创世记 23 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

创世记 23:1-20

亚伯拉罕买地葬撒拉

1撒拉享年一百二十七岁, 2迦南境内的基列·亚巴,即希伯仑去世。亚伯拉罕在那里痛哭,哀悼她。 3他从妻子尸体旁边站起来对人说: 4“我是寄居在你们这里的异乡人,请你们给我一块地,我好埋葬我的亡妻。” 5人回答说: 6“我主,请听我们说,你在我们中间是一位尊贵的王子,你可以选我们这里最好的坟地,没有人会反对你使用他的坟地埋葬你的妻子。” 7亚伯拉罕就向他们下拜,说: 8“如果你们真的准我安葬妻子,就请你们代我求琐辖的儿子以弗仑9请他当着你们的面,把他田地尽头的麦比拉洞按实价卖给我作坟地。”

10当时以弗仑正坐在人当中,于是他在城门口人聚集的地方当众答复亚伯拉罕说: 11“不可!我主,请听我说,我当着族人的面,把那块地和山洞送给你,你只管去安葬你的妻子!” 12亚伯拉罕向当地的人下拜, 13当众对以弗仑说:“你若愿意,请听我说,我要把地钱给你,请你收下,好让我安葬我的妻子。” 14以弗仑回答说: 15“我主,请听我说,四公斤半银子的地对你我来说算什么呢?去安葬你的妻子吧!” 16于是,亚伯拉罕就照以弗仑当众提出的价钱,按通用的重量单位秤了四公斤半银子给他。

17这样,以弗仑麦比拉、靠近幔利的那块地和山洞及地界内所有的树木, 18都归了亚伯拉罕。这是在城门口的人面前买下的。

19之后,亚伯拉罕把妻子撒拉安葬在迦南幔利附近、麦比拉田间的洞里。幔利就是希伯仑20这块人的地和其中的山洞从此成了亚伯拉罕家的坟地。

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 23:1-20

የሣራ ሞት

1ሣራ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ኖረች፤ 2በከነዓን ምድር፣ በቂርያት አርባቅ ማለትም በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያለቅስና ሊያዝን መጣ።

3ከዚያም አብርሃም ከተቀመጠበት ከሚስቱ ሬሳ አጠገብ ተነሣ፤ ኬጢያውያንንም23፥3 ወይም የኬጢ ልጆች፤ 5፡7፡10፡16፡18 እና 20 እንዲሁ እንዲህ አላቸው፤ 4“እኔ ለአገሩ እንግዳ፣ ለሰዉ ባዳ ሆኜ በመካከላችሁ የምኖር ነኝና ለመቃብር የምትሆን ቦታ ሽጡልኝ፤ የሚስቴንም ሬሳ ልቅበርበት።”

5ኬጢያውያንም ለአብርሃም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ 6“ስማን ጌታዬ፤ አንተ እኮ በእኛ ዘንድ እንደ ኀያል መስፍን ነህ፤ ከመቃብር ቦታችን በመረጥኸው ስፍራ ሬሳህን መቅበር ትችላለህ፤ ማናችንም ብንሆን የሞተብህን ሰው እንዳትቀብርበት የመቃብር ቦታችንን አንከለክልህም።”

7ከዚያም አብርሃም ተነሥቶ የአገሬውን ሕዝብ፣ ኬጢያውያንን እጅ ነሣ፤ 8እንዲህም አላቸው፤ “እንድቀብር ከፈቀዳችሁልኝ፣ አንዴ ስሙኝና የሰዓርን ልጅ ኤፍሮንን ስለ እኔ ሆናችሁ ለምኑልኝ። 9ይኸውም በዕርሻው ድንበር ላይ ያለችውን መክፈላ የተባለችውን ዋሻውን እንዲሸጥልኝ ነው፤ በመካከላችሁም የመቃብር ቦታ እንድትሆነኝ በሙሉ ዋጋ እንዲሸጥልኝ ለምኑልኝ።”

10ኬጢያዊው ኤፍሮንም እዚያው መካከላቸው ተቀምጦ ስለ ነበር፣ ወደ ከተማው በር መግቢያ መጥተው የተሰበሰቡት ኬጢያውያን በሙሉ እየሰሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ 11“እንዲህ አይደለም ጌታዬ፤ አድምጠኝ፤ ዕርሻውን በውስጡ ካለው ዋሻ ጋር ውሰደው። እነሆ፤ በወገኖቼ ኬጢያውያን ፊት ሰጥቼሃለሁ፤23፥11 ወይም ሸጬልሃለሁ ሬሳህን ቅበርበት።”

12አብርሃም እንደ ገና የአገሬውን ሕዝብ እጅ ነሣና 13ሁሉም እየሰሙት፣ “የዕርሻውን ቦታ ዋጋ ልክፈል፤ እባክህን ተቀበለኝና ሬሳዬን ልቅበርበት” አለው።

14ኤፍሮንም ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ 15“ጌታዬ ስማኝ፤ የመሬቱ ዋጋማ አራት መቶ ጥሬ ብር23፥15 4.5 ኪሎ ግራም ገደማ ይሆናል ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በአንተ መካከል ምን ቁም ነገር አለው? ይልቅስ ሬሳህን ቅበርበት” አለው።

16አብርሃምም፣ ኤፍሮን በኬጢያውያን ፊት በተናገረው ዋጋ ተስማማ፤ በወቅቱም የንግድ መለኪያ መሠረት አራት መቶ ጥሬ ብር መዘነለት።

17በዚህ ሁኔታ፣ በመምሬ አጠገብ በመክፈላ ያለው የኤፍሮን ዕርሻ ቦታ ከነዋሻው በክልሉ ካሉት ዛፎች ሁሉ ጭምር ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈ፤ 18ወደ ከተማው በር በመጡት ኬጢያውያንም ሁሉ ፊት የአብርሃም ንብረት መሆኑም ተረጋገጠለት። 19ከዚህም በኋላ አብርሃም በከነዓን ምድር፣ በመምሬ አጠገብ፣ መክፈላ በተባለች ዕርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ የሚስቱን የሣራን ሬሳ ቀበረ፤ ይህችም ኬብሮን ናት። 20ስለዚህ ዕርሻውና ውስጡ የሚገኘው ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከኬጢያውያን ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈለት።