历代志下 31 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志下 31:1-21

希西迦的改革

1当一切都办妥后,所有在场的以色列人就前往犹大各城邑,打碎神柱,砍倒亚舍拉神像,又拆毁犹大便雅悯以法莲玛拿西境内所有的丘坛和祭坛,然后各自返回自己的城邑和家园。

2希西迦分派祭司和利未人的班次,使他们各司其职,献上燔祭和平安祭,在耶和华殿门内事奉,称谢、颂赞耶和华。 3王又从自己的产业中划分出一部分作为早晚的燔祭,以及安息日、朔日及耶和华律法规定的其他节期的燔祭。

4他又吩咐耶路撒冷的居民将祭司和利未人当得的份交给他们,好使他们专心执行耶和华的律法。 5谕旨一出,以色列人就献出许多初熟的五谷、新酒、新油、蜂蜜、田间的出产及各样物品的十分之一,数量极多。 6住在犹大各城的以色列人和犹大人也送来牛羊的十分之一,以及献给他们的上帝耶和华的圣物,就是十一奉献,把它们堆积成堆。 7他们从三月开始堆积,到七月才结束。 8希西迦与众官员来了,看见堆积起来的供物,就称颂耶和华,又为耶和华的以色列子民祝福。 9希西迦向祭司和利未人询问这些供物的事, 10撒督家族的亚撒利雅大祭司回答说:“自从民众把这些供物送到耶和华的殿里以来,我们不但吃得饱,还剩下许多。因为耶和华赐福给祂的子民,所以才有这么多剩余。”

11于是,希西迦下令在耶和华的殿里预备库房。他们预备好后, 12便忠心地把供物、十一奉献和圣物放进库房。利未歌楠雅总管这事,他的兄弟示每做助手。 13耶歇亚撒细雅拿哈亚撒黑耶利末约撒拔以列伊斯玛基雅玛哈比拿雅做监督协助歌楠雅和他兄弟示每,他们都是希西迦王和管理上帝殿的亚撒利雅指派的。 14看守东门的利未人音拿的儿子可利,负责管理民众自愿献给上帝的礼物,以及分发献给耶和华的供物和至圣之物。 15伊甸珉雅珉耶书亚示玛雅亚玛利雅示迦尼雅在祭司所在的各城忠心地协助可利,按照班次,不分老幼,将物品分给他们的弟兄。 16此外,他们还分给三岁及三岁以上、姓名记在家谱上、每天在耶和华的殿中按班次供职的男子, 17并分给按宗族登记在家谱上的祭司,按班次和职任分给二十岁及二十岁以上的利未人, 18也按照家谱分给他们的妻子儿女,因为他们诚心洁净自己。 19至于住在各城郊野做祭司的亚伦子孙,各城都有指定的人把应得之份分给祭司中所有的男子和登记在家谱上的利未人。

20希西迦犹大全境都如此行,做他的上帝耶和华视为良善、正直和忠心的事。 21无论是在上帝的殿中事奉,还是遵行律法和诫命,他都寻求他的上帝,尽心去做。因此,他行事顺利。

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 31:1-21

1ይህ ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ፣ በዚያ የነበሩት እስራኤላውያን ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው፣ የማምለኪያ ድንጋዮችን ሰባበሩ፤ የአሼራን ምስል ዐምዶች ቈረጡ፤ እንዲሁም በመላው ይሁዳና በብንያም፣ በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን የኰረብታ መስገጃዎችና መሠዊያዎች አጠፉ፤ እስራኤላውያን እነዚህን ሁሉ ካጠፉ በኋላ ወደየከተሞቻቸውና ወደየርስታቸው ተመለሱ።

ለካህናት የተደረገ ስጦታ

31፥20-21 ተጓ ምብ – 1ነገ 18፥5-7

2ሕዝቅያስ ካህናቱና ሌዋውያኑ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት31፥2 በትውፊት፣ የሰላም መሥዋዕት ይባላል። እንዲያቀርቡ፣ እንዲያገለግሉና እንዲያመሰግኑ እንዲሁም በእግዚአብሔር ማደሪያ ደጆች ውዳሴውን እንዲዘምሩ፣ ካህናትንም ሆኑ ሌዋውያንን እያንዳንዳቸውን እንደየተግባራቸው በየክፍሉ መደባቸው። 3በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ንጉሡ ጧትና ማታ እንደዚሁም በየሰንበቱ፣ በየወሩ መባቻውና በተወሰኑ በዓላት፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ከራሱ ንብረት ሰጠ። 4ካህናቱና ሌዋውያኑም ሙሉ ጊዜያቸውን ለእግዚአብሔር ሕግ አገልግሎት ማዋል ይችሉ ዘንድ፣ በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ተገቢውን ድርሻ እንዲሰጣቸው አዘዘ። 5ትእዛዙ እንደ ወጣ እስራኤላውያን ወዲያውኑ የእህሉንና የአዲሱን ወይን ጠጅ፣ የዘይቱንና የማሩን እንዲሁም የዕርሻውን ፍሬ ሁሉ በኵራት በልግስና ሰጡ፤ ካላቸው ከማንኛውም ነገር ሁሉ ላይ እጅግ ብዙ የሆነ ዐሥራት አውጥተው አመጡ። 6በይሁዳ ከተሞች ይኖሩ የነበሩት የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎችም ከከብቶቻቸው፣ ከበግና ከፍየል መንጎቻቸውና ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ከለዩአቸው የተቀደሱ ነገሮች ዐሥራት አውጥተው አመጡ፤ ከመሩትም። 7ይህንም በሦስተኛው ወር ጀምረው፣ በሰባተኛው ወር አጠናቀቁ። 8ሕዝቅያስና ሹማምቱም መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ሕዝቡን እስራኤልንም ባረኩ።

