约伯记 23 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约伯记 23:1-17

约伯的回答

1约伯回答说:

2“我的哀诉至今充满苦楚,

祂的责罚使我呻吟不止。

3但愿我知道何处能寻见上帝,

知道怎样去祂的居所。

4我好在祂面前陈明案情,

滔滔不绝地为自己申辩;

5我好知道祂的答复,

看看祂对我说什么。

6祂会用大能与我争辩吗?

不会的,祂会垂听我的申诉,

7允许正直的人与祂理论,

审判者会让我永远脱罪。

8“然而,我去东边,祂不在那里;

我到西边,也找不到祂。

9祂在北边工作,我看不见祂;

祂转到南边,我也看不见祂。

10但祂知道我的一举一动,

我被祂试炼后必如纯金。

11我紧随祂的脚步,

持守祂的道,没有偏离。

12我没有违背祂的诫命,

我珍视祂的话语胜过我日用的饮食。

13祂独行其事,谁能阻挡祂?

祂按自己的意愿行事。

14祂在我身上的计划必然实现,

祂还有许多这样的计划。

15所以,我在祂面前惊恐不安。

我想起这事,便对祂充满恐惧。

16上帝使我心惊胆战,

全能者使我惊恐不安。

17然而,我不会因为置身黑暗,

被幽暗笼罩而缄默不言。

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 23:1-17

ኢዮብ

1ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤

2“ዛሬም ሐዘኔ መራራ ነው፤

እያቃሰትሁ እንኳ እጁ23፥2 በሰብዓ ሊቃናት ትርጕም፣ በሱርስትና በዕብራይስጡ ላይ፣ እጅ በላዬ ይላል። በላዬ ከብዳለች።

3እርሱን የት እንደማገኘው ባወቅሁ፤

ወደ መኖሪያውም መሄድ በቻልሁ!

4ጕዳዬን በፊቱ አቀርብ ነበር፤

አፌንም በሙግት እሞላው ነበር።

5የሚመልስልኝ ቃል ምን እንደ ሆነ ባወቅሁ ነበር፤

የሚለኝንም ባስተዋልሁ ነበር።

6በታላቅ ኀይሉ ከእኔ ጋር ይሟገት ይሆን?

አይደለም፤ ይልቁን ያደምጠኛል።

7ቅን ሰው ጕዳዩን በእርሱ ፊት ያቀርባል፤

እኔም ከፈራጄ ለዘላለም ነጻ እሆናለሁ።

8“ዳሩ ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ፣ በዚያ የለም፤

ወደ ምዕራብም ብሄድ፣ እርሱን አላገኘውም፤

9በሰሜን እየሠራ ሳለ አላየውም፤

ወደ ደቡብ በሚዞርበት ጊዜ ደብዛው አይገኝም።

10ግን እኔ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤

ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።

11እግሮቼ ርምጃውን በጥብቅ ተከታትለዋል፤

ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ።

12ከአፉ ከወጣው ትእዛዝ አልራቅሁም፣

የአንደበቱን ቃል ከዕለት እንጀራዬ አብልጬ ይዣለሁ።

13“እርሱ ግን ራሱን ችሎ ብቻውን የሚኖር ነው፤ የሚቋቋመውስ ማን ነው?

እርሱ የፈቀደውን ያደርጋል።

14በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤

ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው።

15በፊቱ የደነገጥሁትም ለዚህ ነው፤

ይህን ሁሉ ሳስብ እፈራለሁ።

16እግዚአብሔር ልቤን አባባው፤

ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደነገጠኝ።

17ይህም ሆኖ ሳለ ጨለማው፣

ፊቴንም የጋረደው ጽልመት ልሳኔን አልዘጋውም።