约翰福音 7 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约翰福音 7:1-52

耶稣的弟弟不信祂

1之后,耶稣周游加利利,不愿去犹太地区,因为犹太人想要杀祂。 2犹太人的住棚节快到了, 3耶稣的弟弟们对祂说:“离开这里,去犹太过节吧,好让你的门徒在那里也看见你所做的啊! 4因为人想出名,都不会暗地里行事,你既然可以做这些事,就把自己显给世人看吧!” 5原来连祂的弟弟们也不信祂。

6耶稣对他们说:“我的时候还没有到,你们什么时候都很方便。 7世人不会恨你们,只会恨我,因为我指证他们行为邪恶。 8你们先去过节吧,我现在还不上去,因为我的时候还没有到。” 9耶稣说完这些话,仍留在加利利

耶稣过住棚节

10他们走了以后,耶稣避开了人们的注意,暗地里上去过节。 11节期到了,犹太人到处查问:“耶稣在哪里?”

12众人对祂议论纷纷,有些人说:“祂是好人,”有些说:“不,祂欺骗民众。” 13不过,没有人敢公开议论祂的事,因为害怕犹太人。

14节期约过了一半,耶稣来到圣殿教导人。 15犹太人感到惊奇,说:“这个人没有受过教育,怎么懂得这么多呢?”

16耶稣说:“我的教导不是出于我自己,而是出于差我来的那位。 17如果你们愿意遵行上帝的旨意,就能分辨这些教导是出于上帝,还是出于我自己。 18凭自己讲论的人是要寻求自己的荣耀,但人子真实无伪,毫无不义,祂是为了使差祂来的那位得荣耀。 19摩西不是把律法传给了你们吗?你们却没有一个人遵守。为什么想要杀我呢?”

20众人回答说:“你一定是被鬼附身了!谁要杀你啊?”

21耶稣说:“我行了一件神迹,你们都感到惊奇。 22摩西把割礼传给你们,你们也在安息日行割礼。其实割礼不是摩西定的,而是从祖先们的时代就有了。 23为了避免违背摩西的律法,行割礼的那一天就算是安息日,你们还是照行。那么,我在安息日使一个病人完全康复,你们为什么责怪我呢? 24不要根据外表来断定是非,要按公义的原则判断。”

耶稣是基督吗

25有些住在耶路撒冷的人说:“这不是他们要杀的那个人吗? 26你看祂这样公开讲道,居然没有人说什么,难道官长也真的认为祂是基督吗? 27可是基督来的时候,根本没有人知道祂从哪里来,我们却知道这个人是从哪里来的。”

28于是,耶稣在圣殿里高声教导人说:“你们知道我是谁,也知道我是从哪里来的。其实我来不是出于自己的意思,差我来的那位是真实的,你们不认识祂。 29但我认识祂,因为我是从祂那里来的,差我来的就是祂。” 30他们听了,想捉拿耶稣,只是没有人下手,因为祂的时候还没有到。

31人群中有许多人信了耶稣,他们说:“基督来的时候所行的神迹,难道会比这个人行得更多吗?”

32法利赛人听见众人这样议论耶稣,就联合祭司长派差役去抓祂。 33耶稣对众人说:“我暂时还会跟你们在一起,不久我要回到差我来的那位那里。 34那时你们要找我却找不到,你们也不能去我所在的地方。”

35犹太人彼此议论说:“祂要去哪里使我们找不着呢?难道祂要到我们犹太人侨居的希腊各地去教导希腊人吗? 36祂说我们找不到祂,又不能去祂所在的地方,是什么意思?”

活水的江河

37节期最后一天,也是整个节期的高潮,耶稣站起来高声说:“人若渴了,可以到我这里来喝。 38正如圣经所言,信我的人,‘从他里面要流出活水的江河来’。” 39耶稣这话是指信祂的人要得到圣灵,但当时圣灵还没有降临,因为耶稣还没有得到荣耀。

40听见这些话后,有些人说:“祂真是那位先知。” 41也有些人说:“祂是基督。”还有些人说:“不会吧,基督怎么会出自加利利呢? 42圣经上不是说基督是大卫的后裔,要降生在大卫的故乡伯利恒吗?” 43众人因为对耶稣的看法不同,就起了纷争。 44有些人想抓祂,只是没有人下手。

犹太官长不信耶稣

45祭司长和法利赛人看见差役空手回来,就问:“你们为什么不把祂带来呢?”

46差役答道:“从未有人像祂那样说话!”

47法利赛人说:“难道你们也被祂迷惑了吗? 48哪有官长和法利赛人信祂呢? 49这群不明白律法的民众该受咒诅!”

50曾经夜访耶稣、属于他们当中一员的尼哥德慕说: 51“难道不听被告申辩,不查明事实真相,我们的律法就定祂的罪吗?”

