耶利米书 10 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

耶利米书 10:1-25

上帝与偶像

1以色列人啊,听听耶和华对你们说的话吧! 2耶和华说:

“不要效法列国的行为。

他们被天象吓倒,

你们却不要因天象而害怕。

3他们信奉的毫无价值,

他们从林中砍一棵树,

工匠用木头雕刻偶像,

4以金银作装饰,

用钉子和锤子钉牢,

以免晃动。

5它们像瓜园中的稻草人,

不能说话,不能行走,

需要人搬运。

你们不要怕它们,

它们既不能害人,

也不能助人。”

6耶和华啊,你伟大无比,

你的名充满力量!

7万国的王啊,谁不敬畏你?

敬畏你是理所当然的。

因为万国的智者和君王中无人能与你相比。

8他们都愚昧无知,

毫无用处的木制偶像能教导他们什么呢?

9偶像上的银片来自他施

金片来自乌法

都是匠人的制品,

这些偶像穿的蓝色和紫色衣服是巧匠制作的。

10唯有耶和华是真神,

是永活的上帝,

是永恒的君王。

祂一发怒,大地便震动,

万国都无法承受。

11你们要这样对他们说:“那些神明没有创造天地,它们将从天下消亡。”

12耶和华施展大能,

用智慧创造大地和世界,

巧妙地铺展穹苍。

13祂一声令下,天上大水涌动;

祂使云从地极升起,

使闪电在雨中发出,

祂从自己的仓库吹出风来。

14人人愚昧无知,

工匠都因自己铸造的偶像而惭愧,

因为这些神像全是假的,

没有气息。

15它们毫无价值,

荒谬可笑,

在报应的时候必被毁灭。

16雅各的上帝截然不同,

祂是万物的创造者,

被称为“万军之耶和华”,

以色列是祂的子民。

17被围困的犹大人啊,

收拾行装吧!

18因为耶和华说:

“看啊,这次我要把这地方的居民抛出去,

使他们苦不堪言。”

19我有祸了!因我的创伤难愈。

但我说:“这是疾病,我必须忍受。”

20我的帐篷已毁,

绳索已断;

我的儿女都离我而去,

再没有人为我支搭帐篷,

挂上幔子。

21首领愚昧,

没有求问耶和华,

因此一败涂地,

百姓如羊群四散。

22听啊,有消息传来,

喧嚣的敌军从北方冲来,

要使犹大的城邑荒凉,

沦为豺狼的巢穴。

23耶和华啊,人不能驾驭自己的命运,

不能左右自己的将来。

24耶和华啊,求你公正地惩罚我,

不要带着怒气惩罚我,

否则我将不复存在。

25求你向不认识你的列国和不求告你名的民族发烈怒,

因为他们吞噬、毁灭雅各

使他的家园一片荒凉。

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 10:1-25

ባዕድ አምልኮና እውነተኛው አምልኮ

10፥12-16 ተጓ ምብ – ኤር 51፥15-19

1የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔር የሚላችሁን ስሙ። 2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“የአሕዛብን መንገድ አትከተሉ፤

እነርሱ በሰማይ ምልክቶች ይታወካሉ፣

እናንተ ግን በእነዚህ አትረበሹ።

3የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤

ዛፍ ከጫካ ይቈርጣሉ፤

ዐናጺም በመሣሪያው ቅርጽ ያበጅለታል።

4በብርና በወርቅ ይለብጡታል፤

እንዳይወድቅም፣

በመዶሻ መትተው በምስማር ያጣብቁታል።

5ጣዖቶቻቸው በዱባ ዕርሻ መካከል እንደ ቆመ ማስፈራርቾ ናቸው፤

የመናገር ችሎታ የላቸውም፤

መራመድም ስለማይችሉ፣

ተሸካሚ ያስፈልጋቸዋል፤

ጕዳት ማድረስም ሆነ፣

መልካምን ነገር ማድረግ ስለማይችሉ፣

አትፍሯቸው።”

6እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤

አንተ ታላቅ ነህ፤

የስምህም ሥልጣን ታላቅ ነው።

7የሕዝቦች ሁሉ ንጉሥ ሆይ፤

አንተን የማይፈራ ማነው?

