以西结书 31 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以西结书 31:1-18

香柏树的比喻

1第十一年三月一日,耶和华对我说: 2“人子啊,你要对埃及王法老和他的百姓说,

“‘谁能比你强大呢?

3看啊,亚述曾是黎巴嫩的一棵香柏树,

枝繁叶茂,遮天蔽日,

高耸入云。

4它在河流和深泉的滋润下茁壮成长,

溪流四围环绕它,

浇灌着林间的树木。

5充足的水源使它高过田间所有的树木,

枝子长得又粗又长。

6空中的飞鸟都在它的枝头上搭窝,

田间的野兽都在它的树荫下生产,

所有的大国都住在它的荫下。

7它高大美丽,枝干修长,

因为树根深入水源,

8连上帝园中的香柏树也不能与它相比。

松树不能与它的枝干相比,

枫树不能与它的枝条相比,

主耶和华园中的树木没有一棵能与它媲美。

9我使它枝繁叶茂,美丽无比,

以致上帝伊甸园里的树木都羡慕它。’

10“因此,主耶和华说,‘因为它树干高大,树梢高耸入云,心高气傲, 11我要把它交在列国的首领手里,他必按照它的邪恶惩治它。我丢弃了它。 12外族人,就是列邦中最残暴的人要把它砍倒,丢弃在那里,它折断的枝干散落在山间和河谷中。世上各族都离开它的荫下, 13天上的飞禽要栖身在那折断的树干上,地上的走兽要躺卧在它的枝条中。 14故此,水边的树木都不再傲然矗立,高耸入云,水源充足的大树也不再如此高大,因为它们都注定要与下坟墓的人一同死亡,落到阴间的深处。’

15“主耶和华说,‘它下到阴间的那天,我要使哀声响起,使深渊闭塞,江河止息,洪水停滞。我要使黎巴嫩为它哀哭,田野的树木因它而枯萎。 16我将它与下坟墓的人一同抛到阴间时,列国听见它坠落的响声,都恐惧战抖。伊甸园中的树木和黎巴嫩水源充足、上好的树木都在阴间得到安慰。 17在它荫庇下做它爪牙的盟友都与它一同落到阴间,到被杀的人那里。

18“‘伊甸园的树木中,谁能与你的威荣相比呢?然而你却要与伊甸园的树木一同下到阴间,躺卧在未受割礼的人当中,与被杀的人在一起。

“‘这就是法老和他百姓的结局。这是主耶和华说的。’”

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 31:1-18

የሊባኖስ ዝግባ

1በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖንና ስፍር ቍጥር ለሌለው ሕዝቡ እንዲህ በል፤

“ ‘በክብር ከአንተ ጋር ማን ሊወዳደር ይችላል?

