以西结书 33 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以西结书 33:1-33

耶和华立以西结为守望者

1耶和华对我说: 2“人子啊,你要告诉你的同胞,‘我若使战争降临某地,那地方的百姓就应选一人做守望者。 3守望者发现敌人来攻打,便吹号警告百姓。 4凡听见号声而不接受警告的,敌人来把他杀了,这流血的罪就要由他自己承担。 5因为他听见号声,却不接受警告,他的死是咎由自取。他若接受警告,就不至于死了。 6但如果守望者看见敌人来攻打而不吹号警告百姓,以致有人被敌人杀了,那人固然是因自己的罪恶而被杀,我却要向这守望者追讨那人被杀的血债。’

7“人子啊,现在我立你为以色列人的守望者,你要听我的信息,代我警告他们。 8如果我说恶人必定要死,你却不警告他离开罪恶的行径,他必因自己的罪而死,我却要向你追讨他丧命的血债。 9如果你警告恶人离开罪恶的行径,他却不听,他必因自己的罪恶而死,他的死与你无关。

10“人子啊,你要对以色列人说,‘你们说,我们背负过犯和罪恶,正因此而灭亡。我们怎能存活下去呢? 11你要告诉他们,主耶和华说,“我凭我的永恒起誓,我绝不喜欢恶人死亡,我更愿意恶人改邪归正,得以存活。以色列人啊,回头吧!回头吧!改邪归正吧!何必自取灭亡呢?”’ 12人子啊,你要对你的同胞说,‘当义人犯罪时,他以往的义救不了他;当恶人悔改时,他以往的恶不会使他灭没。义人若犯罪,他以往的义不能使他存活。’ 13我虽对义人说他必能存活,但如果他仗着自己的义而犯罪,他的义将不会被记念,他必因犯罪而死亡。 14我虽对恶人说他必定要死,但他若改邪归正,行事公正仁义, 15偿还抵押,归还赃物,遵行生命之律例,不再犯罪,就必存活,不致死亡。 16他犯的罪不会被追究,因为他行事公正仁义,所以必得存活。

17“你的同胞却说,主这样做不公平。其实是他们自己行事不公。 18义人离义行恶,必因恶行而死亡。 19恶人弃恶行义,必因义行而存活。 20可是你们却说,主这样做不公平。以色列人啊,我必按你们各人的行为审判你们。”

21在我们被掳后第十二年十月五日,有人从耶路撒冷逃出来对我说:“城已经沦陷了。” 22逃难的人来的前一晚,耶和华的灵降在我身上,开了我的口。当那人早上来到我这里时,我就开了口,不再沉默。

23耶和华对我说: 24“人子啊,那些住在以色列废墟中的人说,‘亚伯拉罕一人尚且能拥有这片土地,我们这么多人更能拥有这片土地为业。’ 25但你要告诉他们,主耶和华这样说,‘你们吃带血的肉,仰赖偶像,又杀人流血,怎能拥有这片土地呢? 26你们靠刀剑行可憎之事,个个玷污别人的妻子,你们怎能拥有这片土地呢?’ 27你要告诉他们,主耶和华这样说,‘我凭我的永恒起誓,那些住在废墟中的必死于刀下,逃到田野的必被野兽吞吃,躲进堡垒和洞穴的必死于瘟疫。 28我要使这片土地荒凉不堪,使她所夸耀的势力消逝。以色列的山必荒凉,杳无人迹。 29因为他们所行的一切可憎之事,我必使这地方荒凉不堪,那时他们就知道我是耶和华。’

30“人子啊,你的同胞在墙边和门口彼此议论你说,‘来,听听耶和华要他传什么信息。’ 31他们随着人群来到你面前,坐着聆听你的话,俨然像我的子民。但他们不付诸实行,嘴里说的是甜言蜜语,心中却追求不义之财。 32他们只听不做,你在他们眼中只不过是善唱情歌、长于弹奏乐器的人。 33看吧,我所说的必定应验。当一切应验的时候,他们就知道有先知在他们当中。”

