出埃及记 37 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

出埃及记 37:1-29

约柜

1比撒列用皂荚木造了一个柜,长一点一米,宽六十六厘米,高六十六厘米。 2这柜子里外都包上纯金,还镶了一圈金边。 3他造了四个金环,安在柜的四个脚上,每边两个环, 4又用皂荚木造了两根横杠,外面包上金, 5然后把横杠穿过柜旁的金环,便于抬柜。 6他用纯金造施恩座,长一点一米,宽六十六厘米。 7又在施恩座的两端用金子打造两个基路伯天使, 8这两个基路伯天使跟施恩座连在一起, 9在施恩座的两端,面对面朝向施恩座,向上展开翅膀遮盖施恩座。

桌子

10他用皂荚木造了一张桌子,长八十八厘米,宽四十四厘米,高六十六厘米。 11整张桌子都包上纯金,四周镶上金边。 12在桌子四周造一个八厘米宽的外框,上面也镶上金边。 13他又造四个金环,安在桌子四角的桌腿上, 14金环靠近外框,以便穿横杠抬桌子。 15他用皂荚木造两根横杠,外面包金,用来抬桌子。 16又用纯金造桌子上的器具,就是盘、碟及献酒用的杯和瓶。

17他用纯金造了一座灯台,灯台的灯座、灯柱、油杯、花瓣和花苞都是用一块纯金打成的。 18灯台两边各伸出三个分枝,共有六个分枝。 19每个分枝都伸出三个杏花形状、有花瓣和花苞的油杯,六个分枝都是这样。 20灯台上有四个杏花形状、有花瓣和花苞的杯。 21灯台上每一对分枝的相连处有花苞,三对分枝都是这样。 22整座灯台,包括一切装饰,都是用一块纯金打成的。 23他又用纯金为这座灯台造了七个灯盏,以及灯剪和灯花盘。 24造整座灯台和灯台的器具共用了三十四公斤纯金。

造香坛

25他又用皂荚木造了一座方形的香坛,长宽各四十五厘米,高九十厘米,坛的四角与坛连成一体, 26坛顶、坛的四面和坛上的角状物包上纯金,四周镶上金边。 27他造了两个金环,安在坛两侧的金边下面, 28又用皂荚木造横杠,包上金,穿在两个环里,用来抬香坛。

29他又用调制香料的方法制作圣膏油和纯净芬芳的香。

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 37:1-29

የኪዳኑ ታቦት

37፥1-9 ተጓ ምብ – ዘፀ 25፥10-20

1ባስልኤል ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል37፥1 ከፍታው 1.1 ሜትር ወርዱና ርዝመቱ 0.7 ሜትር ያህል ማለት ነው።፣ ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር ዕንጨት ሠራ። 2በውስጥና በውጭ በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት። 3አራት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርቶ ሁለት ቀለበቶችን በአንድ በኩል፣ ሁለት ቀለበቶችንም በሌላ በኩል አድርጎ ከአራቱ እግሮቹ ጋር አያያዛቸው። 4ከዚያም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 5መሎጊያዎቹንም መሸከሚያ እንዲሆኑ በታቦቱ ጐንና ጐን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው።

6ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል37፥6 ርዝመቱ 1.1 ሜትር ወርዱ 1.1 ሜትር ያህል ማለት ነው።፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ከንጹሕ ወርቅ የስርየት መክደኛ ሠራ። 7ከዚያም ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሁለት ኪሩቤልን ከመክደኛው ጫፎች ላይ ሠራ። 8አንዱን ኪሩብ በአንዱ ጫፍ ላይ፣ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ጫፍ ላይ ሠራ፤ ከሁለቱ ጫፎች ላይ ከክዳኑ ጋር አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው፤ 9ኪሩቤልም የስርየት ክዳኑን በመሸፈን ክንፋቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ነበር፤ ኪሩቤል ወደ ስርየት መክደኛው እየተመለከቱ እርስ በርሳቸው ገጽ ለገጽ ነበሩ።

