历代志下 18 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志下 18:1-34

米该雅先知警告亚哈

1约沙法极有财富和尊荣,他与亚哈结为姻亲。 2几年后,约沙法下到撒玛利亚拜访亚哈亚哈宰了很多牛羊款待他和他的随从,又游说他与自己一起去攻打基列拉末3以色列亚哈犹大约沙法说:“你愿意与我一起去攻打基列拉末吗?”约沙法回答说:“你我不分彼此,我的民就是你的民,我必与你同去。” 4约沙法又对以色列王说:“你要先求问耶和华。”

5于是,以色列王召来四百名先知,问他们:“我可以去攻打基列拉末吗?”他们说:“可以去,上帝必把那城交在王手中。” 6约沙法问:“这里没有耶和华的先知供我们求问吗?” 7以色列王回答说:“还有一个人,是音拉的儿子米该雅,我们可以托他求问耶和华。可是我厌恶他,因为他给我的预言都是有凶无吉。”约沙法说:“王不要这样说。” 8以色列王召来一名内侍,说:“你快把音拉的儿子米该雅带来。”

9以色列王和犹大约沙法身穿朝服,坐在撒玛利亚城门前麦场的宝座上,众先知都在他们面前说预言。 10基拿拿的儿子西底迦造了两只铁角,说:“耶和华这样说,‘你必用这铁角抵亚兰人,直到毁灭他们。’” 11所有的先知也都预言说:“去攻打基列拉末吧,一定得胜,耶和华必将那城交在王的手中。”

12去召米该雅的使者对米该雅说:“众先知都异口同声地向王说吉言,你也像他们一样说些吉言吧。” 13米该雅回答说:“我凭永活的耶和华起誓,我的上帝对我说什么,我就说什么。” 14米该雅来到王面前,王就问他:“米该雅啊,我们可不可以去攻打基列拉末?”米该雅回答说:“上去攻打吧,一定得胜,敌人必被交在你们手中。” 15王却说:“我要嘱咐你多少次,你才肯奉耶和华的名对我说实话呢?” 16米该雅说:“我看见所有以色列人四散在山上,好像没有牧人的羊群一样。耶和华说,‘这些人没有主人,让他们各自平安地回家去吧。’”

17以色列王对约沙法说:“我不是告诉过你吗?他给我的预言都是有凶无吉。” 18米该雅说:“你们要听耶和华的话。我看见耶和华坐在宝座上,众天军侍立在祂左右。 19耶和华说,‘谁愿意去引诱以色列亚哈基列拉末去送死呢?’众天军议论纷纷。 20后来,有一个灵站出来对耶和华说他愿意去。耶和华问他用什么方法, 21他说,‘我要做谎言之灵,进入他众先知的口中。’耶和华说,‘你必能成功,就这样做吧。’ 22现在,耶和华已经把谎言之灵放进这些先知口中,耶和华已决意降祸给你。”

23基拿拿的儿子西底迦听了米该雅的话就上前打他的脸,说:“耶和华的灵怎会离开我向你说话呢?” 24米该雅说:“你躲进密室的那天就知道了。” 25以色列王下令说:“把米该雅交给亚们总督和约阿施王子, 26告诉他们,‘王说,要把这人关进监牢,只给他一些饼和水,直到我平安地回来。’” 27米该雅说:“你若能够平安回来,耶和华就没有借着我说话。”他又说:“众民啊,你们都要记住我的话。”

亚哈之死

28以色列王和犹大约沙法出兵攻打基列拉末29以色列王对约沙法说:“我要改装上阵,你就穿王袍吧。”以色列王改装后,他们就上阵去了。 30亚兰王已经吩咐战车长不要与对方的大小军兵交锋,只攻击以色列王。 31战车长看见约沙法,以为他就是以色列王,便转身攻击他。约沙法高声喊叫,耶和华上帝就帮助他,使敌人离开他。 32战车长见他不是以色列王,便不再追杀他。 33有人随手放了一箭,射进了以色列王的铠甲缝中。王对驾车的说:“调转车头拉我离开战场吧,我受了重伤。” 34那天的战事非常激烈,以色列王勉强支撑着站在车上迎战亚兰人,直到黄昏。太阳下山的时候,他就死了。

