士师记 10 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

士师记 10:1-18

士师陀拉和雅珥

1亚比米勒死后,以萨迦陀拉拯救了以色列人。他住在以法莲山区的沙密,祖父是朵多,父亲是普瓦2陀拉做士师二十三年,死后葬在沙密

3之后,基列雅珥做士师二十二年。 4他有三十个儿子,每人骑一头驴。他们在基列拥有三十座城,那些城到现在还叫“雅珥之城”。 5雅珥死后,葬在加们

以色列人因犯罪而受罚

6后来,以色列人又做耶和华视为恶的事,祭拜巴力亚斯她录,又拜亚兰西顿摩押亚扪非利士的神明。他们背弃耶和华,不再事奉祂。 7耶和华向他们发怒,把他们交在非利士人和亚扪人手中。 8那年,非利士人和亚扪人击垮了以色列人,压迫基列地区、约旦河东亚摩利境内的以色列人达十八年。 9亚扪人还渡过约旦河攻击犹大便雅悯以法莲支派,使以色列人苦不堪言。 10于是,他们呼求耶和华说:“我们背弃我们的上帝去祭拜巴力,我们得罪了你。” 11耶和华对他们说:“你们受埃及人、亚摩利人、亚扪人、非利士人、 12西顿人、亚玛力人和马云人的压迫,就呼求我,我岂没有拯救你们吗? 13但你们竟背弃我,去事奉别的神明,所以我不再救你们。 14你们去呼求自己选择的神明吧!你们有难,让他们救你们吧!” 15他们对耶和华说:“我们犯了罪,任你处置我们,只求你今天拯救我们。” 16以色列人除掉了他们的外邦神像,转而事奉耶和华。耶和华不忍再看以色列人受苦。

17当时,亚扪人整装备战,在基列安营;以色列人也集合起来,在米斯巴安营。 18基列的首领们彼此商议说:“谁先攻打亚扪人,谁就做所有基列人的首领。”

New Amharic Standard Version

መሳፍንት 10:1-18

ቶላ

1ከአቤሜሌክ በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ የዱዲ ልጅ፣ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፤ እርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ሳምር በምትባል መንደር ይኖር ነበር። 2ቶላ በእስራኤል ላይ ሃያ ሦስት ዓመት በፈራጅነት ከተቀመጠ በኋላ ሞተ፤ በሳምርም ተቀበረ።

ኢያዕር

3ከቶላ ቀጥሎ ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፤ እርሱም በእስራኤል ላይ ሃያ ሁለት ዓመት በፈራጅነት10፥3 በዚህና በቍጥር 3 ላይ በትውፊት መሳፍንት ይባላል። ተቀመጠ። 4ኢያዕር በሠላሳ አህዮች የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ልጆቹም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች በገለዓድ ምድር ነበሯቸው። 5ኢያዕር ሞተ፤ በቃሞንም ተቀበረ።

ዮፍታሔ

6እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የሶሪያን፣ የሲዶናን፣ የሞዓብን፣ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ስለ ተዉና ስላላገለገሉት፣ 7ተቈጣቸው፤ በፍልስጥኤማውያንና በአሞናውያን እጅ ሸጣቸው፤ 8እነርሱም በዚያን ዓመት ሰበሯቸው፤ አደቀቋቸውም፤ እስራኤላውያንን ሁሉ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው በገለዓድ ምድር፣ 9በአሞራውያን አገር ዐሥራ ስምንት ዓመት እንዲሁም አሞናውያን ይሁዳን፣ ብንያምንና የኤፍሬምን ቤት ለመውጋት ዮርዳኖስን ስለ ተሻገሩ እስራኤላውያን እጅግ ተጨነቁ። 10ከዚያም እስራኤላውያን፣ “አንተን አምላካችንን በመተው የበኣልን አማልክት በማምለካችን አንተን በድለናል” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።

11እግዚአብሔርም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ግብፃውያን፣ አሞራውያን፣ አሞናውያን፣ ፍልስጥኤማውያን፣ 12ሲዶናውያን፣ አማሌቃውያንና ማዖናውያን10፥12 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ምድያማውያን ይላሉ። አሠቃዩአችሁ፤ እናንተም እንድረዳችሁ ወደ እኔ ጮኻችሁ፤ ታዲያ እኔ ከእጃቸው አላዳንኋችሁምን? 13እናንተ ግን እኔን ትታችሁ ሌሎች አማልክትን አመለካችሁ፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ አላድናችሁም፤ 14ሂዱና ወደ መረጣችኋቸው አማልክት ጩኹ፤ መከራ በሚያገኛችሁ ጊዜ እስቲ ያድኗችሁ።”

15እስራኤላውያንም እግዚአብሔርን፣ “ኀጢአት ሠርተናል፤ መልካም መስሎ የታየህን አድርግብን፤ እባክህን የዛሬን ብቻ አድነን” አሉት። 16ከዚያም በመካከላቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመለኩ፤ እግዚአብሔርም እስራኤል ስትጐሳቈል ዝም ብሎ ማየት አልቻለም።

17አሞናውያን ለጦርነት ዝግጁ ሆነው በገለዓድ በሰፈሩ ጊዜ፣ እስራኤላውያንም እንደዚሁ ተሰብስበው በምጽጳ ሰፈሩ። 18የገለዓድ ሕዝብ አለቆችም እርስ በእርሳቸው፣ “በአሞናውያን ላይ ጦርነቱን የሚጀምር ሰው በገለዓድ ነዋሪዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆናል” ተባባሉ።