የኅብስት ማስቀመጫው ጠረጴዛ

37፥10-16 ተጓ ምብ – ዘፀ 25፥23-29

10ርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ከፍታውም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሠሩ37፥10 በዚህና በቍጥር 11-29 ባሉት ክፍሎች፣ ሥሩ11ከዚያም በንጹሕ ወርቅ በመለበጥ በዙሪያው የወርቅ ክፈፍ አበጁለት። 12በዙሪያውም ስፋቱ አንድ ስንዝር37፥12 ወደ 8 ሳንቲ ሜትር ያህል ማለት ነው። የሆነ ጠርዝ በማበጀት በጠርዙ ላይ የወርቅ ክፈፍ አደረጉበት። 13ለጠረጴዛው አራት የወርቅ ቀለበቶች አበጅተው አራቱ እግሮች ካሉበት ከአራቱ ማእዘኖች ጋር አያያዟቸው። 14ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች እንዲይዙ ቀለበቶቹ ከጠርዙ አጠገብ ሆኑ። 15ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች ከግራር ዕንጨት የተሠሩና በወርቅ የተለበጡ ነበሩ። 16የጠረጴዛውን ዕቃዎች ይኸውም ዝርግ ሳሕኖችን፣ ድስቶችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን እንዲሁም የመጠጥ መሥዋዕቱ ማፍሰሻ የሆኑትን ማንቈርቈሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠሯቸው።

መቅረዙ

37፥17-24 ተጓ ምብ – ዘፀ 25፥31-39

17መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩት፤ መቆሚያውንና ዘንጉን ቀጥቅጠው አበጁት፤ የአበባ ቅርጽ ያላቸው ጽዋዎች፣ እንቡጦችና የፈኩ አበቦች ከእርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ተሠርተው ነበር። 18ሦስቱ በአንድ በኩል ሦስቱ በሌላ በኩል በመሆን ስድስት ቅርንጫፎች ከመቅረዙ ጐኖች ተሠርተው ነበር። 19ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች በአንዱ ቅርንጫፍ ላይ፣ ሦስቱ ደግሞ በሚቀጥለው ቅርንጫፍ ላይ ነበሩ፤ ከመቅረዙ ለወጡት ለስድስቱም ቅርንጫፎች ሁሉ እንዲሁ ነበር። 20እንቡጦችና የፈኩ አበቦች ያሉባቸው የለውዝ አበባ የሚመስሉ አራት ጽዋዎች በመቅረዙ ላይ ነበሩ። 21አንደኛው እንቡጥ ከመቅረዙ ወጣ ብለው በሚገኙት በመጀመሪያው ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር፣ ሁለተኛውም እምቡጥ በሁለተኛው ጥንድ ሥር እንዲሁም ሦስተኛው እንቡጥ በሦስተኛው ጥንድ ሥር ነበር፤ በስድስቱም ቅርንጫፎች እንዲሁ ነበር። 22እንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ ተሠርተው ከመቅረዙ ጋር አንድ ወጥ ነበሩ።

23የመቅረዙን ሰባት መብራቶች፣ እንዲሁም መኰስተሪያዎችንና የኵስታሪ ማስቀመጫዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ። 24መቅረዙንና ዕቃዎቹን ሁሉ ከአንድ መክሊት37፥24 ወደ 34 ኪሎ ግራም ያህል ማለት ነው። ንጹሕ ወርቅ ሠሩ።

የዕጣን መሠዊያው

37፥25-28 ተጓ ምብ – ዘፀ 30፥1-5

25የዕጣን መሠዊያውን ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ ርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ከፍታው ሁለት ክንድ37፥25 ርዝመቱ ወርዱ 0.5 ሜትር ከፍታው 0.9 ሜትር ያህል ማለት ነው። ነበር፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ተሠርተው ነበር። 26ላዩን፣ ጐኖቹን ሁሉና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጧቸው፤ በዙሪያው የወርቅ ክፈፍ አበጁ። 27ለሸክም የሚሆኑትን መሎጊያዎች ለመያዝ ትይዩ የሆኑ ከክፈፉ ሥር ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠሩ። 28መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ በወርቅም ለበጧቸው።

29እንዲሁም የተቀደሰውን ቅብዐ ዘይትና የሽቶ ቀማሚ ሥራ የሆነውን፣ ንጹሕና መልካም መዐዛ ያለውን ዕጣን ሠሩ።