士师记 3 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

士师记 3:1-31

迦南余族

1-2耶和华为了考验那些没有经历过迦南战事的以色列人,让他们学习作战,就留下了以下各族: 3五个非利士王、所有的迦南人、西顿人和住在巴力·黑门山到哈马口一带的黎巴嫩山区的希未人。 4耶和华留下这几个外族是要考验以色列人,看他们是否愿意遵从祂借摩西向他们祖先颁布的诫命。 5以色列人住在这些迦南人、人、亚摩利人、比利洗人、希未人和耶布斯人当中, 6跟他们通婚,祭拜他们的神明。

士师俄陀聂

7以色列人做耶和华视为恶的事,忘记他们的上帝耶和华,祭拜假神巴力亚舍拉8耶和华向他们发怒,把他们交在美索不达米亚古珊·利萨田的手中,受古珊·利萨田统治八年。 9他们向耶和华呼求,耶和华就使一位名叫俄陀聂的拯救者兴起,他是迦勒弟弟基纳斯的儿子。 10耶和华的灵降在俄陀聂身上,他就做了以色列的士师,领兵出战。耶和华将美索不达米亚古珊·利萨田交在他手中,他便战胜了古珊·利萨田11此后,国内安享太平四十年,直到俄陀聂去世。

士师以笏

12之后,以色列人又做耶和华视为恶的事,耶和华就使摩押伊矶伦强盛起来,攻打以色列人。 13伊矶伦联合亚扪人和亚玛力人进攻以色列人,占据了棕树城, 14以色列人受摩押伊矶伦统治十八年。 15他们呼求耶和华,耶和华就使一位名叫以笏的拯救者兴起。他是便雅悯基拉的儿子,善用左手。以色列人派他去向摩押伊矶伦进贡。 16他造了一把约半米长的两刃利剑,绑在右腿的衣服里。 17他带着贡物去见肥胖的摩押伊矶伦18以笏献上了贡物之后,便和抬贡物的人一起离去。 19到了吉甲附近雕石神像的地方,他让抬贡物的人先回去,自己则折回王宫,对王说:“王啊,我有机密禀告。”王就命左右的人回避,众人便都退去了。 20当时王独自坐在楼上的房间乘凉,以笏近前说:“我有从上帝而来的讯息要禀告。”王站起来的时候, 21以笏左手拔出藏在右腿上的剑刺进王的肚腹, 22连剑柄也刺了进去,深深嵌入肥肉。以笏没有拔剑, 23便走出房间,把门都关上,锁好。

24以笏走后,王的仆人过来,见房门紧锁,以为王在大解。 25等了很久,门还没开,他们很焦急,就拿钥匙开门,发现他们的主人已经倒毙在地上。

26他们等待的时候,以笏已经逃走了。他经过雕石神像的地方,逃往西伊拉27到了那里,他就在以法莲的山区吹响号角,召集以色列人。众人跟随以笏下山, 28以笏对他们说:“跟我来!耶和华已经把仇敌摩押人交在你们手中了。”于是,众人跟着他占领了通往摩押约旦河各渡口,不许任何人渡河。 29当时他们杀了约一万名强悍善战的摩押勇士,没有一人逃脱。 30这样,以色列人征服了摩押人,国中安享太平八十年。

珊迦

31以笏之后,亚拿的儿子珊迦拯救了以色列人。他曾用一根赶牛棍杀了六百名非利士人。

New Amharic Standard Version

መሳፍንት 3:1-31

1በዚህ ጊዜ በከነዓን ላይ በተደረጉት ጦርነቶች ተሳትፈው የማያውቁትን እስራኤላውያን ለመፈተን፣ እግዚአብሔር ባሉበት የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው፤ 2ይህን ማድረጉ ቀደም ሲል በጦር ሜዳ ውለው የማያውቁትን የእስራኤል ልጆች የጦርነት ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ ብቻ ነው፤ 3እነዚህም አሕዛብ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፣ ከነዓናውያን በሙሉ፣ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማት3፥3 ወይም እስከ መግቢያው ድረርስ መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ። 4እነዚህ፣ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ለቀደሙ አባቶቻቸው የሰጠውን ትእዛዞች ማክበር አለማክበራቸውን ለማወቅ መፈተኛ እንዲሆኑ እዚያው የቀሩ ነበሩ።

5ስለዚህ እስራኤላውያን ከከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኤዊያውያንና ከኢያቡሳውያን ጋር አብረው ኖሩ። 6እስራኤላውያን የእነዚህን ሴቶች ልጆች አገቡ፤ የራሳቸውንም ሴቶች ልጆች ለእነርሱ ወንዶች ልጆች ዳሩ፤ አማልክታቸውንም አመለኩ።

ጎቶንያል

7እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ እግዚአብሔር አምላካቸውንም ረሱ፤ የበኣልንና የአስታሮትን አማልክት አመለኩ። 8እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ስለዚህ ለመስጴጦምያ3፥8 ሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ነው። ንጉሥ ለኵስርስቴም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እስራኤላውያንም ስምንት ዓመት በባርነት ተገዙለት። 9እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ ግን የካሌብን ታናሽ ወንድም የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን ታዳጊ አድርጎ አስነሣላቸው። 10የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የእስራኤል መስፍን3፥10 ወይም መሪ ሆኖ ወደ ጦርነትም ወጣ። እግዚአብሔር የመስጴጦምያን ንጉሥ ኵስርስቴምን አሳልፎ ስለ ሰጠው ድል አደረገ። 11የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።

ናዖድ

12እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ይህን በማድረ ጋቸውም እግዚአብሔር የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎን በእስራኤል ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ። 13እርሱም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን ካስተባበረ በኋላ እስራኤልን ወግቶ የዘንባባ ዛፎች3፥13 ኢያሪኮ ነች ከተማ የሆነችውን ኢያሪኮን ያዙ። 14እስራኤላውያንም ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን ዐሥራ ስምንት ዓመት ተገዘሉት።

15እስራኤላውያን እንደ ገና ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ግራኙን ናዖድን ነጻ እንዲያወጣቸው አስነሣው። እስራኤላውያን ናዖድን ግብር አስይዘው ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት። 16እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመት3፥16 0.5 ሜትር ያህል ነው ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው። 17ግብሩንም ወፍራም ለነበረው ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን አቀረበ፤ 18ናዖድም ግብሩን ካቀረበ በኋላ፣ ግብር ተሸክመው የመጡት ሰዎች ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ። 19እርሱ ራሱ ግን ጌልጌላ አጠገብ ድንጋዮች3፥19 በዚህና በቍጥር 26 ላይ ጣዖት ተብሎ ሊተረጐም ይችላል። ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው።

ንጉሡም፣ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩት አገልጋዮች በሙሉ ትተውት ወጡ።

20ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ3፥20 የዕብራይስጡ ሐረግ ትርጕም በትክክል አይታወቅም። ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ናዖድ ቀረብ ብሎ፣ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ። 21ናዖድ ግራ እጁን ሰደድ በማድረግ ሰይፉን ከደበቀበት ከቀኝ ጭኑ መዝዞ በንጉሡ ሆድ ሻጠው። 22እጀታው ሳይቀር ሰይፉ እንዳለ ሆዱ ውስጥ ገባ፤ ስለቱም በጀርባው ወጣ፤ ሞራም ስለቱን ሸፈነው፤ ናዖድ ሰይፉን ስላልነቀለው አንጀቱ ተዘረገፈ። 23ከዚያም በኋላ ናዖድ በዕልፍኙ3፥23 የዕብራስጡ ቃል ትርጕም በትክክል አይታወቅም። መግቢያ ወጣ፤ የዕልፍኙንም በር በንጉሡ ላይ ዘግቶ ቈለፈው።

24ናዖድ ከሄደ በኋላ፣ የንጉሡ አገልጋዮች ሲመጡ፣ የዕልፍኙ በር ተቈልፎ አገኙት፤ እነርሱም፣ “በውስጠኛው ክፍል እየተጸዳዳ ይሆናል” አሉ፤ 25እስኪደክማቸውም ድረስ ጠበቁ፤ ነገር ግን ንጉሡ የዕልፍኙን በሮች ባለመክፈቱ ቍልፍ ወስደው ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ፣ በወለሉም ላይ ተዘርግቶ አገኙት።

26የንጉሡ አገልጋዮች በዕልፍኙ በር ላይ ቆመው ሲጠባበቁ ናዖድ ርቆ ሄደ፤ ድንጋዮች ተጠርበው በሚወጡበት በኩል ወደ ሴርታይም አመለጠ። 27እዚያም እንደ ደረሰ፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ እስራኤላውያንም በእርሱ መሪነት ከኰረብታው ላይ አብረውት ወረዱ።

28እርሱም፣ “ጠላታችሁን ሞዓብን እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ስለ ሰጣችሁ ተከተሉኝ” በማለት አዘዛቸው፤ እነርሱም ተከትለውት ወረዱ፤ ከዚያም ከዮርዳኖስ ወደ ሞዓብ የሚያሻግሩትን መልካዎች በመያዝ አንድም ሰው እንዳያልፍ ከለከሉ። 29በዚያን ጊዜ ብርቱና ኀይለኛ የሆኑ ዐሥር ሺሕ ሞዓባውያንን ገደሉ፤ አንድም ሰው አላመለጠም። 30በዚያን ቀን ሞዓብ በእስራኤል ድል ሆነች፤ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ሰላም አገኘች።

ሰሜጋር

31ከናዖድ በኋላ ስድስት መቶ ፍልስጥኤማውያንን በበሬ መንጃ የገደለው የዓናት ልጅ ሰሜጋር ተነሣ፤ እርሱም እንደዚሁ ደግሞ እስራኤልን አዳነ።