历代志上 23 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志上 23:1-32

利未人的职务

1大卫年纪老迈,寿数将尽,就立他儿子所罗门以色列王。 2他召集了以色列的众首领、祭司和利未人。 3凡三十岁以上的利未人都在统计之列,共有三万八千男子, 4其中有两万四千人在耶和华的殿里司职,六千人做官长和审判官, 5四千人守门,四千人用大卫提供的乐器颂赞耶和华。 6大卫利未革顺哥辖米拉利的子孙分成班次。

7革顺的儿子有拉但示每8拉但有长子耶歇,还有细坦约珥,共三个儿子, 9都是拉但族的族长。示每的儿子有示罗密哈薛哈兰三人。 10示每的儿子还有雅哈细拿耶乌施比利亚四人。 11雅哈是长子,细拿是次子。耶乌施比利亚的子孙不多,所以合为一族。

12哥辖暗兰以斯哈希伯仑乌薛四个儿子。 13暗兰的儿子是亚伦摩西亚伦和他的子孙永远被分别出来事奉耶和华,向祂献至圣之物,在祂面前烧香,奉祂的名祝福,直到永远。 14上帝的仆人摩西的子孙归在利未支派的名下。 15摩西的儿子是革舜以利以谢16革舜的长子是细布业17以利以谢只有一个儿子利哈比雅,但利哈比雅子孙众多。 18以斯哈的长子是示罗密19希伯仑的长子是耶利雅,次子是亚玛利亚,三子是雅哈悉,四子是耶加缅20乌薛的长子是米迦,次子是耶西雅

21米拉利的儿子是抹利姆示抹利的儿子是以利亚撒基士22以利亚撒终生没有儿子,只有女儿,同族人基士的儿子娶了她们为妻。 23姆示的三个儿子是末力以得耶利摩24以上是利未各宗族的子孙,他们登记在各自族长的名下,凡二十岁以上的男子都在耶和华的殿里任职。 25大卫说:“以色列的上帝耶和华已使祂的子民安享太平,祂永远住在耶路撒冷26利未人再不用抬圣幕和其中的器皿了。” 27按照大卫临终时的嘱咐,二十岁以上的利未人都已被统计。 28他们的任务是帮助亚伦的子孙在耶和华的殿里司职,管理殿的院子和厢房,负责洁净圣物等事务。 29他们还负责供饼、做素祭的细面粉、无酵薄饼的调和、烤制、分量和尺寸。 30他们每天早晚要肃立、颂赞耶和华, 31每逢安息日、朔日23:31 朔日”即每月初一。或其他节期,他们要按照规定的数目将燔祭献给耶和华, 32并负责看守会幕和圣所,帮助他们的亲族——亚伦的子孙在耶和华的殿里供职。

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 23:1-32

ሌዋውያን

1ዳዊት በሸመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፣ ልጁን ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።

2እንዲሁም መላውን የእስራኤልን መሪዎች፣ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ። 3ዕድሜያቸው ሠላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺሕ ነበረ። 4ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ከእነዚህ መካከል ሃያ አራቱ ሺሕ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ይቈጣጠሩ፤ ስድስቱ ሺሕ ደግሞ ሹሞችና ዳኞች ይሁኑ፤ 5አራቱ ሺሕ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራቱ ሺሕ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያ እግዚአብሔርን ያመስግኑ”።

6ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀዓትና በሜራሪ በየጐሣቸው መደባቸው።

ጌድሶናውያን

7ከጌድሶናውያን ወገን፤

ለአዳን፣ ሰሜኢ።

8የለአዳን ወንዶች ልጆች፤

የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዮኤል፤ በአጠቃላይ ሦስት ናቸው።

9የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤

ሰሎሚት፣ ሐዝኤል፣ ሐራን፤ በአጠቃላይ ሦስት ናቸው።

እነዚህ የለአዳን ቤተ ሰብ አለቆች ናቸው።

10የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤

ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፤

እነዚህ አራቱ የሰሜኢ ልጆች ናቸው።

11የመጀመሪያው ኢኢት፣ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛ23፥11 አንድ የዕብራይስጥ ቅጅ፣ የሰብዓ ሊቃናትና የቩልጌት ትርጕሞች (እንዲሁም ቍጥር 11 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ዚና ይላሉ። ነበረ፤ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ የተቈጠሩት በሥራ መደብ እንደ አንድ ቤተ ሰብ ሆነው ነው።

ቀዓታውያን

12የቀዓት ወንዶች ልጆች፤

እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፤ በአጠቃላይ አራት ናቸው።

13የእንበረም ወንዶች ልጆች፤

አሮን፣ ሙሴ።

አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀድሱ፣ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባርኩ ተለዩ። 14የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቈጠሩ።

15የሙሴ ወንዶች ልጆች፤

ጌርሳም፣ አልዓዛር።

16የጌርሳም ዘሮች፤

ሱባኤል።

17የአልዓዛር ዘሮች፤

የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ።

አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የረዓብያ ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ።

18የይስዓር ወንዶች ልጆች፤

የመጀመሪያው ሰሎሚት ነበረ።

19የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤

የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቅምዓም ነበሩ።

20የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤

የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።

ሜራሪያውያን

21የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤

ሞሖሊ፣ ሙሲ።

የሞሖሊ ወንዶች ልጆች፤

አልዓዛርና ቂስ ነበሩ።

22አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቧቸው።

23የሙሲ ወንዶች ልጆች፤

ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ለኢያሪሙት በአጠቃላይ ሦስት ናቸው።

24እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜያቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ። 25ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቷል፤ በኢየሩሳሌምም ለዘላለም ለመኖር መጥቷል፤ 26ሌዋውያን ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኑን ወይም የመገልገያ ዕቃውን ሁሉ መሸከም የለባቸውም።” 27ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት የተቈጠሩት ሌዋውያን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ ነበረ።

28የሌዋውያኑ ተግባር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት የአሮንን ዘሮች መርዳት፣ የቤተ መቅደሱን ቅጥር ግቢና ክፍሎች መንከባከብ፣ የተቀደሱ ዕቃዎችን ሁሉ ማንጻትና በእግዚአብሔር ቤት ያሉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናወን ነበር። 29እንዲሁም መባ ሆኖ የሚቀርበውን ገጸ ኅብስት፣ የእህል ቍርባኑን ዱቄት፣ ያለ እርሾ የሚጋገረውን ቂጣ የሚጋግሩ፣ የሚያቦኩና የሚሰፈረውንም ሆነ የሚለካውን ሁሉ በኀላፊነት የሚቈጣጠሩ እነርሱ ነበሩ። 30በየዕለቱም እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለመወደስ ጧት ጧት ይቆሙ ነበር፤ ይህንም ማታ ማታ 31እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በወር መባቻ በዓልና በተደነገጉት በዓላት ሁሉ፣ የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሚቀርብበት ጊዜ ይፈጽሙ ነበር፤ በተወሰነላቸው ቍጥርና በተሰጠውም መመሪያ መሠረት፣ ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ያገለግሉ ነበር።

32ስለዚህ ሌዋውያኑ ለመገናኛው ድንኳንና ለመቅደሱ እንዲሁም በወንድሞቻቸው በአሮን ዘሮች ሥር ሆነው ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያለባቸውን ኀላፊነት ያከናውኑ ነበር።