提摩太前书 2 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

提摩太前书 2:1-15

要为他人祷告

1我劝你首先要为所有的人恳求、祷告、代求,为他们感谢上帝。 2也要为所有的君王和掌权者祷告,使我们可以怀着虔诚、端正的心过和平安宁的生活。 3这样做很美好,是蒙我们的救主上帝悦纳的。 4因为祂愿全人类都得救,明白真理。 5上帝只有一位,在上帝和人类之间只有一位中保,就是降世为人的基督耶稣。 6祂舍命作全人类的赎价,这在所定的时候已显明出来。 7为此,我被指派做传道人和使徒,教导外族人认识信仰和真理。我说的是实话,并非谎言。

信徒的操守

8我愿男人举起圣洁的手随处祷告,不发怒,不争辩2:8 争辩”或译“疑惑”。9我愿女人衣着朴素端庄,不靠发型、珠宝金饰或名贵衣服来妆饰自己, 10要有良好的行为,这样才配称为敬畏上帝的妇女。 11妇女应当安安静静地学习,完全顺服。

12我不准女人教导或管辖男人,她们应当保持安静。 13因为先造的是亚当,后造的是夏娃14受骗犯罪的不是亚当,是夏娃15不过,女人如果持守信心和爱心,圣洁自律,就必在生育的事上得救。

New Amharic Standard Version

1 ጢሞቴዎስ 2:1-15

አምልኮን በሚመለከት የተሰጠ መመሪያ

1እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ለነገሥታትና ለባለሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ 2ይህም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው። 3ይህ በእግዚአብሔር በአዳኛችን ፊት ደስ የሚያሰኝ ነው፤ 4እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል። 5አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ አስታራቂ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ 6ራሱንም ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም በትክክለኛው ጊዜ ተመስክሮለታል። 7እኔም ለዚህ ነገር የምሥራች አብሣሪና ሐዋርያ እንዲሁም ለአሕዛብ የእውነተኛ እምነት አስተማሪ ሆኜ ተሾምሁ፤ እውነቱን እናገራለሁ፤ አልዋሽም።

8እንግዲህ ወንዶች በሁሉም ቦታ ያለ ቍጣና ያለ ክርክር የተቀደሱ እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ። 9እንዲሁም ሴቶች በጨዋነትና ራስን በመግዛት ተገቢ የሆነ ልብስ ይልበሱ እንጂ በሹሩባ ወይም በዕንወይም ዋጋቸው ውድ በሆኑ ልብሶች አይሽቀርቀሩ፤ 10ነገር ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ በመልካም ተግባር ይዋቡ።

11ሴት በጸጥታና በሙሉ መገዛት ትማር። 12ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፤ 13ምክንያቱም አዳም ቀድሞ ተፈጥሯል፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች። 14ደግሞም የተታለለው አዳም አይደለም፤ የተታለለችውና ኀጢአተኛ የሆነችው ሴቷ ናት። 15ይሁን እንጂ ሴት2፥15 ግሪኩ እርሷ ይላል። በእምነትና በፍቅር፣ በቅድስናም ራሷን እየገዛች ብትጸና ልጅ በመውለድ ትድናለች2፥15 ወይም ትታደሳለች