Забур 35 – CARS & NASV

Священное Писание

Забур 35:1-13

Песнь 35

1Дирижёру хора. Песнь Давуда, раба Вечного.

2Грех побуждает нечестивого

из глубин его сердца;

он не боится Всевышнего.

3Льстит он себе в своих же глазах,

что ищет порок свой,

чтобы возненавидеть его35:3 Или: «Он так превозносит себя, что не видит порок свой, чтобы возненавидеть его»..

4Слова его уст полны беззакония и обмана;

он отрёкся от мудрости и не делает добра.

5Даже на ложе своём замышляет он беззаконие.

Он встал на недобрый путь

и не отвергает зла.

6Вечный, милость Твоя до небес,

до облаков Твоя верность!

7Праведность Твоя велика, как горы,

Твоя справедливость глубока, как бездна!

Вечный, Ты хранишь человека и зверя!

8Милость Твоя, Всевышний, драгоценна!

В тени Твоих крыл укрываются смертные.

9Пируют они от щедрот Твоего дома;

из реки отрад Твоих Ты их поишь.

10Ведь у Тебя источник жизни,

и жизнь наша полна света,

когда Ты даёшь Свой свет.

11Излей Свою милость на знающих Тебя,

праведность Свою – на правых сердцем.

12Да не наступит на меня нога гордеца;

да не изгонит меня рука нечестивого.

13Посмотри, как пали беззаконники:

повергнуты они и не могут подняться.

New Amharic Standard Version

መዝሙር 35:1-28

መዝሙር 35

የተጨቈነ ሰው ጸሎት

የዳዊት መዝሙር።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚታገሉኝን ታገላቸው፤

የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።

2ትልቁንና ትንሹን ጋሻ ያዝ፤

እኔንም ለመርዳት ተነሥ።

3በሚያሳድዱኝ ላይ፣

ጦርና ጭሬ ምዘዝ፤35፥3 ወይም …መንገድ ዝጋ

ነፍሴንም፣

“የማድንሽ እኔ ነኝ” በላት።

4ሕይወቴን የሚፈልጓት፣

ይቅለሉ፣ ይዋረዱ፤

እኔን ለማጥፋት የሚያሤሩ፣

ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

5በነፋስ ፊት እንዳለ እብቅ ይሁኑ፤

የእግዚአብሔር መልአክ ያሳድዳቸው።

6መንገዳቸው ጨለማና ድጥ ይሁን፤

የእግዚአብሔር መልአክ ያባርራቸው።

7ያለ ምክንያት ወጥመዳቸውን በስውር አስቀምጠውብኛልና፤

ያለ ምክንያት ለነፍሴ ጕድጓድ ቈፍረውላታል።

8ያልታሰበ ጥፋት ይምጣባቸው፤

የሰወሩት ወጥመድ ይያዛቸው፤

ይጠፉም ዘንድ ወደ ጕድጓዱ ይውደቁ።

9ነፍሴም በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፤

በማዳኑም ሐሤት ታደርጋለች።

10የሠራ አካላቴ እንዲህ ይልሃል፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ማን አለ?

ድኻውን ከእርሱ ከሚበረቱ፣

ችግረኛውንና ምስኪኑን ከቀማኞች ታድናለህ።”

11ጨካኝ ምስክሮች ተነሡ፤

ስለማላውቀውም ነገር ጠየቁኝ።

12በበጎ ፈንታ ክፉ መለሱልኝ፤

ነፍሴንም ብቸኛ አደረጓት።

13እኔ ግን እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፤

ነፍሴንም በጾም አደከምኋት፤

ጸሎቴም መልስ ዐጥቶ ወደ ጕያዬ ተመለሰ።

14ለወዳጄ ወይም ለወንድሜ እንደማደርግ፣

እየተንቈራጠጥሁ አለቀስሁ፤

ለእናቴም እንደማለቅስ፣

በሐዘን ዐንገቴን ደፋሁ።

15እነርሱ ግን እኔ ስሰናከል በእልልታ ተሰበሰቡ፤

ግፈኞች በድንገት ተሰበሰቡብኝ፤

ያለ ዕረፍትም ቦጫጨቁኝ።

16እንደ ምናምንቴዎች አፌዙብኝ፤35፥16 ሰብዓ ሊቃናት እንዲሁ ሲሆን፣ በዕብራይስጥ ግን ምናምንቴ ፌዘኞች ማለት ሊሆን ይችላል።

ጥርሳቸውንም አፋጩብኝ።

17ጌታ ሆይ፤ እስከ መቼ ዝም ብለህ ታያለህ?

ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው፣

ብርቅ ሕይወቴን ከአንበሶች ታደጋት።

18በታላቅ ጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ፤

ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበትም አወድስሃለሁ።

19ከምድር ተነሥተው ጠላቶቼ የሆኑት፣

በላዬ ደስ አይበላቸው፤

እንዲያው የሚጠሉኝ፣

በዐይናቸው አይጣቀሱብኝ።

20የሰላም ንግግር ከአፋቸው አይወጣም፤

ዳሩ ግን በምድሪቱ በጸጥታ በሚኖሩት ላይ፣

ነገር ይሸርባሉ።

21አፋቸውን አስፍተው ከፈቱብኝ፤

“ዕሠይ! ዕሠይ! በዐይናችን አየነው” አሉ።

22እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን አይተሃልና ዝም አትበል፤

ጌታ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ።

23አምላኬ፣ ጌታዬ፤ ለእኔ ለመሟገት ተነሥ!

ልትከራከርልኝም ተንቀሳቀስ።

24እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ በጽድቅህ ፍረድልኝ፤

በእኔም ላይ ደስ አይበላቸው።

25በልባቸው፣ “ዕሠይ! ያሰብነው ተሳካ!

ዋጥ አደረግነውም” አይበሉ።

26በጭንቀቴ ደስ የሚላቸው፣

ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤

በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣

ዕፍረትንና ውርደትን ይከናነቡ።

27ፍትሕ ማግኘቴን የሚወድዱ፣

እልል ይበሉ፤ ሐሤትም ያድርጉ፤

ዘወትርም፣ “የባሪያው ሰላም ደስ የሚለው፣

እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ።

28አንደበቴ ጽድቅህን፣

ምስጋናህንም ቀኑን ሙሉ ይናገራል።