52他们回答说:“难道你也是加利利人吗?你去查查看,就会知道没有先知是从加利利来的。”

New Amharic Standard Version

ዮሐንስ 7:1-53

ኢየሱስ የዳስ በዓል ወደሚከበርበት ሄደ

1ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፣ በዚያ የነበሩት አይሁድ ሊገድሉት ስለ ፈለጉ፣ በይሁዳ አውራጃ መዘዋወር ትቶ በገሊላ ተዘዋወረ። 2የአይሁድ የዳስ በዓል በተቃረበ ጊዜ ግን፣ 3የኢየሱስ ወንድሞች እንዲህ አሉት፤ “ደቀ መዛሙርትህም ደግሞ የምታደርገውን ታምራት እንዲያዩ፣ ከዚህ ወደ ይሁዳ ሂድ፤ 4ራሱን ሊገልጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ ማንም የለምና። አንተም እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ፣ ራስህን ለዓለም ግለጥ።” 5የገዛ ወንድሞቹ እንኳ አላመኑበትም ነበር።

6ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ለእኔ ትክክለኛው ጊዜ ገና አልደረሰም፤ ለእናንተ ግን ማንኛውም ጊዜ ምቹ ነው። 7ዓለም እናንተን ሊጠላ አይችልም፤ እኔ ግን፣ አድራጎቱ ክፉ መሆኑን ስለምመሰክርበት ይጠላኛል። 8እናንተ ወደ በዓሉ ሂዱ፤ ለእኔ ትክክለኛው ጊዜ ስላልደረሰ7፥8 አንዳንድ ቅጆች ገና ስላልደረሰ ይላሉ ወደ በዓሉ አልሄድም።” 9ይህን ብሏቸው በገሊላ ቈየ።

10ይሁን እንጂ፣ ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ፣ እርሱም በግልጥ ሳይሆን በስውር ወደ በዓሉ ሄደ። 11በበዓሉም ላይ አይሁድ፣ “ያ ሰው የት አለ?” እያሉ ይፈልጉት ነበር።

12ስለ እርሱ በሕዝቡ መካከል ብዙ ጕምጕምታ ነበር። አንዳንዶች፣ “ደግ ሰው ነው” አሉ።

ሌሎች ግን፣ “የለም፤ ሕዝቡን የሚያስት ነው” አሉ። 13ይሁን እንጂ አይሁድን ከመፍራት የተነሣ ስለ እርሱ በግልጽ የተናገረ ማንም አልነበረም።

ኢየሱስ በበዓሉ ላይ ተገኝቶ አስተማረ

14በበዓሉም አጋማሽ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ወጥቶ ያስተምር ጀመር። 15አይሁድም በመደነቅ፣ “ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ሊያውቅ ቻለ?” አሉ።

16ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “የማስተምረው ትምህርት ከራሴ ሳይሆን፣ ከላከኝ የመጣ ነው። 17ማንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ ቢፈልግ፣ የእኔ ትምህርት ከእግዚአብሔር ወይም ከራሴ የመጣ መሆኑን ለይቶ ያውቃል፤ 18ከራሱ የሚናገር፣ ያን የሚያደርገው ለራሱ ክብርን ስለሚሻ ነው፤ ስለ ላከው ክብር የሚሠራ ግን እርሱ እውነተኛ ነው፤ ሐሰትም አይገኝበትም። 19ሙሴ ሕግን አልሰጣችሁምን? ነገር ግን አንዳችሁም ሕጉን አልጠበቃችሁም። ለምን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?”

20ሕዝቡም፣ “አንት ጋኔን ያደረብህ! ደግሞ አንተን ማን ሊገድል ይፈልጋል?” አሉት።

21ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “አንድ ሥራ ብሠራ፣ ሁላችሁም ተገረማችሁ። 22ግዝረት የመጣው ከአባቶች እንጂ ከሙሴ አይደለም፤ ሆኖም ሙሴ ግዝረትን ስለ ሰጣችሁ፣ በሰንበት እንኳ ሕፃን ትገርዛላችሁ። 23የሙሴ ሕግ እንዳይሻር ሕፃን በሰንበት የሚገረዝ ከሆነ፣ የሰውን ሁለንተና በሰንበት ስለ ፈወስሁ ለምን በእኔ ላይ ትቈጣላችሁ? 24የሰውን ፊት በማየት መፍረድ ትታችሁ ቅን ፍርድ ፍረዱ።”

