利未记 18 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

利未记 18:1-30

禁止淫乱的条例

1耶和华对摩西说: 2“你把以下条例告诉以色列人。

“我是你们的上帝耶和华。 3你们曾经住在埃及,但不可效法埃及人的行为。我要把你们带到迦南,但你们不可效法迦南人的行为,不可随从他们的风俗。 4你们必须遵行我的典章,持守我的律例。我是你们的上帝耶和华。 5你们要遵守我的典章和律例。遵行的人必存活。我是耶和华。

6“你们任何人不可与近亲乱伦。我是耶和华。 7不可与你母亲乱伦而羞辱你父亲。她是你的母亲,不可与她乱伦。 8不可与你父亲的妻妾乱伦,那会羞辱你的父亲。 9不可与你的姊妹乱伦。不论是同父异母的,还是同母异父的,成长在同一家庭,还是不同家庭,都不可与她乱伦。 10不可与孙女或外孙女乱伦,那会自取羞辱。 11不可与你父亲妻妾的女儿乱伦。她是你的姊妹,不可与她乱伦。 12不可与姑母乱伦,她是你父亲的亲人。 13不可与姨母乱伦,她是你母亲的亲人。 14不可与伯母或婶母乱伦而羞辱你伯父或叔父。 15不可与儿媳乱伦。她是你儿子的妻子,不可与她乱伦。 16不可与兄嫂或弟媳乱伦,她是你兄弟的妻子。

17“不可与一个女人性交,又与她女儿性交,也不可与她孙女或外孙女性交。她们是她的近亲。这都是邪恶行为。 18妻子还在世时,不可娶她的姊妹,与她的姊妹性交,使她们彼此作对。 19女人在月经期间不洁净,不可与她性交。 20不可与邻居的妻子性交,那会玷污自己。 21不可把儿女当作祭物献给假神摩洛,不可亵渎你上帝的名。我是耶和华。 22男人不可与男人性交,像和女人一样,这是可憎的。 23不可与兽类交合,玷污自己。女人也不可与兽类交合。这是变态行为。

24“你们不可做这些事玷污自己。因为我要在你们面前赶走的各国正是因为这些行为而玷污了自己。 25他们居住的土地也都被玷污了,所以我因他们的罪恶而惩罚那片土地,我要使那片土地吐出他们。 26你们必须遵守我的律例和典章。不论你们还是寄居在你们中间的外族人,都不可做这些可憎之事。 27因为在你们之前居住在那里的人做了这些可憎之事,玷污了那片土地。 28如果你们玷污了那片土地,它也会像吐出从前的居民一样把你们吐出去。 29凡做这些可憎之事的,要将他从民中铲除。 30你们要遵守我的命令,不要效法那片土地上居民的恶俗,以致玷污自己。我是你们的上帝耶和华。”

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 18:1-30

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) አምላካችሁ (ኤሎሂም) ነኝ፤ 3በኖራችሁበት በግብፅ እነርሱ እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነዓን እንደሚያደርጉትም አታድርጉ፤ ልማዳቸውንም አትከተሉ። 4ሕጌን ታዘዙ፤ ሥርዐቴንም በጥንቃቄ ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ። 5ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ እነዚህን የሚጠብቅ በሕይወት ይኖርባቸዋልና፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

6“ ‘ማንም ሰው ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ወደ ማንኛውም የሥጋ ዘመዱ አይቅረብ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

7“ ‘ከእናትህ ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም አባትህን አታዋርድ፤ እናትህ ናት፤ ከእርሷ ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ።

8“ ‘ከአባትህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ አባትህን ያዋርዳል።

9“ ‘ከእኅትህ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፣ ከአባትህ ወይም ከእናትህ ሴት ልጅ ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ።

10“ ‘ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ አንተን ያዋርዳል።

11“ ‘የአባትህ ሚስት፣ ለአባትህ ከወለደቻት ሴት ልጅ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እኅትህ ናት።

12“ ‘ከአባትህ እኅት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እርሷ የአባትህ የሥጋ ዘመድ ናት።

13“ ‘ከእናትህ እኅት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እርሷ የእናትህ የሥጋ ዘመድ ናትና።

14“ ‘ከአባትህ ወንድም ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም፣ የአባትህን ወንድም አታዋርድ፤ እርሷ አክስትህ ናት።

15“ ‘ከምራትህ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ የልጅህ ሚስት ናት፤ ከእርሷም ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ።

16“ ‘ከወንድምህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ ወንድምህን ያዋርዳል።

17“ ‘ከእናቲቱና ከሴት ልጇ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እነርሱ የሥጋ ዘመዶቿ ናቸው፤ ይህም ጸያፍ ነው።

18“ ‘ሚስትህ በሕይወት እያለች እኅቷን ጣውንት አድርገህ አታግባት፤ ከእርሷም ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም።

19“ ‘በወር አበባዋ ርኩሰት ጊዜ ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ወደ ሴት አትቅረብ።

20“ ‘ከባልንጀራህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም፣ ራስህን በእርሷ አታርክስ።

21“ ‘ከልጆችህ ማንኛውንም ለሞሎክ እንዲሠዋ18፥21 ወይም በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አሳልፈህ አትስጥ፤ የአምላክህንም (ኤሎሂም) ስም አታርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

22“ ‘ከሴት ጋር እንደሚደረገው ሁሉ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ይህ አስጸያፊ ነው።

23“ ‘ከእንስሳ ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም ራስህን አታርክስ። ሴትም ከእንስሳ ጋር ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ራሷን አታቅርብ፤ ይህ አስጸያፊ ምግባር ነው።

24“ ‘ከእነዚህ በአንዱ እንኳ ራሳችሁን አታርክሱ፤ ከፊታችሁ የማሳድዳቸው አሕዛብ በእነዚህ ሁሉ ረክሰዋልና። 25ምድሪቱም ሳትቀር ረከሰች፤ እኔም ስለ ኀጢአቷ ቀጣኋት፤ ስለዚህ የሚኖሩባትን ሰዎች ተፋቻቸው። 26እናንተ ግን ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ እናንተ የአገር ተወላጆችና በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም አትፈጽሙ። 27ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ስለ ፈጸሙ፣ ምድሪቱ ረክሳለች። 28እናንተም ምድሪቱን ብታረክሷት፣ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ እንደ ተፋች እንዲሁ እናንተንም ትተፋችኋለች።

29“ ‘ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም የሚፈጽም ሰው ሁሉ ከወገኑ ተለይቶ ይጥፋ። 30ትእዛዜን ጠብቁ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች ካደረጓቸው አስጸያፊ ድርጊቶች አንዱንም አትፈጽሙ፤ በእነዚህም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።’ ”