出埃及记 40 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

出埃及记 40:1-38

支起会幕

1耶和华对摩西说: 2“你要在一月一日支起圣幕,即会幕, 3把约柜安置在里面,用幔子遮掩。 4把桌子搬进去,摆好桌上的器具,再把灯台搬进去,点上灯, 5把烧香的金坛放在约柜前面,挂上圣幕入口的帘子。 6要把燔祭坛放在圣幕前面, 7洗濯盆放在会幕和祭坛中间,盆里要有水。 8用帷幔在圣幕四周围成院子,在院子的入口挂上帘子。 9你要用膏油抹圣幕和里面所有的器具,使它们分别出来,成为圣洁之物。 10要抹燔祭坛和坛上所有器具,使燔祭坛分别出来,成为至圣之物。 11要抹洗濯盆和盆座,使它们分别出来,成为圣洁之物。 12要把亚伦父子们叫到会幕入口,用水为他们沐浴, 13亚伦穿上圣衣后膏立他,使他分别出来,做圣洁的祭司事奉我。 14也要把他的儿子们叫来,给他们穿上内袍, 15用同样的仪式膏立他们,使他们做祭司事奉我。他们的受膏将使他们永远做祭司,世代相传。”

16摩西照耶和华的吩咐把事情都办好了。 17第二年一月一日,圣幕支起来了。 18摩西支起圣幕,装上带凹槽的底座,竖起木板,插上横闩,立起柱子, 19在圣幕上面搭起罩棚,铺上顶盖,都遵照耶和华的吩咐。 20他把约版放在约柜里,横杠穿在约柜的两旁,施恩座放在约柜上, 21把约柜抬进圣幕,挂起幔子遮掩约柜,都遵照耶和华的吩咐。 22他把桌子放在会幕内、遮掩约柜的幔子外面、圣幕的北侧, 23将献给耶和华的供饼放在桌上,都遵照耶和华的吩咐。 24他把灯台放在会幕内的桌子对面,在圣幕的南侧, 25然后在耶和华面前点灯,都遵照耶和华的吩咐。 26他把金香坛放在会幕里、遮掩约柜的幔子前面, 27在坛上点燃芬芳的香,都遵照耶和华的吩咐。 28他挂上圣幕入口的帘子, 29在会幕,即圣幕入口的前面设立燔祭坛,在坛上献燔祭和素祭,都遵照耶和华的吩咐。 30他把洗濯盆放在会幕和祭坛之间,盆里盛水,供洗濯用。 31摩西亚伦及其众子都在那里清洗手脚, 32他们进会幕或走近祭坛的时候,都要先清洗,都遵照耶和华的吩咐。 33摩西又在圣幕和祭坛的四周用帷幔围成院子,然后在院子入口挂上帘子。这样,摩西完成了工作。

耶和华的荣光

34那时,有云彩遮盖会幕,耶和华的荣光充满了圣幕。 35摩西不能进会幕,因为云彩停在上面,耶和华的荣光充满了圣幕。 36一路上,云彩从圣幕升起,他们就出发。 37云彩不升起,他们就不出发,一直等到云彩升起。 38一路上,白天有耶和华的云彩停留在圣幕上面,夜间云中有火光为以色列百姓照明。

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 40:1-38

የማደሪያውን ድንኳን መትከል

1ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አለው፤ 2“ማደሪያውን ይኸውም የመገናኛውን ድንኳን በወሩ የመጀመሪያ ቀን ትከለው፤ 3የምስክሩን ታቦት በውስጡ አኑር፤ ታቦቱንም በመጋረጃው ጋርደው። 4ጠረጴዛውንም ወደ ውስጥ አምጥተህ ዕቃዎቹን በላዩ ላይ አሰናዳ፤ ከዚያም መቅረዙን አስገብተህ መብራቶቹን በቦታቸው አስቀምጥ። 5የዕጣኑን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት አስቀምጠው፤ ከማደሪያውም መግቢያ ላይ መጋረጃውን አድርግ።

6“የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን በማደሪያው መግቢያ ፊት ለፊት፣ በመገናኛው ድንኳን አስቀምጠው። 7የመታጠቢያውን ሰን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አኑርበት፤ ውሃም አኑርበት። 8በዙሪያውም የአደባባዩን ቅጥር ትከል፤ መጋረጃውንም በአደባባዩ መግቢያ ላይ አድርገው።