3ለጫካው ጥላ የሆኑ የሚያማምሩ ቅርንጫፎች የነበሩትን፣

እጅግ መለሎ ሆኖ፣

ጫፉ ሰማይ የደረሰውን፣

የሊባኖስን ዝግባ አሦርን ተመልከት።

4ውሆች አበቀሉት፤

ጥልቅ ምንጮች አሳደጉት፤

ጅረቶቻቸው ፈሰሱ፤

የሥሮቹንም ዙሪያ ሁሉ አረሰረሱ፤

በመስኩ ላይ ወዳሉት ዛፎች ሁሉ፣

መስኖዎቻቸውን ለቀቁት።

5ስለዚህ በደን ካሉት ዛፎች ሁሉ፣

እጅግ ከፍ አለ፤

ቅርንጫፎቹ በዙ፤

ቀንበጦቹ ረዘሙ፤

ከውሃውም ብዛት የተነሣ ተስፋፉ።

6የሰማይ ወፎች ሁሉ፣

በቅርንጫፎቹ ላይ ጐጇቸውን ሠሩ፤

የምድር አራዊት ሁሉ፣

ከቅርንጫፎቹ ሥር ግልገሎቻቸውን ወለዱ።

ታላላቅ መንግሥታትም ሁሉ፣

ከጥላው ሥር ኖሩ።

7ከተንሰራፉት ቅርንጫፎቹ ጋር፣

ውበቱ ግሩም ነበር፤

ብዙ ውሃ ወዳለበት፣

ሥሮቹ ጠልቀው ነበርና።

8በእግዚአብሔር ገነት ያሉ ዝግባዎች፣

ሊወዳደሩት አልቻሉም፤

የጥድ ዛፎች፣

የእርሱን ቅርንጫፎች አይተካከሉትም፤

የአስታ ዛፎችም፣

ከእርሱ ቅርንጫፎች ጋር አይወዳደሩም፤

በእግዚአብሔር ገነት ያለ ማናቸውም ዛፍ፣

በውበት አይደርስበትም።

9በብዙ ቅርንጫፎች፣

ውብ አድርጌ ሠራሁት፤

በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ፣

በገነት ያሉትን ዛፎች የሚያስቀና አደረግሁት።

10“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥቅጥቅ ባለው ቅጠል ላይ ጫፉን ከፍ በማድረግ ራሱን በማንጠራራቱ፣ በርዝማኔውም በመኵራራቱ፣ 11እንደ ክፋቱ መጠን የሥራውን ይከፍለው ዘንድ፣ ለአሕዛብ ገዥ አሳልፌ ሰጠሁት። አውጥቼ ጥዬዋለሁ፤ 12ከአሕዛብ ወገን እጅግ ጨካኝ የሆኑትም ባዕዳን ሰዎች ቈራርጠው ጣሉት። ቀንበጦቹ በተራራዎቹና በሸለቆዎቹ ሁሉ ላይ ወድቀዋል፤ ቅርንጫፎቹም በውሃ መውረጃዎቹ ሁሉ ላይ ተሰባብረው ወድቀዋል፤ የምድሪቱ ሰዎች ሁሉ ከጥላው ሥር በመውጣት ትተውት ሄደዋል። 13የሰማይ ወፎች ሁሉ በወደቀው ዛፍ ላይ ሰፈሩ፤ የምድር አራዊት ሁሉ በወደቀው ዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ሰፈሩ። 14ስለዚህ በውሃ አጠገብ ያለ ማንኛውም ዛፍ፣ ጫፎቹን ችምችም ካለው ቅጠል በላይ ከፍ በማድረግ፣ ከእንግዲህ ራሱን በትዕቢት አያንጠራራም። ከእንግዲህ ውሃ በሚገባ ያገኘ ማንኛውም ዛፍ ወደዚህ ዐይነቱ ከፍታ አይደርስም። ሁሉም ከምድር በታች ወደ ጕድጓድ ከሚወርድ ሟች ጋር አብሮ እንዲሞት ተወስኖበታልና።”

15“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወደ መቃብር31፥15 ዕብራይስጡ ሲኦል ይላል፤ እንዲሁም በ16 እና 17 በወረደበት ቀን ጥልቅ ምንጮችን ስለ እርሱ በሐዘን ሸፈንኋቸው፤ ወንዞቹን ገታሁ፤ ታላላቅ ፈሳሾችም ተቋረጡ። በእርሱም ምክንያት ሊባኖስን ጨለማ አለበስሁ፤ የደን ዛፎችም ሁሉ ደረቁ። 16ወደ ጕድጓድ ከሚሄዱት ጋር ወደ መቃብር ባወረድሁት ጊዜ ሲወድቅ በተሰማው ድምፅ አሕዛብ ደነገጡ። ከዚያም የዔድን ዛፎች ሁሉ፣ ምርጥና ልዩ የሆኑት የሊባኖስ ዛፎች፣ ውሃ የጠገቡትም ዛፎች ሁሉ ከምድር በታች ሆነው ተጽናኑ። 17ከአሕዛብ መካከል ከእርሱ ጋር ያበሩ፣ በጥላው ሥር የኖሩ፣ በሰይፍ ከሞቱት ጋር ለመቀላቀል ወደ መቃብር ወርደዋል።”

18“ ‘በዔድን ካሉት ዛፎች በውበትና በትልቅነት የሚወዳደርህ የትኛው ነው? ይሁን እንጂ አንተም እንደዚሁ ከዔድን ዛፎች ጋር ከመሬት በታች ትወርዳለህ፤ በሰይፍ ከተገደሉት፣ ካልተገረዙትም መካከል ትጋደማለህ።

“ ‘እንግዲህ ፈርዖንና ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝቡ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”