ክብር ይገባሃልና።

ከምድር ጠቢባን ሁሉ፣

ከመንግሥቶቻቸውም ሁሉ መካከል፣

እንደ አንተ ያለ የለም።

8ከከንቱ የዕንጨት ጣዖት ትምህርት የሚቀሥሙ ሁሉ፣

ጅሎችና ሞኞች ናቸው።

9የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣

ወርቅም ከአፌዝ ይመጣል።

ባለሙያውና አንጥረኛው የሠሯቸው፣

ብልኀተኞችም ያበጇቸው ሁሉ፣

ሰማያዊና ሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፈዋል።

10እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤

እርሱ ሕያው አምላክ፣ ዘላለማዊም ንጉሥ ነው፤

በሚቈጣበት ጊዜ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤

መንግሥታትም ቍጣውን ሊቋቋሙ አይችሉም።

11“እናንተም፣ ‘እነዚህ ሰማያትንና ምድርን ያልፈጠሩ አማልክት ከምድር ላይ፣ ከሰማያትም በታች ይጠፋሉ’ ትሏቸዋላችሁ።”10፥11 ይህ ጥቅስ የተጻፈው በአራማይክ ቋንቋ ነው

12እግዚአብሔር ግን ምድርን በኀይሉ ፈጠረ፤

ዓለምን በጥበቡ መሠረተ፤

ሰማያትንም በማስተዋሉ ዘረጋ።

13ድምፁን ሲያንጐደጕድ፣ በሰማያት ያሉ ውሆች ይናወጣሉ፤

ጉሙን ከምድር ዳር ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል፤

መብረቅን ከዝናብ ጋር ይልካል፤

ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።

14እያንዳንዳቸው ጅሎችና ዕውቀት የለሾች ናቸው።

ወርቅ አንጥረኛውም ሁሉ በሠራው ጣዖት ዐፍሯል፤

የቀረጻቸው ምስሎቹ የሐሰት ናቸው፤

እስትንፋስም የላቸውም።

15እነርሱ ከንቱ የፌዝ ዕቃዎች ናቸው፤

ፍርድ ሲመጣባቸው ይጠፋሉ።

16የያዕቆብ ዕድል ፈንታ የሆነው ግን እንደነዚህ አይደለም፤

እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነውና፤

እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው።

ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

ሊመጣ ያለው ግዞት

17አንቺ የተከበብሽ፤

ከያለበት ንብረትሽን ሰብስቢ፤

18እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤

“በዚህች ምድር የሚኖሩትን፣

አሁን ወደ ውጪ እወነጭፋቸዋለሁ፤

ጕዳቱ እንዲሰማቸው፣

መከራ አመጣባቸዋለሁ፤”

19ስለ ስብራቴ ወዮልኝ፤

ቍስሌም የማይድን ነው፤

ግን ለራሴ እንዲህ አልሁት፤

“ይህ የኔው ሕመም ነው፤ ልሸከመውም ይገባኛል።”

20ድንኳኔ ፈርሷል፤

ገመዶቹም ሁሉ ተበጣጥሰዋል፤

ልጆቼ ጥለውኝ ሄደዋል፤ ከእንግዲህም አይመለሱም፤

ድንኳኔን ለመትከል፣

መጋረጃዬንም ለመዘርጋት ማንም የቀረ የለም።

21እረኞቹ አእምሮ የላቸውም፤

እግዚአብሔርን አይጠይቁም፤

ስለዚህ አልተከናወነላቸውም፤

መንጎቻቸውም ሁሉ ተበታትነዋል።

22መርዶ ስሙ! እነሆ፤ ከሰሜን ምድር፣

ታላቅ ሽብር እየመጣ ነው፤

የይሁዳን ከተሞች ባድማ፣

የቀበሮዎችም መናኸሪያ ያደርጋል።

የኤርምያስ ጸሎት

23እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰው ሕይወት በራሱ እጅ እንዳልሆነች፣

አካሄዱንም በራሱ አቃንቶ ሊመራ

እንደማይችል ዐውቃለሁ።

24እግዚአብሔር ሆይ፤ ቅጣኝ፤ ብቻ በመጠኑ ይሁንልኝ፤

ፈጽሞ እንዳልጠፋ፣

በቍጣህ አትምጣብኝ።

25ያዕቆብን አሟጥጠው ስለ በሉት፣

ፈጽመው ስለ ዋጡት፣

መኖሪያውንም ወና ስላደረጉ፣

በማያውቁህ ሕዝቦች፣

ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ፣

ቍጣህን አፍስስ።