历代志上 26 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志上 26:1-32

圣殿的守卫

1以下是殿门守卫的班次:

可拉亚萨的后代有可利的儿子米施利米雅2米施利米雅的长子是撒迦利亚,次子是耶叠,三子是西巴第雅,四子是耶提聂3五子是以拦,六子是约哈难,七子是以利约乃4俄别·以东的长子是示玛雅,次子是约萨拔,三子是约亚,四子是沙甲,五子是拿坦业5六子是亚米利,七子是以萨迦,八子是毗乌利太。上帝特别赐福俄别·以东6他儿子示玛雅有几个儿子都很能干,在各自的家族中做首领。 7他们是俄得尼利法益俄备得以利萨巴。他们的亲族以利户西玛迦也很能干。 8这些都是俄别·以东的子孙,他们和他们的儿子及亲族共有六十二人,都是能干称职的人。 9米施利米雅的儿子及亲族共十八人,都很能干。 10米拉利的后代何萨的长子是申利,他本来不是长子,是被他父亲立为长子的。 11次子是希勒迦,三子是底巴利雅,四子是撒迦利亚何萨的儿子及亲族共十三人。

12这些按族长分成小组的殿门守卫在耶和华的殿里按班次供职,与他们的亲族一样。 13他们无论大小,都按照族系抽签,以决定看守哪个门。 14示利米雅抽中东门,他儿子撒迦利亚是个精明的谋士,抽中北门。 15俄别·以东抽中南门,他儿子抽中库房。 16书聘何萨抽中西门和上行之路的沙利基门,两班相对而立。 17每天有六个利未人守东门,四人守北门,四人守南门,守库房的二人一组。 18守卫西面街道的有四人,守卫走廊的有二人。 19以上是可拉的子孙和米拉利的子孙守门的班次。

圣殿里的其他职务

20利未亚希雅负责掌管上帝殿里的库房和放奉献之物的库房。 21革顺拉但的子孙中做族长的有耶希伊利22耶希伊利的两个儿子西坦约珥负责管理耶和华殿里的库房。 23暗兰族、以斯哈族、希伯仑族、乌歇族也各有其职。 24摩西的孙子——革舜的儿子细布业是库房的主管。 25细布业的亲族有以利以谢以利以谢的儿子是利哈比雅利哈比雅的儿子是耶筛亚耶筛亚的儿子是约兰约兰的儿子是细基利细基利的儿子是示罗密26示罗密及其亲族负责管理库房中的奉献之物,这些物品是大卫王、众族长、千夫长、百夫长和将领献给上帝的圣物。 27他们把战争中掳掠的财物献出来,以备建造耶和华的殿。 28撒母耳先见、基士的儿子扫罗尼珥的儿子押尼珥洗鲁雅的儿子约押及其他人奉献的圣物都由示罗密及其亲族管理。

29以斯哈族的基拿尼雅及其众子做官长和士师,为以色列管理圣殿以外的事务。 30希伯仑族的哈沙比雅及其亲族一千七百人都很能干,他们在以色列约旦河以西办理耶和华和王的事务。 31按家谱记载,希伯仑宗族的族长是耶利雅大卫执政第四十年,经过调查,在基列雅谢希伯仑族中找到一些能干的人。 32耶利雅的亲族有两千七百人,都是能干的族长。大卫王派他们在吕便支派、迦得支派和玛拿西半个支派中办理一切有关上帝和王的事务。

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 26:1-32

የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች

1የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች አመዳደብ፤

ከቆሬያውያን ወገን፤

ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም። 2ሜሱላም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤

የመጀመሪያው ዘካሪያስ፣

ሁለተኛው ይዲኤል፣

ሦስተኛው ዮዛባት፣

አራተኛው የትኒኤል፣

3አምስተኛው ኤላም፣

ስድስተኛው ይሆሐናን፣

ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ።

4ዖቤድኤዶምም እንደዚሁ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤

የመጀመሪያው ሸማያ፣

ሁለተኛው ዮዛባት፣

ሦስተኛው ኢዮአስ፣

አራተኛው ሣካር፣

አምስተኛው ናትናኤል፣

5ስድስተኛው ዓሚኤል፣

ሰባተኛው ይሳኮር፣

ስምንተኛው ፒላቲ፤

እግዚአብሔር ዖቤድኤዶምን ባርኮታልና።

6እንዲሁም ልጁ ሸማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በቂ ችሎታ ስለ ነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎች ሆነው ነበር። 7የሸማያ ወንዶች ልጆች፤

ዖትኒ፣ ራፋኤል፣ ዖቤድ፣ ኤልዛባድ፤

ዘመዶቹ ኤሊሁና ሰማክያም እንደዚሁ በቂ ችሎታ ነበራቸው።

8እነዚህ ሁሉ የዖቤድኤዶም ዘሮች ሲሆኑ፣ እነርሱም ሆኑ ወንዶች ልጆቻቸውና ቤተ ዘመዶቻቸው ሥራውን ለመሥራት በቂ ችሎታ ነበራቸው። የዖቤድኤዶም ዘሮች በአጠቃላይ ስድሳ ሁለት ነበሩ።

9ሜሱላም በቂ ችሎታ ያላቸው ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶች ነበሩት፤ ቍጥራቸውም በአጠቃላይ ዐሥራ ስምንት ነበረ።