9ሕዝቅያስም ካህናቱንና ሌዋውያኑን ስለ ክምሩ ጠየቃቸው፤ 10ከሳዶቅ ቤተ ሰብ የሆነው ሊቀ ካህናቱ ዓዛርያስም፣ “ሕዝቡ ስጦታውን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ማምጣት ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ በቂ ምግብ አግኝተናል፤ ብዙም ተርፎናል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለባረከም ይህን ያህል ብዛት ያለው ሊተርፍ ችሏል” አለ።

11ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ጎተራ እንዲያዘጋጁ አዘዛቸው፤ እነርሱም አዘጋጁ። 12ከዚያም ስጦታውን፣ ዐሥራቱንና የተቀደሱ ስጦታዎቹን በታማኝነት አምጥተው አስገቡ። ሌዋዊው ኮናንያ የእነዚሁ ዕቃዎች ኀላፊ ሲሆን፣ ወንድሙ ስሜኢ ደግሞ በማዕረግ ሁለተኛ ነበር። 13ይሒዒል፣ ዓዛዝያ፣ ናሖት፣ አሣሄል፣ ይሬሞት፣ ዮዛባት፣ ኤሊኤል፣ ሰማኪያ፣ መሐትና በናያስ በንጉሡ ሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት ኀላፊ በዓዛርያስ ተሹመው በኮናንያና በወንድሙ በሰሜኢ ሥር ሆነው ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።

14የምሥራቁ በር ጠባቂ የሆነው የሌዋዊው የይምና ልጅ ቆሬ ደግሞ በበጎ ፈቃድ ለእግዚአብሔር በቀረበው ስጦታ ላይ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትንም ነገሮች ለማከፋፈል፣ ኀላፊ ነበረ። 15ዔድን፣ ሚንያሚን፣ ኢያሱ፣ ሸማያ፣ አማርያና ሴኬንያ በካህናቱ ከተሞች ተገኝተው፣ ለካህናት ወገኖቻቸው ለታላላቆቹም ሆነ ለታናናሾቹ፣ እንደየምድባቸው፣ በማከፋፈሉ ረገድ በታማኝነት ረዱት።

16በተጨማሪም፣ ስማቸው በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የነበረና የየዕለት ልዩ ልዩ ተግባራቸውን እንደየኀላፊነታቸው መጠንና እንደየምድብ ሥራቸው ለማከናወን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መግባት ለሚችሉት፣ ዕድሜያቸው ሦስት ዓመትና ከዚያም በላይ ለሆናቸው ወንዶች ልጆች እንደዚሁ አከፋፈሉ። 17በትውልድ መዝገብ በየቤተ ሰባቸው ተቈጥረው ለገቡት ካህናት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ለሆናቸው ሌዋውያን እንደየኀላፊነታቸው መጠንና እንደየምድብ ሥራቸው አካፈሏቸው። 18በዚህ የትውልድ መዝገብ ላይ የተዘረዘሩትን መላውን የማኅበረ ሰቡን ሕፃናት፣ ሚስቶችን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ጨመሯቸው፤ ራሳቸውን በመቀደስ ታማኞች ነበሩና።

19በከተሞቻቸው ዙሪያ ባሉት የዕርሻ ቦታዎች፣ ወይም በሌሎች ከተሞች ሁሉ ለሚኖሩት ለካህናቱ ለአሮን ዘሮች፣ በመካከላቸው ላሉት ወንዶችና በሌዋውያን የትውልድ መዝገብ ለተመዘገቡት ሁሉ እንዲያከፋፍሉ በየስማቸው የተጻፉ ሰዎች ነበሩ።

20ሕዝቅያስ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መልካም፣ ቅንና ታማኝ ሆኖ በመገኘት በመላው ይሁዳ የፈጸመው ተግባር ይህ ነው። 21የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በማገልገልም ሆነ፣ ለእግዚአብሔር ሕግና ትእዛዝ በመገዛት አንጻር ያደረገውን ሁሉ በፍጹም ልቡ አምላኩን በመፈለግ አከናወነ፤ ተሳካለትም።