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 18:1-34

ሚካያ በአክዓብ ላይ ትንቢት ተናገረ

18፥1-27 ተጓ ምብ – 1ነገ 22፥1-28

1ኢዮሣፍጥ ታላቅ ሀብትና ክብር ባገኘ ጊዜ፣ ከአክዓብ ጋር በጋብቻ ተሳሰረ። 2ከጥቂት ዓመታት በኋላም አክዓብን ሊጐበኝ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለእርሱና አብሮት ለነበረው ሕዝብ ብዙ በግና በሬ ዐረደ፤ ከዚያም በሬማት ዘገለዓድ ላይ አደጋ እንዲጥል አግባባው። 3የእስራኤል ንጉሥ አክዓብም የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፣ “ሬማት ዘገለዓድን ለመውጋት አብረኸኝ ትሄዳለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮሣፍጥም፣ “እኔ እንደ አንተው ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ነው፤ በጦርነቱ አብረናችሁ እንሰለፋለን” ሲል መለሰለት። 4ደግሞም ኢዮሣፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ፣ “አስቀድመህ ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቅ” አለው።

5ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አራት መቶ ነቢያትን በአንድነት ሰብስቦ፣ “ሬማት ዘገለዓድን ለመውጋት ልሂድን ወይስ ልቅር?” ሲል ጠየቃቸው።

እነርሱም፣ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ሂድ” ብለው መለሱለት።

6ኢዮሣፍጥ ግን፣ “እንጠይቀው ዘንድ ሌላ የእግዚአብሔር ነቢይ እዚህ የለምን?” አለ።

7የእስራኤልም ንጉሥ ለኢዮሣፍጥ፣ “መኖሩንማ በእርሱ አማካይነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንጠይቅበት አንድ ሰው አሁንም አለ፤ ነገር ግን ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ ደግ ትንቢት ስለማይናገር እጠላዋለሁ፤ እርሱም የይምላ ልጅ ሚካያ ነው” ሲል መለሰ።

ኢዮሣፍጥም፣ “ንጉሥ እንዲህ ማለት አይገባውም” አለው።

8የእስራኤልም ንጉሥ ከሹማምቱ አንዱን ጠርቶ “ሂድና የይምላን ልጅ ሚካያን በፍጥነት አምጣው” አለው።

9የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ልብሰ መንግሥታቸውን ለብሰው፣ በሰማርያ ቅጥር በር መግቢያ አጠገብ ባለው ዐውድማ ላይ በየዙፋናቸው ተቀምጠው፣ ነቢያቱ ሁሉ በፊታቸው ትንቢት ይናገሩ ነበር። 10የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሶርያውያን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’ ” አለ።

11ሌሎቹ ነቢያት ሁሉ፣ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና፣ በሬማት ገለዓድ ላይ አደጋ ጣልባት” በማለት ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር።

12ሚካያን ሊጠራ ሄዶ የነበረውም መልእክተኛ፣ “እነሆ፣ ሌሎቹ ነቢያት በአንድ አፍ ሆነው፣ ንጉሡ ድል እንደሚያደርግ እየተነበዩ ነው፤ የአንተም ቃል እንደ ቃላቸው ይሁን፤ ንጉሡን ደስ የሚያሰኘውን ተናገር” አለው።

13ሚካያ ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! አምላኬ የሚለውን ብቻ እናገራለሁ” አለ።

14እዚያ በደረሰም ጊዜ ንጉሡ፣ “ሚካያ ሆይ፤ ሬማት ዘገለዓድን ለመውጋት እንሂድ ወይስ ልቅር?” ሲል ጠየቀው።

እርሱም መልሶ፣ “ሂዱና ድል አድርጉ፤ በእጃችሁ ዐልፈው ይሰጣሉና” አለው።

15ንጉሡም፣ “ከእውነት በቀር ምንም ነገር በእግዚአብሔር ስም እንዳትነግረኝ ስንት ጊዜ አምልሃለሁ?” አለው።

16ከዚያም ሚካያ፣ “እስራኤል ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበታትነው አየሁ፤ እግዚአብሔርም፣ ‘እነዚህ ሰዎች ጌታ የላቸውም፤ እያንዳንዱም በሰላም ወደየቤቱ ይመለስ’ ብሏል” ሲል መለሰ።

17የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፣ “ስለ እኔ ክፉ ብቻ እንጂ፣ ደግ ትንቢት እንደማይናገር አልነገርሁህምን?” አለው። 18ሚካያም በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣ የሰማይም ሰራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ። 19እግዚአብሔርም፣ ‘የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ በሬማት ገለዓድ ላይ ዘምቶ እዚያው እንዲሞት ማን ያሳስተው?’ አለ።

“አንዱ አንድ ሐሳብ፣ ሌላውም ሌላ ሐሳብ አቀረበ። 20በመጨረሻም አንድ መንፈስ ወደ ፊት ወጥቶ፣ በእግዚአብሔር ፊት በመቆም፣ ‘እኔ አሳስተዋለሁ’ አለ።

እግዚአብሔርም፣ ‘እንዴት አድርገህ?’ ሲል ጠየቀው።

21“እርሱም፣ ‘እሄድና በነቢያቱ ሁሉ አፍ የሐሰት መንፈስ እሆናለሁ’ አለ።

እግዚአብሔርም፣ ‘እንግዲያውስ ሂደህ አሳስተው፤ ይሳካልሃልም’ አለው።

22“አሁንም እነሆ፣ እግዚአብሔር በእነዚህ ነቢያትህ አፍ የሐሰት መንፈስ አኖረ፤ እግዚአብሔርም ጥፋት አዝዞብሃል”።

23ከዚያም የክንዓናም ልጅ ሴዴቅያስ ወጥቶ ሚካያን በጥፊ መታውና፣ “ለመሆኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ያነጋገረህ፣ በየት በኩል ዐልፎኝ ነው?” አለው።

24ሚካያም፣ “ለመሸሸግ ወደ እልፍኝህ በምትሄድበት በዚያ ዕለት ታገኘዋለህ” አለው።

25ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ እንዲህ ሲል አዘዘ፤ “ሚካያን ይዛችሁ ወደ ከተማዪቱ ገዥ ወደ አሞንና ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ ኢዮአስ መልሳችሁ ላኩት፤ 26እነርሱንም፣ ‘ንጉሡ፣ ይህን ሰው እስር ቤት አስገቡት፤ በደኅና እስክመለስም ድረስ ከደረቅ ቂጣና ከውሃ በስተቀር ምንም አትስጡት ብሏል’ በሏቸው።”

27ሚካያም፣ “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አልተናገረም ማለት ነው!” አለ፤ ቀጥሎም፣ “እናንተ ሰዎች ሁላችሁ ስሙኝ” አለ።

አክዓብ በሬማት ገለዓድ ተገደለ

18፥28-34 ተጓ ምብ – 1ነገ 22፥29-36

28ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ወደ ሬማት ገለዓድ ወጡ። 29የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፣ “እኔ ልብሴን ለውጬ ወደ ጦርነቱ እገባለሁ፤ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ” አለው። ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን ለውጦ ሌላ ሰው መስሎ ወደ ጦርነቱ ገባ።

30በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ የሠረገላ አዛዦቹን፣ “ከእስራኤል ንጉሥ በቀር፣ ትንሽም ሆነ ትልቅ ከሌላ ከማንም ጋር አትዋጉ” ብሎ አዘዛቸው። 31የሠረገላው አዛዦችም ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ፣ “የእስራኤል ንጉሥ ይህ ነው” ብለው አሰቡ፤ ሊወጉትም ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥ ግን ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ረዳው፤ አምላክም ከእርሱ መለሳቸው፤ 32የሠረገላ አዛዦቹም የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን በተረዱ ጊዜ እርሱን ከማሳደድ ተመለሱ።

33ይሁን እንጂ ቀስቱን በነሲብ ቢያስፈነጥረው፣ በጥሩሩ መጋጠሚያዎች መካከል ዐልፎ የእስራኤልን ንጉሥ ወጋው። ንጉሡም ሠረገላ ነጂውን “ተመለስና ከጦርነቱ አውጣኝ፤ ቈስያለሁና” አለው። 34ጦርነቱ ቀኑን ሙሉ እንደ ተፋፋመ ዋለ፤ የእስራኤልም ንጉሥ በሶርያውያን ፊት ለፊት በሠረገላው ላይ እስከ ምሽት ድረስ ተደግፎ ነበር፤ ፀሓይ ስትጠልቅም ሞተ።