历代志下 35 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志下 35:1-27

约西亚守逾越节

1约西亚耶路撒冷为耶和华守逾越节。一月十四日,众人宰杀逾越节的祭牲。 2他指派祭司各尽其职,鼓励他们在耶和华的殿里事奉, 3又对将自己献给耶和华、负责教导以色列人的利未人说:“你们把圣约柜放在以色列大卫的儿子所罗门建的殿里,不用再扛在肩上。现在你们去事奉你们的上帝耶和华和祂的以色列子民吧。 4你们要按宗族和班次,依照以色列大卫和他儿子所罗门所写的指示,预备自己。 5你们要按你们弟兄所在宗族的班次,侍立在圣所,每个班次中要有几个利未宗族的人。 6你们要宰杀逾越节的羊羔,洁净自己,为你们的弟兄做好准备,依照耶和华借摩西所吩咐的去行。”

7约西亚从自己的产业中,捐出三万只绵羊羔和山羊羔,以及三千头公牛,赐给所有在场的人做逾越节的祭牲。 8他的众官员也自愿为民众、祭司和利未人捐献。管理上帝殿的希勒迦撒迦利亚耶歇献出两千六百只羊羔和三百头牛,给祭司做逾越节的祭牲。 9利未人的首领歌楠雅和他的两个兄弟示玛雅拿坦业,及哈沙比雅耶利约撒拔献出五千只羊羔和五百头牛,给利未人做逾越节的祭牲。

10一切都准备好后,依照王的吩咐,祭司站在自己的地方,利未人按照班次侍立。 11利未人宰杀逾越节的羊羔,祭司从他们手中接过血,洒在坛上,又剥去祭牲的皮。 12他们按照宗族把燔祭分给众人,好使他们按照摩西书上所写的,把祭物献给耶和华。献牛也是这样。 13他们按规定用火烤逾越节的羊羔,在锅里、罐里和盆里煮圣物,然后迅速分给民众。 14之后,利未人为自己和祭司预备祭物,因为做祭司的亚伦子孙要继续献燔祭和脂肪一直到晚上。 15负责歌乐的亚萨子孙依照大卫亚萨希幔和王的先见耶杜顿的吩咐,站在自己的岗位上;殿门守卫都看守各门,不必离开工作岗位,因为他们的弟兄利未人为他们预备了祭物。

16当天,一切事奉的事都办好了,他们就按约西亚王的命令守逾越节,又在耶和华的坛上献燔祭。 17所有在场的以色列人都在那时守逾越节,又守除酵节七天。 18撒母耳先知以来,在以色列从来没有守过这样的逾越节,以色列从没有君王像约西亚、祭司、利未人、所有在场的犹大人和以色列人,以及耶路撒冷的居民这样守过逾越节。 19这次逾越节是在约西亚执政第十八年庆祝的。

约西亚逝世

20约西亚办理完殿里的事后,埃及尼哥上来,要攻打幼发拉底河附近的迦基米施约西亚出兵拦阻。 21尼哥派使者对约西亚说:“犹大王啊,我与你没有恩怨。我今天来不是要攻击你,乃是要攻击与我作战的那一家。上帝吩咐我要速速完成,你不要与上帝作对,免得祂毁灭你,因为上帝与我同在。” 22约西亚却不听上帝借尼哥说的话。他没有退兵,反而乔装上阵,与尼哥会战于米吉多平原。 23约西亚王在战场上中箭受伤,就对仆人说:“我受了重伤,带我离开吧。” 24他的仆人就扶他下战车,上另一辆战车,送到耶路撒冷约西亚死在那里,葬在他祖先的坟墓里。所有犹大耶路撒冷的人都为他哀悼。 25耶利米约西亚作了哀歌,所有的男女歌乐手至今仍用这些哀歌纪念约西亚,成了以色列的传统。这些哀歌都记在《哀歌书》上。

26约西亚其他的事迹和他怎样忠心地遵行耶和华的律法, 27自始至终都记在《以色列和犹大的列王史》上。

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 35:1-27

ኢዮስያስ ፋሲካን ማክበሩ

35፥118-19 ተጓ ምብ – 2ነገ 23፥21-23

1ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ፋሲካን አደረገ፤ በመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካው በግ ታረደ። 2ካህናቱን በየአገልግሎታቸው መደበ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎትም እንዲተጉ አበረታታቸው። 3እስራኤልን ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩትና ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አላቸው፤ “የእግዚአብሔርን ታቦት የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ አኑሩ፤ በእናንተ ትከሻ አትሸከሙት፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ። 4በእስራኤል ንጉሥ በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን በተጻፈው መመሪያ መሠረት፣ እንደየቤተ ሰባችሁ በክፍል በክፍላችሁ ራሳችሁን አዘጋጁ።

5“ሌዋውያን ባልሆኑ ወንድሞቻችሁ አንጻር እንደየቤተ ሰቡ ምድብ በተቀደሰው ስፍራ ቁሙ፤ ለእያንዳንዱም የቤተ ሰብ ምድብ ሌዋውያን ይኑሩት። 6ከዚያም የፋሲካውን በጎች ዕረዱ፤ ራሳችሁን ቀድሱ፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘውም መሠረት ዕርዶቹን ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።”

7ኢዮስያስም እዚያ ለነበሩት ሕዝብ ሁሉ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆኑ በአጠቃላይ ሠላሳ ሺሕ በግና ፍየል እንዲሁም ሦስት ሺሕ ወይፈን ከራሱ ሀብት ሰጠ።

