说:

“祂的慈爱永远长存。”

3亚伦家说:

“祂的慈爱永远长存。”

4愿那些敬畏耶和华的人说:

“祂的慈爱永远长存。”

5我在苦难中求告耶和华,

祂就答应我,救我脱离困境。

6有耶和华与我同在,

我必不惧怕,

人能把我怎么样?

7耶和华与我同在,帮助我,

我必看见那些恨我的人一败涂地。

8投靠耶和华胜过倚靠人。

9投靠耶和华胜过倚靠权贵。

10列国围住我,

但我靠着耶和华消灭了他们。

11他们四面围住我,

但我靠着耶和华消灭了他们。

12他们如蜜蜂围住我,

然而他们必像燃烧的荆棘,

转瞬消逝;

我靠着耶和华必消灭他们。

13我受到猛烈的攻击,

几乎要倒下了,

但耶和华帮助了我。

14耶和华是我的力量,

是我的诗歌;

祂拯救了我。

15义人的帐篷里传出胜利的欢呼声:

“耶和华伸出右手施展了大能!

16耶和华高举右手,

耶和华的右手施展了大能!”

17我必不至于死,

我要活着,

并要述说耶和华的作为。

18耶和华虽然重重地惩罚我,

却没有置我于死地。

19给我打开圣殿的门吧,

我要进去称谢耶和华。

20这是耶和华的门,

义人都可以进去。

21耶和华啊!我称谢你,

因为你听了我的祷告,

拯救了我。

22工匠丢弃的石头已成了房角石。

23这是耶和华的作为,

在我们看来奇妙莫测。

24这是耶和华得胜的日子,

我们要欢喜快乐。

25耶和华啊,求你拯救我们;

耶和华啊,求你使我们亨通。

26奉耶和华之名而来的当受称颂!

我们要在耶和华的殿中祝福你们。

27耶和华是上帝,

祂的光照亮我们。

要用绳索拴住祭牲,

牵到祭坛的角那里。

28你是我的上帝,我要称谢你;

你是我的上帝,我要尊崇你。

29你们要称谢耶和华,

因为祂是美善的,

祂的慈爱永远长存。

New Amharic Standard Version

መዝሙር 118:1-29

መዝሙር 118

ለዳስ በዓል የቀረበ የጕዞ መዝሙር

1እግዚአብሔር ቸር ነውና አመስግኑት፤

ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

2የእስራኤል ሕዝብ፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበል።

3የአሮን ቤት፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበል።

4እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣

“ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበሉ።

5በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤

እግዚአብሔርም መለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ።

6እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

7ይረዳኝ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፤

የጠላቶቼንም ውድቀት አያለሁ።

8ሰውን መከታ ከማድረግ ይልቅ፣

በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።

9በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ፣

በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።

10ሕዝቦች ሁሉ ከበቡኝ፤

ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

11መክበቡንስ በየአቅጣጫው ከበቡኝ፤

ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

12እንደ ንብ መንጋ ከበቡኝ፤

ነገር ግን እንደሚነድድ እሾኽ ከሰሙ፤

በርግጥም በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

13ተገፍትሬ ልወድቅ ተንገደገድሁ፤

እግዚአብሔር ግን ረዳኝ።

14እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤

አዳኝ ሆነልኝ።

15በጻድቃን ድንኳን የእልልታና የሆታ ድምፅ፣

እንዲህ እያለ ያስተጋባል፤

የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች፤

16የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለች፤

የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች።”

17ተርፌ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም፤

የእግዚአብሔርንም ሥራ ገና እናገራለሁ።

18መገሠጹን እግዚአብሔር እጅግ ገሥጾኛል፤

ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም።

19የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤

በዚያ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።

20ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤

ጻድቃን በእርሷ በኩል ይገባሉ።

21ሰምተህ መልሰህልኛልና፣

አዳኝም ሆነህልኛልና አመሰግንሃለሁ።

22ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣

እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ።

23እግዚአብሔር ይህን አደረገ፤

ለዐይናችንም ድንቅ ናት።

24እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤

በእርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን።

25እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አድነን፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አሳካልን።

26በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው።

ከእግዚአብሔር ቤት ባረክናችሁ።

27እግዚአብሔር አምላክ ነው፤

ብርሃኑንም በላያችን አበራ፤

እስከ መሠዊያው118፥27 ወይም የክብረ በዓልን መሥዋዕት በገመድ ማሰር ወይም መውሰድ ቀንዶች ድረስ በመውጣት፣

ዝንጣፊ ይዛችሁ በዓሉን ከሚያከብሩት ጋር ተቀላቀሉ።

28አንተ አምላኬ ነህ፤ አመሰግንሃለሁ፤

አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።

29ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤

ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።