申命记 16 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

申命记 16:1-22

逾越节

1“你们要在亚笔月16:1 亚笔月是犹太历的第一个月,约在阳历三月中旬到四月中旬,相当于中国的春分时节。为你们的上帝耶和华守逾越节,因为祂在这个月的一个晚上带领你们离开了埃及2你们要在你们的上帝耶和华选定的敬拜场所,把牛羊作为逾越节的祭牲献给祂。 3吃祭牲的时候,不可吃有酵的饼,七天之内要吃无酵饼,即忆苦饼,以便你们一生谨记离开埃及的日子,因为当时你们离开得很仓促。 4那七天之内,你们境内不可有酵母。第一天傍晚献的祭肉不可留到第二天早晨。 5在你们的上帝耶和华将要赐给你们的各城中,你们不可随便献逾越节的祭牲, 6而是要在傍晚日落时分,即你们离开埃及的时候,到你们的上帝耶和华选定的敬拜场所献逾越节的祭牲。 7你们要在那里煮祭肉吃,第二天早晨可以返回自己的帐篷。 8在随后的六天之内,你们要吃无酵饼。第七天,要举行庄严的聚会,敬拜你们的上帝耶和华。那一天你们不可做工。

七七收获节

9“从收割那天开始算起,你们要算出七周的时间。 10七周后,要为你们的上帝耶和华守七七收获节16:10 七七收获节”后称为五旬节。。那时,你们要按照你们的上帝耶和华所赐的福分,甘心乐意地献上祭物。 11你们要和儿女、仆婢、同城的利未人、寄居者及孤儿寡妇在你们的上帝耶和华选定的敬拜场所,在祂面前一起欢喜快乐。 12你们要记住自己曾在埃及做过奴隶,因此要谨遵这些律例。

住棚节

13“在收藏好谷物和新酒后,你们要守七天的住棚节。 14住棚节期间,你们要和儿女、仆婢、同城的利未人、寄居者及孤儿寡妇一起欢庆。 15要在你们的上帝耶和华选定的地方,为祂守住棚节七天;要满心欢喜,因为你们的上帝耶和华赐福你们,使你们的出产丰富、凡事顺利。

16“你们所有男子要每年三次,即在无酵节、七七收获节和住棚节,在你们的上帝耶和华指定的地方朝见祂。你们不可空手朝见, 17各人要按祂赐的福分,尽自己的能力献上礼物。

委任审判官

18“要在你们的上帝耶和华将要赐给你们的各城中,按支派委任审判官及其他官员。官员们要秉公审判, 19不可徇私枉法、偏心待人,收受贿赂,因为贿赂能蒙蔽智者的眼睛,使正直人颠倒是非。 20你们要追求公正公义,以便可以存活,承受你们的上帝耶和华将要赐给你们的土地。

不可拜偶像

21“在为你们的上帝耶和华建造的祭坛旁,你们不可竖立亚舍拉木神像, 22也不可竖立神柱,因为这些是你们的上帝耶和华所憎恶的。

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 16:1-22

ፋሲካ

16፥1-8 ተጓ ምብ – ዘፀ 12፥14-20ዘሌ 23፥4-8ዘኍ 28፥16-25

1አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በአቢብ ወር ከግብፅ በሌሊት ስላወጣህ፣ የአቢብን ወር ጠብቅ፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ፋሲካ አክብርበት። 2እግዚአብሔር (ያህዌ) ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋህ አንዱን እንስሳ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፋሲካ አድርገህ ሠዋው። 3ከቦካ ቂጣ ጋር አትብላው፤ ከግብፅ የወጣኸው በችኰላ ነውና ከግብፅ የወጣህበትን ጊዜ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ታስብ ዘንድ የመከራ ቂጣ ሰባት ቀን ብላ። 4በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማናቸውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቈይ አታድርግ። 5አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚሰጥህ በማናቸውም ከተማ ፋሲካን መሠዋት አይገባህም፤ 6ነገር ግን ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚመርጠው ስፍራ፣ ፀሓይ ስትጠልቅ ምሽቱ16፥6 ወይም፣ ፀሓይ ስትወጣ ንጋቱ ላይ ላይ ከግብፅ በወጣህበት ሰዓት16፥6 ወይም ዓመታዊ መታሰቢያ እንዲሆን፣ በዚያ ፋሲካን ሠዋ። 7ሥጋውንም ጠብሰህ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚመርጠው ስፍራ ብላ፤ ሲነጋም ወደ ድንኳንህ ተመልሰህ ሂድ።

8ስድስት ቀን ያልቦካ ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የተቀደሰ ጉባኤ አድርግ፤ ሥራም አትሥራበት።

የመከር በዓል

16፥9-12 ተጓ ምብ – ዘሌ 23፥15-22ዘኍ 28፥26-31

9እህልህን ማጨድ ከምትጀምርበት ዕለት አንሥቶ ሰባት ሳምንት ቍጠር። 10ከዚያም በኋላ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በባረከህ መጠን፣ በፈቃድህ የምታመጣውን ስጦታ በማቅረብ በመከሩ በዓል አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) አክብር። 11አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፣ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችህ፣ በከተሞችህ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፣ በመካከልህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ደስ ይበላችሁ። 12አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስታውስ፤ ይህንም በጥንቃቄ ጠብቅ።

የዳስ በዓል

16፥13-17 ተጓ ምብ – ዘሌ 23፥33-43ዘኍ 29፥12-39

13የእህልህን ምርት ከዐውድማህ፣ ወይንህንም ከመጭመቂያህ ከሰበሰብህ በኋላ፣ የዳስን በዓል ሰባት ቀን አክብር። 14በበዓልህ አንተ፣ ወንድና ሴት ልጅህ፣ ወንድና ሴት አገልጋይህ፣ በከተማው ያለ ሌዋዊ፣ መጻተኛ፣ አባት አልባውና መበለቲቱ ደስ ይበላችሁ። 15እግዚአብሔር (ያህዌ) በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በዓሉን ሰባት ቀን አክብር፤ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በእህል ምርትህና በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክሃል፤ ደስታህም ፍጹም ይሆናል።

16ወንዶችህ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ፣ በቂጣ በዓል፣ በመከር በዓልና በዳስ በዓል ላይ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ይቅረቡ፤ ማንም ሰው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ባዶ እጁን አይቅረብ። 17አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በባረከህ መጠን እያንዳንዱ እንደ ችሎታው ይስጥ።

ስለ ፍርድ አሰጣጥ

18አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ። 19ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጕቦም አትቀበል፤ ጕቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። 20በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ፣ ቅን ፍርድን ብቻ ተከተል።

ሌሎችን አማልክት ስለ ማምለክ

21ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የአሼራን ምስል የዕንጨት ዐምድ አታቁም16፥21 ወይም፣ ለአሼራ ብለህ ምንም ዐይነት ዛፍ አትትከል22አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚጠላውን ማምለኪያ ዐምድ ለአንተ አታቁም።