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 33:1-33

ሕዝቅኤል ጕበኛው

1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለአገርህ ሰዎች ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘በምድር ላይ ሰይፍን ሳመጣ፣ የምድሪቱ ሕዝብ ከሰዎቻቸው አንዱን መርጠው ጕበኛ ቢያደርጉት፣ 3እርሱም በምድሪቱ ላይ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ፣ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ መለከት ቢነፋ፣ 4ከዚያም ማንም መለከቱን ሰምቶ ባይጠነቀቅ፣ ሰይፍም መጥቶ ሕይወቱን ቢያጠፋ፣ ደሙ በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል። 5የመለከቱን ድምፅ ሰምቶ ባለመጠንቀቁ፣ ደሙ በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል፤ ቢጠነቀቅ ኖሮ ግን ራሱን ባዳነ ነበር። 6ነገር ግን ጕበኛ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ፣ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ መለከት ሳይነፋ ቢቀርና ከመካከላቸው የአንዱን ሰው ሕይወት ሰይፍ ቢያጠፋ፣ ያ ሰው ስለ ኀጢአቱ ይወሰዳል፤ ጕበኛውን ግን ስለ ሰውየው ደም ተጠያቂ አደርገዋለሁ።’

7“የሰው ልጅ ሆይ፤ አንተን ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፤ ስለዚህ የምናገረውን ቃል ስማ፤ ማስጠንቀቂያዬንም ስጣቸው። 8ክፉውን፣ ‘አንተ ክፉ ሰው፤ በርግጥ ትሞታለህ’ ባልሁት ጊዜ፣ እርሱን ከመንገዱ እንዲመለስ ባታደርገው፣ ያ ክፉ ሰው በኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ስለ ደሙ ተጠያቂ ትሆናለህ። 9ነገር ግን ክፉውን ሰው ከመንገዱ እንዲመለስ ነግረኸው እሺ ባይል፣ እርሱ ስለ ኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ራስህን አድነሃል።

10“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፤ ‘እንዲህ ትላላችሁ፤ “በደላችንና ኀጢአታችን ከብዶናል፤ ከዚህም33፥10 ወይም በእርሱ የተነሣ ልንጠፋ ነው፤ ታዲያ እንዴት መኖር እንችላለን?” ’ 11እንዲህ በላቸው፤ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዳቸው ተመልሰው በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ በክፉዎች ሞት ደስ አልሰኝም። ተመለሱ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለምን ትሞታላችሁ?’

12“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ፤ ለአገርህ ሰዎች እንዲህ በላቸው፤ ‘ጻድቅ ሰው ትእዛዝን በተላለፈ ጊዜ የቀድሞ ጽድቁ አያድነውም፤ ኀጢአተኛ ሰው ከኀጢአቱ ከተመለሰ፣ ከቀድሞ ክፋቱ የተነሣ አይጠፋም። ጻድቅ ሰው ኀጢአት ቢሠራ፣ በቀድሞ ጽድቁ ምክንያት በሕይወት እንዲኖር አይደረግም።’ 13ጻድቁን ሰው በርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ብለው፣ እርሱም ጽድቁን ተማምኖ ክፋት ቢሠራ፣ ከጽድቅ ሥራው አንዱም አይታሰብለትም፤ በኀጢአቱም ምክንያት ይሞታል። 14እንዲሁም ክፉውን ሰው፣ ‘በርግጥ ትሞታለህ’ ብለው፣ እርሱም ከኀጢአቱ ተመልሶ ቀና የሆነውንና ትክክለኛውንም ነገር ቢያደርግ፣ 15ለሰጠው ብድር የተቀበለውን መያዣ ቢመልስ፣ የሰረቀውንም መልሶ ቢሰጥ፣ ሕይወት የሚሰጡትን ትእዛዞች ቢከተል፣ ክፉ ነገርንም ባያደርግ፣ በርግጥ እርሱ በሕይወት ይኖራል፤ አይሞትምም። 16ከሠራው ኀጢአት አንዱም አይታሰብበትም፤ ቀናውንና ትክክለኛውን አድርጓልና፤ በርግጥ በሕይወት ይኖራል።