8ሹማምቱም ለሕዝቡ፣ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ በገዛ ፈቃዳቸው አዋጥተው ሰጡ። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቆች የሆኑት ኬልቅያስ፣ ዘካርያስና ይሒኤልም ለፋሲካ መሥዋዕት የሚቀርቡ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ በግ እንዲሁም ሦስት መቶ ወይፈን ሰጡ። 9ደግሞም ኮናንያ፣ ወንድሞቹ ሸማያና ናትናኤል እንደዚሁም የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸቢያ፣ ይዔኤልና ዮዛባት ለፋሲካ መሥዋዕት እንዲሆኑ አምስት ሺሕ በግና ፍየል አምስት መቶም በሬ ለሌዋውያኑ ሰጧቸው።

10የአገልግሎቱ ዝግጅት በተጠናቀቀ ጊዜ፣ ንጉሡ ባዘዘው መሠረት ካህናቱ በየክፍላቸው ከተመደቡት ሌዋውያን ጋር ቦታ ቦታቸውን ይዘው ቆሙ። 11የፋሲካው በጎች ታረዱ፤ ካህናቱ የተቀበሉትን ደም ረጩ፤ ሌዋውያኑም የበጎቹን ቈዳ ገፈፉ። 12በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈው ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡም፣ እንደየቤተ ሰቡና እንደየምድቡ ለሕዝቡ ለመስጠት የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለዩ፤ ወይፈኖቹንም እንደዚሁ አደረጉ። 13እነርሱም የፋሲካውን መሥዋዕት በሥርዐቱ መሠረት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቍርባን በምንቸት፣ በሰታቴና በድስት ቀቀሉ፤ ወዲያውኑም ለሕዝቡ አደሉ። 14ከዚህ በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱ ዝግጅት አደረጉ፤ ምክንያቱም ካህናቱ የአሮን ልጆች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሥቡን እስከ ሌሊት ድረስ ያቀርቡ ስለ ነበር ነው። ስለዚህ ሌዋውያኑ ለራሳቸውና ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ዝግጅት አደረጉ።

15መዘምራኑ የአሳፍ ዘሮች በዳዊት፣ በአሳፍ፣ በኤማንና በንጉሡ ባለ ራእይ በኤዶታም በተሰጠው መመሪያ መሠረት በቦታቸው ነበሩ። በእያንዳንዱ በር ላይ የነበሩት በር ጠባቂዎችም ሌዋውያን ወገኖቻቸው ስላዘጋጁላቸው፣ ከጥበቃ ቦታቸው መለየት አያስፈልጋቸውም ነበር።

16በዚህ ዐይነት የፋሲካን በዓል በማክበርና የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ በማቅረብ የእግዚአብሔር አገልግሎት ሁሉ ንጉሥ ኢዮስያስ ባዘዘው መሠረት በዚያኑ ቀን ተከናወነ። 17በዚያን ጊዜ በስፍራው የተገኙ እስራኤላውያን የፋሲካን በዓል አከበሩ፤ የቂጣንም በዓል እንደዚሁ ሰባት ቀን አከበሩ። 18ከነቢዩ ከሳሙኤል ዘመን ወዲህ እንዲህ ያለ ፋሲካ በእስራኤል ዘንድ ተከብሮ አያውቅም፤ ኢዮስያስ ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑ፣ ከመላው ይሁዳና ከእስራኤል፣ በዚያ ከነበሩትም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ጋር እንዳከበረው አድርጎ ያከበረ አንድም የእስራኤል ንጉሥ የለም። 19ይህ ፋሲካ የተከበረው በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ ስምንኛው ዓመት ነበር።

የኢዮስያስ መሞት

35፥20–36፥1 ተጓ ምብ – 2ነገ 23፥28-30

20ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢዮስያስ ቤተ መቅደሱን አደራጅቶ ባጠናቀቀ ጊዜ፣ የግብፅ ንጉሥ ኒካዑ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ በከርከሚሽ ላይ ለመዋጋት ወጣ፤ ኢዮስያስም ጦርነት ሊገጥመው ወጣ። 21ኒካዑ ግን፣ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፤ አንተንና እኔን የሚያጣላን ምንድን ነው? ጦርነት ከገጠምሁት ቤት ጋር እንጂ በአሁኑ ጊዜ አንተን የምወጋህ አይደለሁም፤ እግዚአብሔር እንድፈጥን አዝዞኛል፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር ያለውን እግዚአብሔርን መቃወምህን ተው፤ አለዚያ ያጠፋሃል” አለው።

22ኢዮስያስ ግን ሌላ ሰው መስሎ በጦርነት ሊገጥመው ወጣ እንጂ ወደ ኋላ አልተመለሰም፤ በመጊዶ ሜዳ ላይ ሊዋጋው ሄደ እንጂ፣ ኒካዑ ከእግዚአብሔር ታዝዞ የነገረውን ሊሰማ አልፈለገም።

23ቀስተኞች ንጉሥ ኢዮስያስን ወጉት፤ እርሱም የጦር መኰንኖቹን፣ “ክፉኛ ቈስያለሁና ከዚህ አውጡኝ” አላቸው። 24ስለዚህ ከሠረገላው አውርደው በራሱ ሠረገላ ላይ አስቀምጠውት ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ እዚያም ሞተ፤ በአባቶቹ መካነ መቃብር ተቀበረ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሁሉ አለቀሱለት።

25ኤርምያስ ለኢዮስያስ የሐዘን እንጕርጕሮ ግጥም ጻፈለት፤ ወንዶችና ሴቶች ሙሾ አውራጆች ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ በዚህ ግጥም ኢዮስያስን ያስታውሱታል፤ ይህም በእስራኤል የተለመደ ሆኖ በልቅሶ ግጥም መጽሐፍ ተጽፏል።

26በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ድርጊትና በእግዚአብሔር የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት ያከናወነው መንፈሳዊ ተግባር፣ 27ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ያደረገው ሁሉ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል።