Забур 92 – CARS & NASV

Священное Писание

Забур 92:1-5

Песнь 92

1Вечный царствует.

Он облачён величием,

облачён Вечный и силою препоясан.

Мир стоит твёрдо

и не поколеблется.

2Престол Твой утверждён издревле;

Ты – испокон веков.

3Возвышают потоки, Вечный,

возвышают потоки голос свой,

возвышают потоки волны свои.

4Но сильнее шума всех вод,

сильнее могучих волн морских –

Вечный, Который живёт в вышине небес.

5Заповеди Твои надёжны.

Дому Твоему, Вечный,

принадлежит святость навек.

New Amharic Standard Version

መዝሙር 92:1-15

መዝሙር 92

ጻድቅ ሰው ሲደሰት

በሰንበት ቀን የሚዘመር መዝሙር፤ ማሕሌት።

1እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፤

ልዑል ሆይ፤ ለስምህ መዘመር ጥሩ ነው፤

2ምሕረትህን በማለዳ፣

ታማኝነትህንም በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፤

3ዐሥር አውታር ባለው በገና፣

በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ ጥሩ ነው።

4እግዚአብሔር ሆይ፤ በሥራህ ስለ ተደሰትሁ፣

ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ።

5እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው!

ሐሳብህስ ምን ያህል ጥልቅ ነው!

6ደነዝ ሰው ይህን አያውቅም፤

ነኁላላም አያስተውለውም።

7ክፉዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ፣

ክፉ አድራጊዎች ቢለመልሙ፣

ለዘላለሙ ይጠፋሉ፤

8እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም ልዑል ነህ።

9ጠላቶችህ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፤

ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይበተናሉ።

10የእኔን ቀንድ ግን እንደ አውራሪስ ቀንድ92፥10 ጥንካሬን የሚያመለክት ነው። ከፍ ከፍ አደረግኸው፤

በለጋ ዘይትም አረሰረስኸኝ።

11ዐይኖቼ የባላንጦቼን ውድቀት አዩ፤

ጆሮዎቼም የክፉ ጠላቶቼን ድቅቀት ሰሙ።

12ጻድቃን እንደ ዘንባባ ይንሰራፋሉ፤

እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይንዠረገጋሉ።

13በእግዚአብሔር ቤት ተተክለዋል፤

በአምላካችንም አደባባይ ይንሰራፋሉ።

14ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ፤

እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ።

15እግዚአብሔር ትክክለኛ ነው፤

እርሱ ዐለቴ ነው፤ በእርሱ ዘንድ እንከን የለም” ይላሉ።