17“ይህም ሆኖ የአገርህ ሰዎች፣ ‘የጌታ መንገድ ቀና አይደለችም’ ይላሉ፤ ቀና ያልሆነው ግን የእነርሱ መንገድ ነው። 18ጻድቅ ሰው የጽድቁን ሥራ ትቶ ክፉ ነገር ቢያደርግ፣ ስለ ኀጢአቱ ይሞታል። 19ክፉም ሰው ከክፉ ሥራው ተመልሶ ቀናውንና ትክክለኛውን ነገር ቢያደርግ፣ ይህን በማድረጉ በሕይወት ይኖራል። 20ይሁን እንጂ የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ‘የጌታ መንገድ ቀና አይደለችም’ ትላላችሁ፤ ነገር ግን በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደ መንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ።”

የኢየሩሳሌም መውደቅ

21በተማረክን በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፣ በዐሥረኛው ወር፣ በአምስተኛው ቀን፣ ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፣ “ከተማዪቱ ወደቀች!” አለኝ። 22ሰውየው ከመድረሱ በፊት በነበረው ምሽት፣ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ላይ ነበረች፤ በማለዳም ሰውየው ወደ እኔ ከመምጣቱ በፊት እግዚአብሔር አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ፤ ከዚያ በኋላ ዝም አላልሁም።

23ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 24“የሰው ልጅ ሆይ፤ በእስራኤል ምድር በፍርስራሾች ውስጥ የሚኖሩት ሕዝቦች፣ ‘አብርሃም አንድ ራሱን ብቻ ነበር፤ ያም ሆኖ ምድሪቱን ወረሰ፤ እኛ ግን ብዙዎች ነን፤ በርግጥ ምድሪቱ ርስት ሆና ተሰጥታናለች’ ይላሉ። 25ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ዐይኖቻችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምም ታፈስሳላችሁ፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን ልትወርሱ ታስባላችሁ? 26በሰይፋችሁ ትመካላችሁ፤ አስጸያፊ ነገሮችን ትፈጽማላችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የባልንጀራችሁን ሚስት ታረክሳላችሁ፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል?’

27“እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ በፍርስራሾች ውስጥ የተረፉት በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በገጠር ያሉትን ቦጫጭቀው እንዲበሏቸው ለዱር አራዊት እሰጣቸዋለሁ፤ በምሽግና በዋሻ ያሉትም በቸነፈር ይሞታሉ። 28ምድሪቱን ጠፍና ባድማ አደርጋታለሁ፤ የምትመካበት ጕልበቷ እንዳልነበረ ይሆናል፤ የእስራኤልም ተራሮች ማንም እንዳያልፍባቸው ባድማ ይሆናሉ። 29ካደረጓቸው አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሣ፤ ምድሪቱን ጠፍና ባድማ በማደርግበት ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’

30“አንተን በሚመለከት፣ የሰው ልጅ ሆይ፤ የአገርህ ሰዎች በየቤቱ በርና ግድግዳ ሥር ሆነው ስለ አንተ ይነጋገራሉ፤ እርስ በራሳቸውም እንዲህ ይባባላሉ፤ ‘ኑና ከእግዚአብሔር የመጣውን መልእክት እንስማ።’ 31ሁልጊዜ እንደሚያደርጉት ሕዝቤ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ቃልህንም ለመስማት ከፊትህ ይቀመጣሉ፤ ነገር ግን አይፈጽሙትም። በከንፈራቸው ብዙ ፍቅርን ይገልጣሉ፤ ልባቸው ያረፈው ግን ተገቢ ባልሆነ ጥቅም ላይ ነው። 32ቃልህን ሰምተው ሥራ ላይ የማያውሉት በመሆናቸው፣ አንተ ለእነርሱ በአማረ ድምፅ የፍቅር ዘፈን የሚዘፍን፣ በዜማ መሣሪያም አሳምሮ የሚጫወት ሙዚቀኛ ሆነህላቸዋል።

33“ይህ ሁሉ ሲሆን፣ ደግሞም በርግጥ ይሆናል፣ በመካከላቸው ነቢይ እንደ ነበረ፣ ያውቃሉ።”