耶利米书 3 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

耶利米书 3:1-25

1耶和华说:“如果丈夫休掉妻子,

妻子离去另嫁别人,

前夫怎会再娶她呢?

那样做岂不完全玷污了土地吗?

你曾与许多情人苟合,

现在要归向我吗?

2“你举目看看那些光秃的高山,

哪里没有被你玷污过呢?

你坐在路旁等候情郎,

就像旷野的游牧者,

你的淫乱恶行玷污了土地。

3因此,秋雨不降,

春雨不来。

你却仍然不知羞耻,

一副娼妓的嘴脸。

4你不是刚对我说,

‘我父啊!你从我年幼时就做我的朋友。

5难道你会永远发怒、

怀恨到底吗?’

你虽然这样说,

却仍大肆作恶。”

呼吁不忠的以色列悔改

6约西亚王执政期间,耶和华对我说:“你看见以色列的不忠不贞了吗?她在高山上、在绿荫下放纵情欲。 7我以为她放纵之后会回到我身边,她却执迷不悟。她不忠的妹妹犹大也看见了这事。 8因为以色列不忠贞,我给她休书,把她休掉。她不忠的妹妹犹大却不害怕,竟也去淫乱。 9以色列肆意淫乱,拜石头木头,玷污了土地。 10尽管如此,她不忠的妹妹犹大只是假装归向我,并不诚心。这是耶和华说的。”

11耶和华对我说:“不忠贞的以色列比奸诈的犹大罪过还轻。 12你去向北方宣告,

“‘耶和华说,

不忠贞的以色列啊,回转吧!

我必不向你们发怒,

因为我充满慈爱,

不会永远怀怒。’

这是耶和华说的。

13‘你必须要承认自己的罪,

承认背叛了你的上帝耶和华,

在绿荫树下祭拜各种外邦的神明,

不听从我的话。’

这是耶和华说的。

14“‘不忠贞的子民啊,回转吧!

因为我是你们的主人3:14 主人”或译作“丈夫”。

我要从你们中间选些人带回锡安

每座城邑或每个宗族选一两个人。’

这是耶和华说的。

15“我要赐给你们合我心意的牧人,让他们用知识与智慧牧养你们。 16你们在地上繁衍昌盛的时候,人们不会再提及耶和华的约柜,不会再把它放在心上,不会再感到需要它,也不会再造一个。这是耶和华说的。 17那时,耶路撒冷会被称为‘耶和华的宝座’,万国都要聚集在耶路撒冷敬拜耶和华,不再执迷不悟地作恶。 18那时,犹大人必与以色列人一同从北方来到我赐给你们祖先作基业的地方。

19“我曾想,我多么愿意把你们当成我的儿女,

赐给你们万国中最肥美的土地。

我原以为你们会叫我‘父亲’,

再不离弃我。

20然而,以色列人啊!

你们竟对我不忠,

就像妻子不忠于丈夫。

这是耶和华说的。”

21从光秃的山头传来声音,

以色列子民哭泣呼求的声音,

因为他们走入歧途,

忘掉了他们的上帝耶和华。

22耶和华说:“不忠贞的子民啊,

归来吧!

我要医治你们不忠贞的病。”

他们说:“是的,我们要到你面前,

因为你是我们的上帝耶和华。

23在高山丘陵上狂欢、

拜偶像真是枉然,

唯有我们的上帝耶和华才能拯救以色列

24“从我们年幼时,那些可耻的神像就吞噬了我们祖先辛苦得来的牛羊和儿女。 25我们躺在自己的羞耻中,让我们的耻辱遮盖我们吧!因为我们和我们的祖先都得罪了我们的上帝耶和华,我们自幼至今一直没有顺服我们的上帝耶和华。”

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 3:1-25

1“ሰው ሚስቱን ቢፈታ፣

እርሷም ሄዳ ሌላ ሰው ብታገባ፣

ወደ እርሷ ይመለሳልን?

ምድሪቱስ ፈጽማ አትረክስምን?

አንቺ ግን ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር አመንዝረሻል፤

ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽን?”

ይላል እግዚአብሔር

2“እስቲ ቀና ብለሽ ጭር ያሉትን ኰረብቶች ተመልከቺ፣

በርኩሰት ያልተጋደምሽበት ቦታ ይገኛልን?

በበረሓ እንደ ተቀመጠ ዘላን ዐረብ፣

በየመንገዱ ዳር ተቀምጠሽ ወዳጆችሽን ጠበቅሽ።

በዝሙትሽና በክፋትሽ፣

ምድሪቱን አረከስሽ።

3ስለዚህ ካፊያ ተከለከለ፤

ኋለኛው ዝናብም ጠፋ።

አንቺ ግን አሁንም የጋለሞታ ገጽታ አለብሽ፤

ዐይንሽን በዕፍረት አልሰብር ብለሻል።

4አሁንም ወደ እኔ ተጣርተሽ፣

‘አባቴ፣ የልጅነት ወዳጄ፣

5ሁልጊዜ ትቈጣለህን?

ቍጣህስ ለዘላለም ነውን?’ አላልሽኝም?

የምትናገሪው እንዲህ ነው፤

ይሁን እንጂ የቻልሽውን ክፋት ሁሉ ታደርጊያለሽ።”

ከዳተኛዋ እስራኤል

6እግዚአብሔር በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፤ “ከዳተኛዪቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ከፍ ወዳለው ኰረብታ ሁሉ ወጥታ፣ ወደ ለመለመው ዛፍ ሥር ሁሉ ሄዳ በዚያ አመነዘረች። 7ይህን ሁሉ ካደረገች በኋላ፣ ወደ እኔ ትመለሳለች ብዬ ነበር፤ ሆኖም አልተመለሰችም፤ ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳም ይህን አየች። 8ለከዳተኛዪቱ እስራኤል ስለ ምንዝርናዋ ሁሉ የፍች ወረቀቷን ሰጥቼ አባረርኋት። ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳም ይህን አይታ እንዳልፈራች አየሁ፤ ወጥታም አመነዘረች። 9በቅሌቷም ምድሪቱን አረከሰች፤ ከድንጋይና ከግንድ ጋር አመነዘረች፤ 10ይህም ሁሉ ሆኖ ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳ ወደ እኔ የተመለሰችው በማስመሰል እንጂ በሙሉ ልቧ አልነበረም” ይላል እግዚአብሔር

11እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ከከሓዲዋ ይሁዳ ይልቅ ከዳተኛዪቱ እስራኤል ጻድቅ ሆና ተገኘች። 12ሂድና ይህን መልእክት ወደ ሰሜን እንዲህ ብለህ ተናገር፤

“ ‘ከዳተኛዪቱ እስራኤል ሆይ፤ ተመለሽ’ ይላል እግዚአብሔር

‘እኔ መሓሪ ስለሆንሁ፣

ከእንግዲህ በቍጣ ዐይን አላይሽም’

ይላል እግዚአብሔር። ‘ለዘላለም አልቈጣም።

13በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ በማመፅሽ፣

ክብርሽንም ለእንግዶች አማልክት፣

በየለምለሙ ዛፍ ሥር አሳልፈሽ በመስጠት፣

ለእኔ ባለመታዘዝሽ፣

በደለኛ መሆንሽን ይህን አንድ ነገር ብቻ እመኚ’ ”

ይላል እግዚአብሔር

14“ከዳተኛ ልጆች ሆይ፤ እኔ ባለቤታችሁ ነኝና ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድ ሁለት መርጫችሁ ወደ ጽዮን አመጣችኋለሁ። 15እንደ ልቤም የሆኑ፣ በዕውቀትና በማስተዋል የሚመሯችሁን እረኞች እሰጣችኋለሁ። 16ቍጥራችሁ በምድሪቱ እጅግ በሚበዛበት ጊዜም” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚያ ዘመን፣ ‘የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት’ ብለው ከእንግዲህ አይጠሩም፤ ትዝ አይላቸውም፤ አያስታውሱትምም፤ አይጠፋም፤ ሌላም አይሠራም። 17በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን፣ ‘የእግዚአብሔር ዙፋን’ ብለው ይጠሯታል፤ መንግሥታትም ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ለማክበር በኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ፤ የክፉ ልባቸውንም እልኸኝነት ከእንግዲህ አይከተሉም። 18በዚያን ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት በአንድነት ሆነው ከሰሜን ምድር ለአባቶቻቸው ርስት አድርጌ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይመጣሉ።

19“እኔም፣

“ ‘የተመረጠችውን ምድር፣

የትኛውም ሕዝብ ያላገኘውን የተዋበች ርስት ልሰጥሽ፣

እንደ ወንዶች ልጆቼ ምንኛ በደስታ ልቍጠርሽ’ አልሁ፤

‘አባቴ’ ብለሽ የምትጠሪኝ፣

እኔንም ከመከተል ዘወር የማትዪ መስሎኝ ነበር።

20የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሚስት፣

ስታታልሉኝ ኖራችኋል፤”

ይላል እግዚአብሔር

21እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት፣

መንገዳቸውን አጣመዋልና፣

የእስራኤል ሕዝብ ጩኸት፣

አሳዛኝ ልቅሶ ባድማ ከሆኑት ኰረብታዎች ተሰማ።

22“እናንት ከዳተኞች ልጆች ተመለሱ፤

ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ።

“አንተ እግዚአብሔር አምላካችን ነህና፤

አዎን፤ ወደ አንተ እንመጣለን።

23በርግጥ በኰረብቶች ላይ፣

እንዲሁም በተራሮች ላይ፣ ሆ! ብለን መውጣታችን መታለል ነው፤

በርግጥ የእስራኤል መዳን፣

በአምላካችን በእግዚአብሔር ነው።

24ከለጋ ዕድሜያችን ጀምሮ፣

የአባቶቻችንን የድካም ፍሬዎች፣

በጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፣

ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን፣ ነውረኛ ጣዖቶች በሏቸው።

25እንግዲህ ዕፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤

ውርደታችንም ይሸፍነን፤

እኛም አባቶቻችንም፣

እግዚአብሔር አምላካችንን በድለናልና፤

ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣

አምላካችንን እግዚአብሔርን አልታዘዝንም።”