9“ቅብዐ ዘይቱን ወስደህ ማደሪያውንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቅባ፤ እርሱንና ዕቃውን ሁሉ ቀድስ፤ የተቀደሰም ይሆናል። 10ከዚያም የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ቅባ፤ መሠዊያውን ቀድስ፣ እጅግም የተቀደሰ ይሆናል። 11የመታጠቢያው ሰንና ማስቀመጫውን ቅባ፤ ቀድሳቸውም።

12“አሮንና ወንዶች ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ አምጥተህ በውሃ ዕጠባቸው። 13ከዚያም አሮንን የተቀደሰውን ልብስ አልብሰው፤ ካህን ሆኖ ያገለግለኝ ዘንድ ቅባው፤ ቀድሰውም። 14ወንዶች ልጆቹን አምጥተህ ሸሚዝ አልብሳቸው። 15ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ ልክ አባታቸውን እንደ ቀባህ ቅባቸው፤ መቀባታቸውም በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ለሚቀጥል ክህነት ነው።” 16ሙሴ ሁሉንም ነገር ልክ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው አደረገ።

17እንዲሁም በሁለተኛው ዓመት፣ የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን የማደሪያው ድንኳን ተተከለ። 18ሙሴ የማደሪያውን ድንኳን በተከለ ጊዜ፣ መቆሚያዎቹን በቦታቸው አኖረ፤ ወጋግራዎቹን አቆመ፤ አግዳሚዎቹን አስገባ፤ ምሰሶዎቹንም ተከለ። 19ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው ድንኳኑን በማደሪያው ላይ፣ መደረቢያውንም በድንኳኑ ላይ ዘረጋው።

20ምስክሩን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጠው፤ መሎጊያዎቹንም ከታቦቱ ጋር አያያዛቸው፤ የስርየት መክደኛውንም በላዩ ላይ አደረገው። 21ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው ታቦቱን ወደ ማደሪያው ድንኳን አስገብቶ መከለያ መጋረጃውን ሰቀለ፤ የምስክሩንም ታቦት ጋረደው።

22ሙሴ ጠረጴዛውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣ ከማደሪያው በስተ ሰሜን ከመጋረጃው ውጭ አኖረው፤ 23እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘውም ኅብስቱን በላዩ ላይ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አኖረ።

24መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከጠረጴዛው ትይዩ ከማደሪያው ድንኳን በስተ ደቡብ በኩል አኖረው፤ 25እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘውም መብራቶቹን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አበራ።

26ሙሴ የወርቅ መሠዊያውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ፊት ለፊት አኖረው፤ 27እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘውም መልካም መዐዛ ያለውን ዕጣን አጠነበት። 28ከዚያም መጋረጃውን በማደሪያው ድንኳን መግቢያ ላይ ሰቀለው።

29የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ አኖረው፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘውም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን መሥዋዕት በላዩ ላይ አቀረበ።

30የመታጠቢያውን ሰን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀመጠ፤ ለመታጠቢያም ውሃ አደረገበት፤ 31ሙሴና አሮን፣ ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡበት ነበር። 32እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው ወደ መገናኛው ድንኳን በገቡና ወደ መሠዊያው በቀረቡ ቍጥር ይታጠቡ ነበር።

33ከዚያም ሙሴ በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ አደባባዩን ተከለ፤ በአደባባዩም መግቢያ ላይ መጋረጃውን ሰቀለ፤ እንደዚህ አድርጎ ሙሴ ሥራውን ፈጸመ።

የእግዚአብሔር ክብር

34ከዚያም ደመናው የመገናኛውን ድንኳን ሸፈነ፤ የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ክብር ማደሪያውን ሞላ። 35ደመናው በላዩ ላይ ስለ ነበረና የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ክብር ማደሪያውን ስለ ሞላው፣ ሙሴ ወደ መገናኛው ድንኳን መግባት አልቻለም።

36በእስራኤላውያን ጕዞ ሁሉ ደመናው ከማደሪያው ላይ በተነሣ ጊዜ፣ ይጓዙ ነበር፤ 37ደመናው ካልተነሣ ግን፣ እስከሚነሣበት ቀን ድረስ አይጓዙም ነበር። 38ስለዚህ በጕዟቸው ሁሉ ወቅት፣ በእስራኤል ቤት ፊት ሁሉ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ደመና በቀን ከማደሪያው በላይ፣ በሌሊትም እሳቱ በደመናው ውስጥ ነበር።