ኢየሱስ፣ እርሱ ክርስቶስ ስለ መሆኑ

25በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም የነበሩ አንዳንድ ሰዎች እንዲህ አሉ፤ “ሊገድሉት የሚፈልጉት ሰው ይህ አይደለምን? 26ይኸው እርሱ በአደባባይ ይናገራል፤ አንድም ቃል አይናገሩትም፤ ክርስቶስ7፥26 ወይም መሲሑ፤ እንዲሁም 27፡31፡41 እና 42 ይመ ነው ብለው ባለሥልጣኖቹም ተቀብለውት ይሆን? 27ይህ ሰው ግን ከየት እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን፤ ክርስቶስ ሲመጣ እኮ ከየት እንደ ሆነ ማንም አያውቅም።”

28ኢየሱስ በቤተ መቅደስ አደባባይ ሲያስተምር ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “አዎን፣ እኔን ታውቁኛላችሁ፤ ከየት እንደ ሆንሁም ታውቃላችሁ። እኔ እዚህ ያለሁት በገዛ ራሴ አይደለም፤ ነገር ግን የላከኝ እርሱ እውነተኛ ነው። እናንተ አታውቁትም፤ 29እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ስለሆንሁ፣ እርሱም ስለ ላከኝ ዐውቀዋለሁ።”

30ስለዚህ ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም እጁን አላሳረፈበትም፤ 31ሆኖም ከሕዝቡ ብዙዎች በእርሱ አምነው፣ “ታዲያ፣ ክርስቶስ ሲመጣ ይህ ሰው ከሚሠራቸው ታምራዊ ምልክቶች የበለጠ ያደርጋል?” አሉ።

32ፈሪሳውያን፣ ሕዝቡ ስለ እርሱ በጕምጕምታ የሚነጋገረውን ነገር ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም እንዲይዙት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎችን ላኳቸው።

33ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “ከእናንተ ጋር የምቈየው ጥቂት ጊዜ ነው፤ ከዚያም ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ 34ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ ወዳለሁበትም ልትመጡ አትችሉም።”

35አይሁድም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “ይህ ሰው፣ ልናገኘው የማንችለው ወዴት ለመሄድ ቢያስብ ነው? በግሪኮች መካከል ተበታትነው ወደሚኖሩት ወገኖቻችን ሄዶ ግሪኮችን ሊያስተምር ፈልጎ ይሆን? 36‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤’ ደግሞም፣ ‘እኔ ወዳለሁበት ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ይሆን?”

37የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤ 38በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ7፥37-38 ወይም ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣ፤ 38 በእኔ የሚያምን ይጠጣ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” 39ይህን ያለው በእርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት መንፈስ ነበር፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ አልተሰጠም ነበር።

40ከሕዝቡ አንዳንዶቹ ቃሉን ሰምተው፣ “ይህ ሰው በርግጥ ነቢዩ ነው” አሉ።

41ሌሎችም፣ “እርሱ ክርስቶስ ነው” አሉ።

ሌሎች ደግሞ እንዲህ አሉ፤ “ክርስቶስ ከገሊላ እንዴት ሊመጣ ይችላል? 42መጽሐፍ፣ ክርስቶስ ከዳዊት ዘር7፥42 ወይም ከዳዊት ቤተ ሰብ፣ ዳዊትም ከኖረበት ከቤተ ልሔም እንደሚመጣ ይናገር የለምን?” 43ስለዚህም በኢየሱስ ምክንያት በሕዝቡ መካከል መለያየት ሆነ፤ 44አንዳንዶቹም ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ማንም እጁን አላሳረፈበትም።

የአይሁድ መሪዎች አለማመን

45በመጨረሻም የቤተ መቅደስ ጠባቂዎቹ፣ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን ተመልሰው ሄዱ፤ እነርሱም ጠባቂዎቹን፣ “ለምን አላመጣችሁትም?” አሏቸው።

46ጠባቂዎቹም፣ “እንደዚህ ሰው፣ ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቅም” ሲሉ መለሱ።

47ፈሪሳውያንም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተም ተታላችኋል ማለት ነው? 48ለመሆኑ ከባለሥልጣኖችና ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለ? 49ሕጉን የማያውቅ ይህ ሕዝብ ግን የተረገመ ነው።”

50ከዚህ ቀደም ወደ ኢየሱስ ሄዶ የነበረውና ከእነርሱ አንዱ የሆነው ኒቆዲሞስ እንዲህ አላቸው፤ 51“ሕጋችን፣ አስቀድሞ አንድን ሰው ሳይሰማና ምን እንዳደረገ ሳይረዳ ይፈርድበታልን?”

52እነርሱም፣ “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ7፥52 ሁለት የጥንት ቅጆች ነቢዩ ይላሉ። ከገሊላ እንደማይነሣ መርምር፤ ትደርስበታለህ” ብለው መለሱለት።

53ከዚህ በኋላ ሁሉም ወደየቤታቸው ሄዱ።