10ከሜራሪ ወገን የሆነው ሖሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤

የመጀመሪያው ሽምሪ ነበረ፤ የበኵር ልጅ ባይሆንም እንኳ፣ አባቱ ቀዳሚ አድርጎት ነበር።

11ሁለተኛው ኬልቅያስ፣ ሦስተኛው ጥበልያ፣ አራተኛው ዘካርያስ።

የሖሳ ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶቹ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

12የቤተ መቅደሱም ጠባቂዎች በአለቆቻቸው ሥር ተመድበው ልክ እንደ ቤተ ዘመዶቻቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ለማከናወን ምድብ ተራ ነበራቸው። 13ለእያንዳንዱም በር ወጣት ሽማግሌ ሳይባል ለሁሉም እኩል ዕጣ ተጣለ።

14የምሥራቁ በር ዕጣ ለሴሌምያ ወጣ።

ከዚያም ምክር ዐዋቂ ለሆነው ለልጁ ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ እርሱም የሰሜኑ በር ደረሰው።

15የደቡቡ በር ዕጣ ለዖቤድኤዶም ሲወጣ፣ የግምጃ ቤቱ ዕጣ ደግሞ ለልጆቹ ወጣ።

16የምዕራቡ በርና በላይኛው መንገድ ላይ የሚገኘው የሸሌኬት በር ዕጣዎች ለሰፊንና ለሖሳ ወጣ።

በአንዱ ዘብ ጥበቃ ትይዩ ሌላ ዘብ ጥበቃ ነበረ፤

17በየቀኑም በምሥራቅ በኩል ስድስት፣

በሰሜን በኩል አራት፣

በደቡብ በኩል አራት፣

በዕቃ ቤቱ በኩል በአንድ ጊዜ ሁለት ሌዋውያን ይጠብቁ ነበር።

18በምዕራቡ በኩል የሚገኘውን አደባባይ ደግሞ በመንገዱ ላይ አራት፣ በአደባባዩ ላይ ደግሞ ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር።

19እንግዲህ የቆሬና የሜራሪ ዘሮች የሆኑት በር ጠባቂዎች ድልድል ይህ ነበር።

የግምጃ ቤት ኀላፊዎችና ሌሎች ሹማምት

20ከሌዋውያን መካከል አኪያ የእግዚአብሔር ቤት ግምጃ ቤትና የተቀደሱት ዕቃዎች የሚቀመጡበት ግምጃ ቤት ኀላፊ ነበረ።

21የለአዳን ዘሮች፣ በለአዳን በኩል ጌድሶናውያን የሆኑትና ለጌድሶናዊው ለለአዳን ቤተ ሰቦች አለቆች የሆኑት የለአዳን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ ይሒኤሊ፣ 22የይሒኤሊ ወንዶች ልጆች፣ ዜቶምና ወንድሙ ኢዩኤል። እነዚህም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት ኀላፊዎች ነበሩ።

23ከእንበረማውያን፣ ከይስዓራውያን፣ ከኬብሮናውያን፣ ከዑዝኤላውያን፤

24የሙሴ ልጅ የጌርሳም ዘር የሆነው ሱባኤል የግምጃ ቤቱ የበላይ ኀላፊ ነበረ። 25በአልዓዛር በኩል የሚዛመዱት፤ ልጁ ረዓብያ፣ ልጁ የሻያ፣ ልጁ ኢዮራም፣ ልጁ ዝክሪ፣ ልጁ ሰሎሚት።

26ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተ ሰቡ ኀላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዛዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች ነበሩ። 27በጦርነት ከተገኘውም ምርኮ ከፊሉን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ማደሻ እንዲሆን ቀደሱት። 28ባለ ራእዩ ሳሙኤል፣ የቂስ ልጅ ሳኦል፣ የኔር ልጅ አበኔር፣ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የቀደሱትን ሁሉና እንዲሁም ሌሎቹን ንዋያተ ቅድሳት ሰሎሚናትና ቤተ ዘመዶቹ ይጠብቁ ነበር።

29ከይስዓራውያን፤

ከናንያና ወንዶች ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ባለው ሥራ በእስራኤል ላይ ሹማምትና ዳኞች ሆነው ተመደቡ።

30ከኬብሮናውያን፤

ለሐሻብያ፣ ጠንካራና ጐበዝ የሆኑ አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰዎች ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ በሚገኘው የእስራኤል ምድር ላለው የእግዚአብሔር ሥራና ለንጉሡም አገልግሎት ኀላፊዎች ሆነው ተመደቡ። 31በኬብሮናውያን በኩል በቤተ ሰቦቻቸው የትውልድ መዝገብ መሠረት ይሪያ አለቃቸው ነበረ።

በዳዊት ዘመነ መንግሥት በአርባኛው ዓመት መዛግብቱ ተመርምረው ስለ ነበር፣ በገለዓድ ውስጥ ኢያዜር በተባለ ቦታ ከኬብሮናውያን መካከል ጠንካራ ሰዎች ሊገኙ ችለዋል። 32ይሪያም ጠንካሮችና የቤተ ሰባቸው አለቆች የሆኑ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ሥጋ ዘመዶች ነበሩት። ንጉሥ ዳዊትም እነዚህን የእግዚአብሔር ለሆነውና የንጉሡም በሆነው ጕዳይ ላይ ሮቤልን፣ ጋድንና የምናሴን ነገድ እኩሌታ ኀላፊ አድርጎ ሾማቸው።