Joël 3 – BDS & NASV

La Bible du Semeur

Joël 3:1-5

Le jour de l’Eternel à la fin des temps

L’effusion de l’Esprit

1Après cela, ╵moi, je répandrai mon Esprit ╵sur tout le monde.

Vos fils, vos filles prophétiseront.

Vos vieillards, par des songes,

vos jeunes gens, par des visions, ╵recevront des révélations3.1 Les v. 1-5 sont cités en Ac 2.16-21. Pour l’effusion de l’Esprit, voir Es 32.15 ; 44.3 ; Jr 31.33-34 ; Ez 36.26-27 ; 39.29 ; Za 12.10-13..

2Et même sur les serviteurs, ╵sur les servantes,

moi, je répandrai mon Esprit ╵en ces jours-là.

3Je produirai ╵des signes prodigieux

dans le ciel, sur la terre :

du sang, du feu ╵et des colonnes de fumée.

4Et le soleil s’obscurcira,

la lune deviendra de sang

avant que vienne ╵le jour de l’Eternel,

ce jour grand et terrible.

5Alors tous ceux ╵qui invoqueront l’Eternel ╵seront sauvés3.5 Voir Dn 12.1. Cité en Rm 10.13. :

selon ce qu’a dit l’Eternel3.5 selon ce qu’a dit l’Eternel: voir Ab 17 ; Es 37.32.,

il y aura, ╵des rescapés

sur le mont de Sion ╵et à Jérusalem3.5 il y aura… Jérusalem. Sens obtenu en adoptant une légère modification du texte hébreu traditionnel et d’après Ab 17 ; Es 37.32. Le texte hébreu traditionnel a : sur le mont Sion, et dans Jérusalem, il y aura des rescapés, selon ce qu’a dit l’Eternel, et parmi les survivants que l’Eternel appellera (la fin du verset n’est pas compréhensible). Au lieu de des rescapés, certains traduisent la délivrance.,

les survivants ╵que l’Eternel appellera3.5 Réminiscence en Ac 2.39..

New Amharic Standard Version

ኢዩኤል 3:1-21

የተፈረደባቸው ሕዝቦች

1“በዚያ ዘመን፣ በዚያ ጊዜ፣

የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮ ስመልስ፣

2አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤

ወደ ኢዮሣፍጥም3፥2 ኢዮሣፍጥ፣ የስሙ ትርጕም እግዚአብሔር ይፈርዳል ማለት ነው፤ 12 ላይም እንዲሁ፤ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤

ስለ ርስቴ፣ ስለ ሕዝቤ፣ ስለ እስራኤል፣

በዚያ ልፈርድባቸው እገባለሁ፤

ምድሬን ከፋፍለዋል፤

ሕዝቤንም በሕዝቦች መካከል በታትነዋልና።

3በሕዝቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤

ወንዶች ልጆችን በዝሙት ዐዳሪዎች ለወጡ፤

ወይን ጠጅ ለመጠጣትም፣

ሴቶች ልጆችን ሸጡ።

4“ጢሮስና ሲዶና እንዲሁም እናንተ የፍልስጥኤም ግዛቶች ሁሉ ሆይ፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ምን አላችሁ? ስላደረግሁት ነገር ብድር ልትመልሱልኝ ነውን? የምትመልሱልኝ ከሆነ፣ በፍጥነትና በችኰላ እናንተ ያደረጋችሁትን በራሳችሁ ላይ መልሼ አደርግባችኋለሁ። 5ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፤ የተመረጠውንም ንብረቴን ተሸክማችሁ ወደ ቤተ መቅደሳችሁ አስገብታችኋልና። 6ከገዛ ምድራቸው ልታርቋቸው፣ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሰዎች ለግሪኮች ሸጣችኋቸው።

7“እነሆ፤ እነርሱን ከሸጣችሁባቸው ቦታዎች አነሣሣቸዋለሁ፤ እናንተም ያደረጋችሁትን በገዛ ራሳችሁ ላይ እመልስባችኋለሁ። 8ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻችሁን ለይሁዳ ሰዎች ሸጣለሁ፤ እነርሱም መልሰው በሩቅ ላሉት ለሳባ ሰዎች ይሸጧቸዋል፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሯልና።

9በሕዝቦች መካከል ይህን ዐውጁ፤

ለጦርነት ተዘጋጁ፤

ተዋጊዎችን አነሣሡ፤

ጦረኞችም ሁሉ ቀርበው ያጥቁ።

10ማረሻችሁ ሰይፍ፣

ማጭዳችሁም ጦር እንዲሆን ቀጥቅጡት፤

ደካማውም ሰው፣

“እኔ ብርቱ ነኝ” ይበል።

11እናንት በዙሪያ ያላችሁ ሕዝቦች ሁላችሁ፤

ፈጥናችሁ ኑ፤ በዚያም ተሰብሰቡ።

እግዚአብሔር ሆይ፤ ተዋጊዎችህን ወደዚያ አውርድ!

12“ሕዝቦች ይነሡ፤

ወደ ኢዮሣፍጥም ሸለቆ ፈጥነው ይውረዱ፤

ዙሪያውን ባሉት ሕዝቦች ሁሉ ላይ ልፈርድ፣

በዚያ እቀመጣለሁና።

13ማጭዱን ስደዱ፤

መከሩ ደርሷልና፤

ኑ ወይኑን ርገጡ፤

የወይን መጭመቂያው ሞልቶ፣

ከጕድጓዶቹም ተርፎ ፈስሷልና፤

ክፋታቸው እንደዚህ ታላቅ ነው።”

14ብዙ ሕዝብ፣ በጣም ብዙ ሕዝብ፣

ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ ተሰብስቧል፤

ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ፣

የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና።

15ፀሓይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤

ከዋክብትም ከእንግዲህ አያበሩም።

16እግዚአብሔር ከጽዮን ጮኾ ይናገራል፤

ከኢየሩሳሌም ያንጐደጕዳል፤

ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤

እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፣

ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።

በረከት ለእግዚአብሔር ሕዝብ

17“ከዚያም እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር

በቅዱሱ ተራራዬ በጽዮን እንደምኖር ታውቃላችሁ፤

ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፤

ከእንግዲህም ወዲያ ባዕዳን አይወርሯትም።

18“በዚያ ጊዜ ተራሮች፣ አዲስ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤

ኰረብቶችም ወተት ያፈስሳሉ፤

በይሁዳ ያሉ ሸለቆዎች3፥18 ወይም የሸጢም ሸለቆ ሁሉ ውሃ ያጐርፋሉ፤

ከእግዚአብሔር ቤት ምንጭ ይፈልቃል፤

የሰጢምን ሸለቆ ያጠጣል።

19ግብፅ ባድማ፣

ኤዶምም ምድረ በዳ ትሆናለች፤

በምድራቸው ንጹሕ ደም በማፍሰስ፣

በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጽመዋልና።

20ይሁዳ ለዘላለም፣

ኢየሩሳሌምም ለትውልድ ሁሉ መኖሪያ ትሆናለች፤

21ደማቸውን እበቀላለሁ፤

በደለኛውንም ንጹሕ አላደርግም።”

እግዚአብሔር በጽዮን ይኖራል!